group-telegram.com/MedinaTube/1283
Last Update:
ሰይዲና ዑመር በአንድ ወቅት ወደ ረሱል ሄዱና ሰይዲና አባበክርን እንዲህ ሲሉ ከሰሱ...
"ሁሌም አባ በክር እኔ ሰላምታ ካለቀረብኩለት ሰላምታን ቀድሞ አያቀርብልኝም አላቸው"
ረሱሉም አባ በክር ሲመጣ ጠየቁት ለምን እንዲህ
ታደርጋለህ አባበክር አሉት ....አባ በክርም እንዲህ ሲል መለሰላቸው...
እርሶ ሙስሊም ወንድሙን ሰላምታ ቀድሞ
ያቀረበለት ሰው ጀነት ላይ ህንፃ ይገነባለታል ስትሉ
ሰምቻለሁና ያ ህንፃ ለዑመር እንዲገነባለት ፈልጌ ነው አላቸው ...ዑመርም ይህን ሲሰሙ አለቀሱ🥺😊
እንዲህ ነበሩ በረሱሉ ተርቢያ የተገነብ ሰሀቦች
በዲን የተሳሰረ ውብ ወንድማማችነታቸው
ይህ ነው እንግዲህ ውብ ኢስላም ይህ ነው
እውነተኛው ወንድማማችነች ....
አላህ ይህንን ምርጥ ትውልድ በማይሻለው
ውብ ቃሉ በማረ አገላለፅ ፈለጋቸውን እንከትል
ዘንዳ እንዲህ ይገልፅልናል አስተውሉትማ...😊
{مُّحَمَّدٌ رَّسُولُ اللَّهِ ۚ وَالَّذِينَ مَعَهُ أَشِدَّاءُ عَلَى الْكُفَّارِ رُحَمَاءُ بَيْنَهُمْ ۖ تَرَاهُمْ رُكَّعًا سُجَّدًا يَبْتَغُونَ فَضْلًا مِّنَ اللَّهِ وَرِضْوَانًا ۖ سِيمَاهُمْ فِي وُجُوهِهِم مِّنْ أَثَرِ السُّجُودِ ۚ ذَٰلِكَ مَثَلُهُمْ فِي التَّوْرَاةِ ۚ وَمَثَلُهُمْ فِي الْإِنجِيلِ كَزَرْعٍ أَخْرَجَ شَطْأَهُ فَآزَرَهُ فَاسْتَغْلَظَ فَاسْتَوَىٰ عَلَىٰ سُوقِهِ يُعْجِبُ الزُّرَّاعَ لِيَغِيظَ بِهِمُ الْكُفَّارَ ۗ وَعَدَ اللَّهُ الَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ مِنْهُم مَّغْفِرَةً وَأَجْرًا عَظِيمًا}
"የአላህ መልክተኛ ሙሐመድ እነዚያም ከእርሱ ጋር ያሉት (ወዳጆቹ) በከሓዲዎቹ ላይ ብርቱዎች በመካከላቸው አዛኞች ናቸው፡፡ አጎንባሾች፣ ሰጋጆች ኾነው ታያቸዋለህ፡፡ ከአላህ ችሮታንና ውዴታን ይፈልጋሉ፡፡ ምልክታቸው ከስግደታቸው ፈለግ ስትኾን በፊቶቻቸው ላይ ናት፡፡ ይህ በተውራት (የተነገረው) ጠባያቸው ነው፡፡ በኢንጂልም ውስጥ ምሳሌያቸው ቀንዘሉን አንደአወጣ አዝመራና፣ (ቀንዘሉ) እንዳበረታው፣ እንደወፈረምና፣ ገበሬዎቹን የሚያስደንቅ ኾኖ በአገዳዎቹ ላይ ተስተካክሎ እንደ ቆመ (አዝመራ) ነው፡፡ (ያበረታቸውና ያበዛቸው) ከሓዲዎችን በእነርሱ ሊያስቆጭ ነው፡፡ አላህም እነዚያን ያመኑትንና ከእነርሱ በጎዎችን የሠሩትን ምሕረትንና ታላቅ ምንዳን ተስፋ አድርጎላቸዋል፡፡"
[ሱረቱል ፈትህ:29]
በዚህ ፍቅር የዚህ ስነምግባር ችቦ ለኳሽ በሆኑት
اللَّهُــمَّ صَلِّ وَسَـــلِّمْ وَبَارِك علــى نَبِيِّنَـــا مُحمَّدﷺ
💚💚💚
@medinatube
BY Medina Tube || መዲና ቲዩብ
Warning: Undefined variable $i in /var/www/group-telegram/post.php on line 260
Share with your friend now:
group-telegram.com/MedinaTube/1283