Telegram Group Search
#MoE

ከግንቦት 25-30/2017 ዓ.ም በተሰጠው የሪሚዲያል ተማሪዎች የማጠቃለያ ፈተና የተከለከሉ ነገሮችን ይዘው በተገኙ የተወሰኑ ተፈታኞች ላይ የዲሲፕሊን እርምጃ ተወስዷል። - ትምህርት ሚኒስቴር

የሪሚዲያል ፈተናውን ደኅንነት ለማስጠበቅ ሲባል የተወሰኑ ተፈታኖች ከፈተናው እንዲሰናበቱ መደረጉን በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈጻሚ ኤባ ሚጀና (ዶ/ር) ገልፀዋል፡፡

76,790 የሪሚዲያል ተማሪዎች ለማጠቃለያ ፈተናው መቀመጣቸውን መሪ ስራ አስፈጻሚው ተናግረዋል።

@tikvahuniversity
81👍33🙏1
#MoE

የ2017 ዓ.ም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመውጫ ፈተና በጥብቅ ዲሲፕሊን እየተሠ ነው። - ትምህርት ሚኒስቴር

ከሰኔ 2/2017 ዓ.ም ጀምሮ እየተሰጠ ለሚገኘው የመውጫ ፈተና የሚያገለግል የፈተና ፕሮቶኮል ተዘጋጅቶ ተፈታኞች እና ፈታኞች እንዲያውቁት መደረጉ ተገልጿል።

የፈተና ፕሮቶኮል ሰነዱ በመውጫ ፈተና የተከለከሉ ነገሮች፣ ተፈታኝ ሊከተሏቸው የሚገቡ የፈተና ዲሲፕሊን እንዲሁም ጥፋት ከተገኘ የሚወሰደው እርምጃን የሚገልጽ መሆኑን በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈጻሚ ኤባ ሚጀና (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

ፈተናው ከሌሎች ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተመድበው በመጡ ፈታኞች እየተሰጠ እንደሆነም መሪ ስራ አስፈጻሚው ገልፀዋል፡፡

በዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንቶች የሚመራ ግብረኃይል የፈተና አሰጣጡን በቅርብ ክትትል እንደሚያደርግ ተናግረዋል።

190,787 ተማሪዎች እስከ ሰኔ 10/2017 ዓ.ም የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና በመውሰድ ላይ ይገኛሉ።

@tikvahuniversity
143👎28
#MoE

የመውጫ ፈተና የሦስተኛ ቀን መርሐግብር
(ሰኔ 4/2017 ዓ.ም)

ፈተናው በ23 የትምህርት ፕሮግራምች በሦስት ክፍለ-ጊዜ ይሰጣል፦
ፈረቃ 1: ጠዋት ከ2:30-5:00 ሰዓት
ፈረቃ 2: ረፋድ ከ5:30-8:00 ሰዓት
ፈረቃ 3: ከሰዓት ከ8:30-11:00 ሰዓት

@tikvahuniversity
132👍28👎17😱7
አስር የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ምክትል ፕሬዝዳንቶች እና የምርምር ዳይሬክተሮች በዩናይትድ ስቴትስ ጉብኝት በማድረግ ላይ ይገኛሉ።

የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች እና የአስር ዩኒቨርሲቲዎች ኃላፊዎች በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በተዘጋጀ የዩኒቨርሲቲ ምርምር አስተዳደር ዓለም አቀፍ የጎብኚዎች የአመራር ፕሮግራም ላይ እየተሳተፉ መሆናቸው ታውቋል።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ፣ አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ፣ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ፣ ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ፣ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ፣ ጅማ ዩኒቨርሲቲ፣ ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ፣ መቐለ ዩኒቨርሲቲ እና ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተወካዮች እየተሳተፉ ነው።

ለሁለት ሳምንት በሚቆየው ጉብኝት፤ ተሳታፊዎች የዩናይትድ ስቴትስ ዩኒቨርሲቲ ምርምር አስተዳደር ጽ/ቤቶችን የተለያዩ ዘመናዊ አሰራሮች እየተመለከቱ መሆናቸው ተገልጿል።

@tikvahuniversity
83👎39
Tikvah-University
#MoH ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በAnesthesia ሙያ በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቃችሁ የጽሁፍ ፈተና ያለፋችሁና የተግባር ፈተና (OSCE) ለመውሰድ ምዝገባ ያጠናቀቃችሁ ተፈታኞች፥ የተግባር ፈተናው ግንቦት 22/2017 ዓ.ም እንደሚሰጥ ጤና ሚኒስቴር አሳውቋል። በፈተናው ዕለት ማንነታችሁን የሚገልጽ መታወቂያ (የቀበሌ መታወቂያ፣ ፓስፖርት፣ መንጃ ፍቃድ ወይም ሌላ በግልጽ የሚታይ ህጋዊ መታወቂያ) ይዛችሁ…
#MoH

ግንቦት 22/2017 ዓ.ም የተሰጠውን የተግባር ምዘና ፈተና (OSCE) የወሰዳችሁ የአንስቴዥያ ተመዛኞች ውጤታችሁን ኦንላይን መመልከት ትችላላችሁ። - ጤና ሚኒስቴር

የአንስቴዥያ ተመዛኞች http://hple.moh.gov.et/hple ላይ በመግባት ሙሉ ስም እና የፈተና መለያ ቁጥራችሁን በማስገባት የፈተና ውጤታችሁን መመልከት የምትችሉ መሆኑን ጤና ሚኒስቴር አሳውቋል።

በውጤታችሁ ላይ ቅሬታ ያላችሁ ተመዛኞች ከሰኔ 3/2017 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት አስር (10) ተከታታይ የሥራ ቀናት በስልክ ቁጥሮች 0115186275 / 0115186276 በመደወል ጥያቄዎቻችሁን ማቅረብ ትችላላችሁ ተብሏል።

ፈተናውን ያለፋችሁ ተመዛኞች ዛሬ ሰኔ 4/2017 ዓ.ም ስም ዝርዝራችሁ ወደ ክልል ተቆጣጣሪ አካላት የሚላክ በመሆኑ፥ ሌሎች ቅድመ ሁኔታዎችን በማሟላት የሙያ ፍቃድ ማውጣት የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል።

@tikvahuniversity
113😢10👏2
የመምህራን መውጫ ፈተና!

በክረምት የመምህራን ስልጠና መርሐግብር ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ለቆዩ 5,521 መምህራን የመውጫ ፈተና ይሰጣል። - ትምህርት ሚኒስቴር

በክረምት የመምህራን ስልጠና መርሐግብር ትምህርታቸውን በተለያዩ የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሲከታተሉ የነበሩ 5,521 መምህራን የመውጫ ፈተና እንደሚወስዱ ተገልጿል።

መምህራኑ የመውጫ ፈተናውን በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ በተዘጋጁ 35 የፈተና ማዕከላት ሰኔ 10/2017 ዓ.ም እንደሚወስዱ በሚኒስቴሩ የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈጻሚ ኤባ ሚጀና (ዶ/ር) ተናግረዋል።

መምህራኑ የመውጫ ፈተናውን ስልጠና በተከታተሉባቸው 24 የትምህርት ፕሮግራሞች እንደሚወሰዱ መሪ ስራ አስፈጻሚው ገልፀዋል።

ተፈታኞቹ ወደ ፈተና ማዕከላት ሲሔዱ ብሄራዊ መታወቂያ (ፋይዳ) መያዝና በትምህርት ሚኒስቴር የተዘጋጀውን የፈተና ፕሮቶኮል ማክበር ይገባቸዋል ብለዋል፡፡

@tikvahuniversity
140👍27😱9👎6😢5👏3🙏3🥰2
#AASTU

አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጄ ዩኒቨርሲቲ Virtual Desktop Infrastructure (VDI) የተሰኘ የማስተማሪያ ዲጂታል ላይብረሪ አስመርቋል።

ዲጂታል ላይብረሪው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን በበይነ መረብ ለመስጠት የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል።

ላይብረሪው ዘመኑ የሚጠይቀው የቴክኖሎጂ ከፍታ ያሟላና ከአንድ ማዕከል በተመሳሳይ ሰዓት የተለያዩ ፈተናዎችን ለመስጠት፣ ትምህርት ለማስተማር እንዲሁም ተማሪዎች ከአንድ ማዕከል የተለያዩ ሶፍትዌሮችን እንዲያገኙ የሚያስችል ነው ተብሏል።

@tikvahuniversity
👏8472🙏8👎5👍2😢1
#MoE

የመውጫ ፈተና የአራተኛ ቀን መርሐግብር
(ሰኔ 5/2017 ዓ.ም)

ፈተናው በ58 የትምህርት ፕሮግራምች በሦስት ክፍለ-ጊዜ ይሰጣል፦
ፈረቃ 1: ጠዋት ከ2:30-5:00 ሰዓት
ፈረቃ 2: ረፋድ ከ5:30-8:00 ሰዓት
ፈረቃ 3: ከሰዓት ከ8:30-11:00 ሰዓት

@tikvahuniversity
138👎18🙏13👍12😢1
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ የ6ኛ ክፍል መሰጠት ተጀምሯል።

ከ48 ሺህ በላይ የ6ኛ ክፍል ተማሪዎች የአንደኛ ደረጃ ትምህርት መልቀቂያ ፈተና እንደሚወስዱ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ገልጿል።

@tikvahuniversity
27👍3
2025/08/20 20:13:19
Back to Top
HTML Embed Code: