THIQAH
"ይቅርታ ለእስራኤል ጥሩ ነው" - ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ የእስራኤል ጠ/ሚኒስትር ኔታንያሁ የሙስና ወንጀላቸው በይቅርታ እንድታለፍላቸው በደብዳቤ ጠየቁ። ኔታንያሁ ለፕሬዝዳንት አይዛክ ሄርዞግ በፃፉት ደብዳቤ ለአመታት የቆየው የሙስና ክስ እንዲቆምላቸው መጠየቃቸውን አስታውቀዋል። ኔታንያሁ፣ "ይቅርታ ለእስራኤል ጥሩ ነው" ሲሉ ክሳቸው እንድቋረጥላቸው ተማጽነዋል ተብሏል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ "ይቅርታውን…
#Update
ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ ፍርድ ቤት ቀረቡ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትናንትናው እለት ለፕሬዚዳንት አይዛክ ሄርዞግ በፃፉት ደብዳቤ የሙስና ክሳቸው እንድቋረጥላቸው ጠይቀው ነበር።
ይሁን እንጅ ክሳቸው በይቅርታ እንዲታለፍ የጠየቁት ኔታንያሁ ዛሬ ፍርድ ቤት መቅረባቸው ተገልጿል።
የዛሬው የችሎት ውሎ ቀደም ብለው ቀጠሮ በተያዘላቸው በዲፕሎማሲ እና ደህንነት ቀጠሮ ምክንያት ለሌላ ጊዜ እንዲራዘም ቢጠይቁም ተቀባይነት አላገኘም።
በኔታንያሁ ውሳኔ የተበሳጩ ዜጎች በዛሬው እለት ተቃውሟቸውን አደባባይ ወጥተው አሰምተዋል። #anadoluagency
@ThiqahETH

❤13🤔7👏2
#Gambella
ጨቅላ ህፃንን ወንዝ ለመጣል ያስወሰናቸው ምን ይሆን?
የአንድ ቀን ጨቅላ ህፃን ወንዝ ውስጥ ተጥሎ ሞቶ መገኘቱን የመንገሽ ወረዳ ፖሊስ አስታውቋል።
ዛሬ በጋምቤላ ክልል ማጃንግ ብሔረሰብ መንገሽ ወረዳ በሶኖይ ቀበሌ 04 መንደር የአንድ ቀን ጨቅላ ህጻን ወንዝ ውስጥ ተጥሎ ሞቶ መገኘቱን የወረዳው ፖሊስ ጽ/ቤት ወንጀል መከላከል ክፍል ኃላፊ ኢንስፔክተር ቅድማኤል እንታኘን ገልጸዋል።
መረጃው የጋምቤላ ክልል ፓሊስ ኮሚሽን፣ እንዲሁም የመንገሽ ወረዳ ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው።
ህፃኑ ለምንና በማን እንደተጣለ ፓሊስ በግልጽ ያሳወቀው ነገር የለም።
ሰዎች "ልጆቻቸውን ጥለው ጠፉ፣ መጸዳጃ ቤት ከተቱ" ሲባል በተደጋጋሚ ይደመጣል፤ ሰዎቹ ለዚህ ውሳኔ የሚያደርሳቸው ችግር ምን እንደሆነ ግን በግለጽ አይነገርም።

😭13💔4❤2😢2
በዓለም ላይ 40.8 ሚሊዮን ሰዎች በኤች አይ ቪ ቫይረስ መያዛቸው ተገለጸ፡፡
የዓለም ጤና ድርጅት በዓለም አቀፍ ደረጃ 40.8 ሚሊዮን ሰዎች ኤች አይ ቪ በደማቸው ይገኛል ያለ ሲሆን፤ 64 በመቶው የሚሆኑት በአፍሪካ የሚኖሩ ናቸው፡፡
ድርጅቱ ዛሬ ታኅሣሥ 1 ቀን 2025 የሚከበረውን የዓለም ኤድስ ቀን ምክንያት በማድረግ ይፋ ባደረገው አዲስ ሪፖርት፤ በ2024 በአፍሪካ 26.3 ሚሊየን ሰዎች ኤች አይ ቪ በደማቸው ውስጥ እንደነበረባቸው ገልጿል።
በዚሁ ዓመት 650 ሺህ አዳዲስ ሰዎች በኤች አይ ቪ እንደተያዙ፤ 380,000 የሚሆኑት ደግሞ ህይወታቸው ማለፉን አስታውቋል፡፡
የዓለም ጤና ድርጅት ከ2010 ጀምሮ አዲስ የቫይረሱ ስርጭት በ40 በመቶ ፣ እንዲሁም ከኤችአይቪ ጋር የተያያዙ ሞቶች በ54 በመቶ መቀነሳቸውን ጠቅሶ፣ የውጭ እርዳታ ቅነሳዎች ግን እነዚህን ድሎች ሊቀለብሱ እንደሚችሉ ሰግቷል።
አስቸኳይ እና ቀጣይነት ያለው እርምጃ ካልተወሰደ እ.ኤ.አ. በ2030 ኤድስን እንደ ማህበረሰብ ጤና ስጋት ለማጥፋት የተያዘው እቅድ እንደማይሳካ ድርጅቱ በሪፖርቱ አስጠንቅቋል።

😭14❤7💔4🕊2
በኮንጎ 43 ሰዎች በኢቦላ ሕይወታቸው ማለፉ ተነገረ።
በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የኢቦላ ወረርሽኝ ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር መቻሉን የሀገሪቱ ጤና ሚኒስቴር ገልጿል።
የሀገሪቱ ጤና ሚኒስትር ሮገር ካምባ 53 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ፣ 43 የሚሆኑት ህይወታቸው አልፏል ብለዋል።
ወረርሽኙ እንዳይስፋፋ ለመከላከል ከ27,000 በላይ ለሚደርሱ ዜጎች ክትባት ተሰጥቷል ተብሏል። #associatedpress

😢7❤2💔2🤔1🕊1
"አብሮ መኖር ህልም የሆነበት ጊዜ ላይ ነው የምንገኘው። ሰላምና አንድነትን ማምጣት ይቻላል፣ አለመተማመን እና ፍረጃ ግን ሁሌም ሳይጠቅሙን ይኖራሉ" - ፖፕ ሊዮ 14ኛ
ሊባኖስ የሚገኙት ፖፕ ሊዮ 14ኛ ሰላም እንድሰፍን ጠየቁ።
"አብሮ መኖር ህልም የሆነበት ጊዜ ላይ ነው የምንገኘው" ያሉት ሊቀ ጳጳሱ "ሰላምና አንድነትን ማምጣት ይቻላል፣ አለመተማመን እና ፍረጃ ግን ሁሌም ሳይጠቅሙን ይኖራሉ" ብለዋል።
ፖፕ ሊዮ 14ኛ ከሊባኖሱ ጉብኝት በፊት በቱርክ የሶስት ቀን ጉብኝት ማድረጋቸው ተገልጿል። #euronews

❤13🙏5👏1
"ወንድሜ በህይወት ቢኖርም ህሊናው ተጎድቷል" - የጠቅላይ ሚኒስትር ካህን እህት
የቀድሞው የፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር ኢምራን ካህን በእስር ቤት "ህይወታቸው አልፏል" መባሉ ውሸት መሆኑ ተገለጸ።
የሞት መረጃዎች መውጣታቸውን ተከትሎ የኢምራን ደጋፊዎች አደባባይ በመውጣት ከእስር እንዲለቀቁ ጠይቀዋል።
ዛሬ በአዲያላ ማረሚያ ቤት ተገኝታ የጠየቀችው እህቱ ኡዝማ ካህን "ሙሉ ጤንነቱ ጥሩ ነው" ብላለች።
የጠቅላይ ሚኒስትሩ እህት "ወንድሜ በህይወት ቢኖርም ህሕሊናው ተጎድቷል" ስትል ተናግራለች።
"በኢምራን ላይ የሚፈጠር ችግር በፓኪስታን የፀጥታ ስርዓት ላይ የረጅም ጊዜ ጠባሳ ያሳርፋል" በማለት አስጠንቅቃለች።
ኡዝማ ወንድሟን ለመጠየቅ ከአንድ ሳምንት በላይ ስትደራደር መቆየቷን ተናግራለች። #times

❤6😢5🤔2
#AddisAbabapolice
የሁለት ሰዎችን ህይወት አጥፍቶ የተሰወረን ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ማዋሉን ፓሊስ አስታወቀ።
የወንጀል ድርጊቱ የተፈጸመው ህዳር 04 እና 05 ቀን 2018 ዓ/ም በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 06 ልዩ ቦታው 23 ቀበሌ መዝናናኛ ክበብ አካባቢ መሆኑን የአዲስ አበባ ፓሊስ ጠቅላይ መምሪያ ገልጿል።
ተከሳሽ እሱ ያውቃል ቢያዝን ከባለቤቱ ከወ/ሮ ሐመልማል አለምነህ ጋር በትዳር ተጣምረው መኖር ከጀመሩ አራት ወራትን አስቆጥረዋል፡፡
ተከሳሽ ከባለቤቱ ጋር በኪራይ ከሚኖሩበት ቤት ህዳር 04 ቀን 2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 4 ሰዓት ላይ ከሌላ ወንድ ጋር ስልክ ትደዋወያለሽ በሚል ቂም በቀል በመነሳሳት ሟችን አንገቷን በማነቅ ህይወቷ እንዲያልፍ በማድረግ በር ዘግቶባት ከአካባቢው ለጊዜው መሰወሩን አስረድቷል።
ተከሳሹ ከአንድ ቀን በኋላ ህዳር 05 ቀን 2018 ዓ/ም ባለቤቱን ከገደለበት መኖሪያ ግቢ ተመልሶ በመምጣት ከእዚህ ቀደም ከባለቤቱ ጋር በሚፈጠረው ፀብ ያሸማግል የነበረን አለባቸው አየለ የተባለን ጎረቤቱን በሟች ባለቤቱ ይጠረጥረው ስለነበር በስምንት ጥይት ህይወቱ እንዲያልፍ በማድረግ ተሰውሯል።
የአዲስ አበባ ፖሊስ የወንጀል ምርመራና ክትትል ክፍሉ የወንጀል ስፍራው በመገኘት የሟች አለባቸው አየለን አስከሬን በማንሳትና ከአካባቢው በሰበሰበው መረጃ መነሻነት የሟች መኖሪያ ቤት ሲከፈት የሐመልማል አለምነህ አስከሬን አግኝቷል።
ተገቢውን የሰውና የኤሌክትሮኒክስ መረጃዎችን በመከታተል ተጠርጣሪውን ህዳር 18 ቀን 2018 ዓ/ም ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሰሜን ሸዋ ዞን ሞላሌ ከተማ ከተደበቀበት መኖሪያ ቤት የግድያ ወንጀሉን ከፈጸመበት መሳሪያ ጋር በቁጥጥር ስር አውሎ መምርመራ መጀመሩንም አስታውቋል። #AddisAbabapolice

❤11😢7💔2👏1🤔1
#ስልጤ
"በእሳት አደጋው ህይወታቸውን ካጡት ሦስቱ ህፃናት ሁለቱ የ6 አመት እድሜ ያላቸው መንታያ እህትና ወንድም ሲሆኑ ሌላኛው የ2 አመት የጎረቤት ህፃን ነው" - ፓሊስ
በስልጤ ዞን ሚቶ ወረዳ በሰሶ ቆሻሜ ቀበሌ ቀጠና ሁለት ተብሎ በሚጠራው መንደር ለጊዜው መንስዔው ባልታወቀ የእሳት አደጋ የሦስት ህፃናት ህይወት ማለፉን የወረዳው ፖሊስ አስታውቋል።
አደጋው የደረሰው ህዳር 22 ቀን 2018 ዓ/ም ከቀኑ 10 ሰዓት 30 ገደማ መሆኑን፣ እሳቱ ደጅ ላይ ካለ ገለባ መነሳቱን፣ ህፃናቱም ገለባ ውስጥ ተኝተው እንደነበር የወረዳው ፖሊስ አዛዥ ዋና ሳጂን ሙዴ ሚሴቦ ተናግረዋል።
በአደጋው ህይወታቸውን ካጡት ሦስቱ ህፃናት ሁለቱ የስድስት አመት እድሜ ያላቸው መንታያ እህትና ወንድም ሲሆኑ ሌላኛው የሁለት አመት የጎረቤት ህፃን መሆኑ አዛዡ ተናግረዋል።
ህፃናቱ ገለባ ውስጥ መተኛታቸው ስላልታወቀ ህብረተሰቡ በእሳት የተያያዘን የቆርቆሮ ክዳን መኖሪያ ቤት ተረባርቦ ካጠፋ በኋላ ቀድሞ በእሳት የታያዘውን ገለባ ለማጥፉት ሲሞከር የህፃናቱ በድን ገላ መገኘቱንም ተናግረዋል።
አዛዡ በመጨረሻም የህፃናቱን አስክሬን ለምርመራ ወደ ሆስፒታል መላኩን ገልጸው፣ ፖሊስ የአደጋውን መንስዔ በማጣራት ላይ መሆኑን ያስታወቁ ሲሆን፣ መረጃው የወረዳውና የክልሉ ፓሊስ ነው።

😭20😢8❤4👏1😱1🕊1
የቀድሞዋ የአውሮፓ ህብረት የውጭ ፖሊሲ ኃላፊ ፌዴሪካ ሞገርኒ በቁጥጥር ስር ዋሉ።
ከአውሮፓ የውጭ እርዳታ አገልግሎት (EEAS) ለዲፕሎማቶች ስልጠና እንዲውል የተበጀተ ገንዘብ በማጭበርበር ወንጀል ተጠርጥረው መያዛቸውን የቤልጅየም ፖሊስ አስታውቋል።
ሞገርኒ ያለመከሰስ መብታቸው ከተነሳ በኋላ የአውሮፓ የወንጀል ምርመራ ቢሮ (EPPO) የእስር ማዘዣ አውጥቶባቸዋል። #aa #brusselssignal
@ThiqahEth

❤3😢2
#Dessie
በደሴ ከተማ በትራፊክ አደጋ የሦስት ሰዎች ህይወት ማለፉ ተነገረ።
በአማራ ክልል ደሴ ከተማ ሰኞ ገበያ ክፍለ ከተማ ቢለን ተብሎ በተሰኘ ቦታ በደረሰ የመኪና አደጋ የሦስት ሰዎች ህይወት ማለፉን በከተማዋ ፖሊስ መምሪያ የ3ኛ ፖሊስ ጣቢያ ኃላፊ ኢንስፔክተር ፈቲያ ሀሰን ተናግረዋል።
አደጋው ዛሬ ከቀኑ 10 ሰዓት ገደማ መድረሱንም፣ አደጋው የጭነት ተሽከርካሪ መኪና በመገልበጡ ምክንያት መከሰቱን፣ በሁለትና ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድ ጉዳት መድረሱን ገልጸዋል።
በአደጋው በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን የገለጹት ኃላፊዋ፣ የተሽከርካሪው ሹፌር በህግ ስር ሆኖ ህክምና እየተከታተለ እንደሆነና የአደጋው መንስኤ እየተጣራ መሆኑን ተናግረዋል። #FMC

😭13❤5💔3🤔2
"ሶማሊያውያንን በእኛ ሀገር ማየት አልፈልግም" - ትራምፕ
ዶናልድ ትራምፕ የሶማሊያ ዜጎችን ከአሜሪካ ለቀው እንዲወጡ አስጠነቀቁ።
ፕሬዝዳንቱ "እውነት ለመናገር በፖለቲካ ትክክል ላይሆን ይችላል፣ ግን ሶማሊያውያንን በእኛ ሀገር ማየት አልፈልግም" ሲሉ ተደምጠዋል።
"እነሱ (የሶማሊያ ዜጎች) በእኛ ሀገር ላይ የጨመሩት ነገር የለም፣ በአጋጣሚ ሀገራቸው ደግሞ ጥሩ ሁኔታ ላይ አይደለችም" ብለዋል።
የትራምፕ አስተዳደር የኢምግሬሽንና ጉምሩክ አስፈፃሚ (ICE) ቢሮ ሰነድ አልባ ሶማሊያውያን ላይ ምርመራ እንዲጀምር ትዕዛዝ አስተላልፈዋል።
ቢሮው በተለይ የሶማሊያ ዜጎች በስፋት ይኖሩበታል በሚባለው የሚኒሶታ ከተማ ኢላማ ማድረጋቸው ተገልጿል። #euronews

👏12❤4😱4😡4🤔3🕊2
"ከአውሮፓ ጋር ወደ ጦርነት ከገባን ሩሲያ ታሸንፋለች" - ቭላድሚር ፑቲን
"ፑቲን ጦርነቱ ፍፃሜ እንዲያገኝ ይፈልጋሉ" - የትራምፕ ልዩ መልዕክተኛ
ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ለዩክሬን ጦርነት የአውሮፓ ሀገራትን ተጠያቂ አደረጉ።
የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ልዩ መልዕክተኛ ስቲቭ ዊትኮፍ እና አማቻቸው ጃሬድ ኩሽነር ሞስኮ በማቅናት ከፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ተወያይተዋል።
ፑቲን በሰጡት አስተያየት "ከአውሮፓ ጋር ወደጦርነት የመግባት እቅድ የለንም፣ ከገባን ግን ሩሲያ ታሸንፋለች" ሲሉ ተደምጠዋል።
ፕሬዝዳንቱ "አንድ ጊዜ ወደ ጦርነት ከገባን የሰላም ድርድር የሚባል ነገር አይኖርም" ብለዋል።
በዊትኮፍ የሚመራው የአሜሪካ ልዑክ በበኩሉ "ከሰላም አልራቅንም" ሲል ከፑቲን ጋር የነበረው ንግግር ተስፋ ሰጭ እንደነበር አስታውቋል።
ዊትኮፍ በሰጡት መግለጫ "ፑቲን ጦርነቱ ፍፃሜ እንዲያገኝ ይፈልጋሉ" ሲሉ ተናግረዋል። #politico #timeslive

❤20👏3😱1😢1😡1
የ45 እስራት የተፈረደባቸው የቀድሞው የሁንዱራንስ ፕሬዝዳንት በፕሬዝዳንት ትራምፕ ይቅርታ ከእስር ወጡ።
ፕሬዝዳንት ጁዋን ሄርናንዴዝ በአደንዛዥ እፅ እና የጦር መሳሪያ ዝውውር ወንጀል ተከሰው በአሜሪካ ታስረው ቆይተዋል።
ሄርናንዴዝ በፖሊስ የተያዙት በ2022 ሲሆን፣ ባለፈው አመት 2024 የ45 አመት እስር ተፈርዶባቸዋል።
የ57 አመቱ ጁዋን ሄርናንዴዝ በፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ይቅርታ ተደርጎላቸው ከእስር መውጣታቸውን ባለቤታቸው አና ግራሲያ አረጋግጠዋል።
ግራሲያ "ፕሬዚዳንት ትራምፕ አዲስ ተስፋ ስለሰጡን፣ ለእውነት ስለቆሙ ምስጋና ይገባቸዋል" በማለት አመስግነዋል። #havanatimes

👏12❤6🤔2
THIQAH
Photo
በእስያ የጎርፍ አደጋ 1400 ሰዎች ሲሞቱ፣ የጠፉት ቁጥር 1000 ደረሰ።
በኢንዶኔዥያ ብቻ 770 ሰዎች ሲሞቱ 463 የሚሆኑት መጥፋታቸው ተረጋግጧል።
በተመሳሳይ ሁኔታ አደጋው በበረታባት ሲሪላንካ 465 ሞት ሲመዘገብ፣ 366 ሰዎች ጠፍተዋል።
ታይላንድ በበኩሏ በአስከፊው የጎርፍ አደጋ 176 ዜጎቿ ህይወታቸው ማለፉን አስታውቃለች። #anadoluagency

😢7❤2💔1
THIQAH
"ሶማሊያውያንን በእኛ ሀገር ማየት አልፈልግም" - ትራምፕ ዶናልድ ትራምፕ የሶማሊያ ዜጎችን ከአሜሪካ ለቀው እንዲወጡ አስጠነቀቁ። ፕሬዝዳንቱ "እውነት ለመናገር በፖለቲካ ትክክል ላይሆን ይችላል፣ ግን ሶማሊያውያንን በእኛ ሀገር ማየት አልፈልግም" ሲሉ ተደምጠዋል። "እነሱ (የሶማሊያ ዜጎች) በእኛ ሀገር ላይ የጨመሩት ነገር የለም፣ በአጋጣሚ ሀገራቸው ደግሞ ጥሩ ሁኔታ ላይ አይደለችም" ብለዋል። የትራምፕ…
"የትራምፕ ንግግር የተሳሳተ አመለካከት ውጤት ብቻ ሳይሆን ስድብ ነው" - ሶማሊያ
ሶማሊያ በጠቅላይ ሚኒስትሯ አማካኝነት ትራምፕ ስደተኞች ላይ ያሰሙትን ንግግር ተቃወመች።
ጠቅላይ ሚኒስትር ሀምዛ አብዲ ባሬ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ "በሶማሊያ ዜጎች ላይ ያነጣጠረ አሉታዊ ንግግር አሰምተዋል" ብለዋል።
ባሬ "በቀላሉ ትቶ ማለፍ የተሻለ ነው" ሲሉ ተጨማሪ መረጃዎችን ከመስጠት ተቆጥበዋል።
ይሁን እንጂ የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ አሊ ኦማር "ሶማሊያውያን ከሚገኙበት ችግር ለማምለጥ ወይም ለመጥፋት ይጠቅማቸዋል" በማለት ተናግረዋል።
ኦማር "የትራምፕ ንግግር የተሳሳተ አመለካከት ውጤት ብቻ ሳይሆን ስድብ ነው" ሲሉ ገልጸዋል።
ሚኒስትር ዴዔታው "ዜጎቻችን ማንነታቸውን ለዓለም ለማሳየት በትብብር መቆም አለባቸው" በማለት አሳስበዋል። #aa
"ትራምፕ ሶማሊያውያንን በኛ ሀገር ማየት አልፈልግም" ሲሉ መናገራቸው ይታወሳል።

❤18🤔1😢1😭1
#EthiopianCoffee
ከዚህ ቀደም 9 ሺሕ ብር የነበረ የአንድ ፈረሱላ ቡና ዋጋ ወደ 20 ሺሕ ብር ናረ።
ይህን ያለው የኢትዮጵያ ቡና ማህበር፣ ላኪዎች በዚህ ዋጋ ቡና እየገዙ ለአለም ገበያ ማቅረብ እንደሚከብዳቸው፣ አርሶ አደሮች እና ላኪዎች ዋጋውን ከፍ ያደረጉት ወደፊት ይበልጥ ይጨምራል በሚል ግምት እንደሆነም ለሸገርኤፍኤም ገልጿል።
ወደ ውጪ ቡና የሚልኩ ነጋዴዎች ከአርሶ አደሮች እና አቅራቢዎች ምርቱን የሚገዙበት ዋጋ ከተወሰነ ጊዜ ወዲህ ከፍተኛ ጭማሪ ማሳየቱን ማህበሩ ተናግሯል፡፡
የማህበሩ ዋና ስራ አስኪያጅ ግዛት ወርቁ እንዳሉት ቀደም ሲል በፈረሱላ 8 ሺሕ እና 9 ሺሕ ብር ከአርሶ አደሮችና አቅራቢዎች ይገዛ የነበረ ቡና አሁን በፈረሱላ እስከ 20 ሺሕ ብር ገብቷል።
ዋጋው ወደ 20 ሺሕ ብር የተደረገው ከጊዜ በኋላ ይጨምራል በሚል ቢሆንም አሁን ያለው የዓለም አቀፍ ቡና መሸጫ ግን ዋጋው እንደሚጨመር ሳይሆን እንደሚቀንስ የሚያመለክት ነው ብለዋል።
ላኪዎች ከአርሶ አደሮች እና አቅራቢዎች ቡናን የሚገዘቡት ዋጋ ካልተስተካከለ ምርቱን ለአለም ገበያ ማቅረብ አስቸጋሪ እንደሚሆን በመስጋት፣ ዋጋው አሁን ባለበት የሚቀጥል ከሆነ ኢትዮጵያ የምታገኘው ገቢ ብቻ ሳይሆን ወደ ውጪ የምትልከው ቡና መጠንም እንደሚቀንስ አቶ ግዛት ገልጸዋል። #ShegerFm

❤5😢1
#Drivers
"በርካታ ሹፌሮች እና ረዳቶች ታግተው ተወስደዋል" - ማህበሩ
በአማራ ክልል ከበአዲስ ዘመን ጎንደር መንገድ ዛሬ በርካታ ሹፌሮችና ረዳቶች መታገታቸውን የኢትዮጵያ ከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማህበር አስታውቋል።
"25/03/2018 በአማራ ክልል ከአዲስ ዘመን ጎንደር መስመር ልዩ ስሙ ፈረንጅ ውሀ ተብሎ የሚጠረው አካባቢ በርካታ ሹፌሮች እና ረዳቶች ታግተው ተወስደዋል" ብሏል ማኀበሩ።
"ይህ መስመር አጋች ዘራፊ እና ገዳይ ከመብዛቱ የተነሳ መንገዱ የሲወል መንገድ ከሆነ የቆየ ቢሆንም እስካሁን መፍትሄ አልተገኘለትም" ያለው ማህበሩ፣ "በየቦታው ለሚገደል ለሚዘረፍ እና ለሚታገት አሽከርካሪ" ፍትህ እንዲሰጥ ጠይቋል።

❤10😢5🕊1
ዩናይትድ ኪንግደም በሩሲያ ተቋማት እና ግለሰቦች ላይ ማዕቀብ መጣሏን አስታወቀች።
ለንደን ማዕቀቡ በጂ አር ዩ የወታደራዊ ኢንተሊጀንስ ኤጀንሲ እና ማንነታቸው ባልተገለፀ የበይነ መረብ መረጃ ጠላፊ ባለሙያዎች ላይ ያነጣጠረ እንደሆነ ገልፃለች።
የመረጃ ጠላፊዎቹ 29155 ያልተሳኩ የበይነመረብ ጥቃቶች ፈፅመዋል ብላለች።
ማዕቀብ የተጣለባቸው አካላት በ2018 ተመርዘው በሞቱት ሰርጌ ስክሪባል እና ዩሊያ የተባሉ አባትና ልጅ እጃቸው እንዳለበት ገልፃለች። #theinsider

😡3👏1😱1😢1
THIQAH
"በማርበርግ በሽታ ህይወታቸው ያለፉ ሰዎች አስከሬን ለቤተሰብ አይሰጥም" ተባለ አስከሬናቸው እንደማይታጠብና፣ ደህንነቱ በተጠበቀ መንገድ የቀብር ስርዓታቸው እንደማፈጸም፣ ቀብር የተፈፀመባቸው ቦታዎችም በደንብ መጠበቅ እንዳለባቸው ተገልጿል። ማህበረሰቡ የበሽታውን ከባድነት ተረድቶ ይህንን ውሳኔ መቀበል እና መተባበር አለበት ተብሏል። በሌላ በኩል ቫይረሱ በወንድ የዘር ፈሳሽ ውስጥ ለአንድ አመት ጊዜ የሚቆይ…
"የማርበርግ ቫይረስ የሙከራ ክትባት" ለተጋላጭ ማህበረሰቦች ሊሰጥ መሆኑን ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።
የማርበርግ ቫይረስ ምላሽ ለመስጠት የሚደረገውን ጥረት የሚደግፍ 5,000 የማርበርግ ቫይረስ የሙከራ ክትባት ከአሜሪካ መንግስት በድጋፍ መገኘቱን ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
"ክትባቱን ለኢትዮጵያ የመድኃኒት አቅርቦት አገልግሎት የአሜሪካ በኢትዮጵያ አምባሳደር አርቪን ማሲንጋ አስረክበዋል" ተብሏል።
ክትባቱ በአርማወር ሃንሰን የምርምር ተቋም በሚመራ ፈጣን የደረጃ 2 ክሊኒካዊ ሙከራ ተደርጎለት ጥቅም ላይ እንደሚውል ደግሞ፣ የጤና ሚኒስትሯ መቅደስ ዳባ (ዶ/ር) ገልጸዋል።
የምርመራ ተቋሙ ከኢትዮጵያ የምግብ እና የመድኃኒት ባለስልጣን ጋር በመተባበር ቁጥጥር እንደሚያደርግ፣ ክትባቱን ከህዳር 29 ቀን ጀምሮ መስጠት እንደሚጀምር፣ የጤና ባለሙያዎችንና ከፍተኛ ተጋላጭ ለሆኑ ቡድኖች በቅድሚያ እንደሚሰጥ አስረድተዋል። #MoHEthiopia

🙏4❤2
የእስራኤል ጦር የደቡብ ሊባኖስ ነዋሪዎች አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ አሳሰበ።
በጅባ እና ማህሩና ከተማ የሚኖሩ ዜጎች በአስቸኳይ ለቀው እንዲወጡ መልዕክት መተላለፉን የጦሩ ቃል አቀባዩ አቢቼ አዲሬ አስታውቀዋል።
መልዕክቱ የተላለፈው የሂዝቦላ ወታደራዊ መሠረተ ልማት ላይ ጥቃት ለመፈጸም በማቀድ እንደሆነ ተናገረዋል። #lbc

❤4👏2🕊1