group-telegram.com/MedinaTube/1289
Create:
Last Update:
Last Update:
ሁሌም ይሄን ሃዲስ ሳነበው ስሰማው ወላሂ በጣም ይገርመኛል
የአላህ መልክተኛ (ሶ.ዐ.ወ) ተከታዩን ሲናገሩ አድምጫለሁ በማለት "አቡ ዐብዱረህማን ይናገራል፡-
‹‹ከናንተ በፊት የነበሩ በኒ እስራኤላውያኖች መሀከል ሶስት ሰዎች ለጉዞ ተንቀሳቀሱ በመንገድ ላይ እያሉ መሸባቸው ሲመሽባቸው ለአዳር ከአንድ ዋሻ ውስጥ ገቡ ከተራራ ላይ የነበረ አንድ ቋጥኝ ተንከባሎ ዋሻውን ዘጋባቸው ተጨነቁ አላህን በመልካም ተግባራችን ካለመነው በቀር ከዚ ቋጥኝ የሚያድነን ነገር ምንም አይኖርም ስንገባም ማንም ያየን የለም ተባባሉ ከመካከላቸው አንዳቸው እንዲህ አለ፡-
👉 ‹‹አላህ ሆይ! አዛውንት ወላጆች ነበሩኝ እነሱ ሁሌም ወተት አጠጣቸዋለሁ ከመጠጣታቸው በፊት ቤተሰቦቼንም ልጆቼንም እንዲሁም ባርያዎቼን ወተት አላጠጣም ነበር አንድ ቀን እንጨት ለቀማ ሩቅ ቦታ ሄድኩ አጋጣሚ አምሽቼ ነበር እና ስመጣ ወደቤት ተኝተው አገኘኋቸው ወተቱን አልቤ ልቀሰቅሳቸው ስል እንቅልፍ ላይ ሆነው መቀስቀስ አልፈልኩም አሳዘኑኝ እንቅልፍ ማቋረጥ ከነርሱ በፊትም ቤተሰቤን ማጠጣትም አልፈለኩም ወተት የያዘውን ዋንጫ በእጄ እንደያዝኩ መንቃታቸውን ስጠባበቅ ህጻናት ልጆቼ ከእግሮቼ ስር ይንጫጫሉ እባክህን አጠጣን እራበን እያሉ ያለቅሳሉ ይንጫጫሉ ሳላጠጣቸው ልጆቼም ተኙ ወላጆቼ ከእንቅልፋቸው እስኪነቁ ስጠብቅ ሳለ ነጋ ጎህ ቀደደ ወላጆቼም ተነስተው ወተታቸውን ጠጡ አላህ ሆይ! ይህንን ድርጊት የፈጸምኩት ያንተን ውዴታ ከጅዬ ከሆነ በዚህ ቋጥኝ ሰበብ ከደረሰብን መከራ አውጣን ቋጥኙ ትንሽ ከፈት አለ ትንሽየ አየር አገኙ ግን መውጣት የማያስችላቸው ያክል ነው፡፡
👉 ሌላኛው ደግሞ እንዲህ አለ ፡-
አንዲት ልጅ ነበረችኝ እጅግ አፈቅራት ነበር፡፡››
‹‹ አንድ ወንድ አንዲትን ሴት የሚያፈቅራትን የመጨረሻው የፍቅር እርከን ያህል አፈቅራታለሁ በወሲባዊ ተራክቦ ጠየቅኳት ፍቃደኛ አልሆነችም አላህን የምትፈራ ሴት ነበርች አንድ የድርቅ ዓመት ተከሰተ (እርዳታዬን ፈልጋ) ወደኔ መጣች የምፈልገውን እንድፈጽም ቃል አስገብቼ አንድ መቶ ሀያ ዲርሀም ሰጠኋት ቃሏን አከብራ መጣች
ከዚያም ወሲብ ልፈፅም ፊቷ ቀረብኩ ልጅቷም አላህን ፍራ ያለ አግባብ ያለ ሀላል ክብረ-ንጽህናዬን አታበላሽ አለችኝ ከ አጠገቧ ዘወር አልኩ ምንም ነገር ሳልፈጽም፡፡ ከማንም አብልጬ እዎዳታለሁ የሰጠኋትንም ወርቅ ብድር ተውኩላት አላህ ሆይ! ይህንን ተግባር የፈጸምኩት የአንተን ውዴታ ከጅዬ ከሆነ ካለንበት መከራ አውጣን::» ቋጥኙ ትንሽ ከፈት አለ መውጣት ግን አይችሉም፡፡››
ሦስተኛው እንዲህ አለ ፡-
👉 ‹‹ ሰራተኞች ቀጥሬ አሰራ ነበር ለሁሉም ያገለገሉበት ክፍያቸውን ከፈልኳቸው ከመካከላቸው አንዱ ሲቀር ድርሻውን እኔ ዘንድ ትቶ ሄደ አንሶኛል አልፈልግም ብሎ ትቶ ሄደ ትቶ የሂደውን ገንዘብ ጥራጥሬም ፍየልም በግም እየገዛሁ እያራባሁ እየገዛሁ እየሸጥኩ ብዙ ብሮች አተረፍኩለት ብዙ ሀብት እስኪሆን ድረስ ከዘመናት በኋላ ችግር አጋጥሞት ያ የቀጠርኩት ሰራተኛ ወደ እኔ መጣ እንዲህም አለኝ ፡- ‹‹ዐብደላህ ሆይ! ድርሻዬን ስጠኝ›› አለኝ ይህ የምትመለከተው ሁሉ ግመሉም ከብቱም ፍየሉም ባሪያውም ድርሻህ ነው አልኩት ‹‹ ዐብደላህ ሆይ! አትቀልድብኝ›› አለኝ፡፡ እየቀለድኩብህ አይደለም አልኩት ሁሉንም ተረክቦ እየነዳ ወሰደ አንዳችም ነገር አልተወም አላህ ሆይ! ይህንን የፈጸምኩት ያንተን ውዴታ በመሻት ከሆነ ካለንበት መከራ አውጣን::» ቋጥኙ ተከፈተ ወጥተው ጉዟቸውን ቀጠሉ፡፡
(ቡኻሪና ሙስሊም)
@MEDINATUBE
BY Medina Tube || መዲና ቲዩብ
Warning: Undefined variable $i in /var/www/group-telegram/post.php on line 260
Share with your friend now:
group-telegram.com/MedinaTube/1289