Telegram Group Search
#ደጉ ሙሀመድ❤️|| አዲስ መንዙማ አሚር ሁሴን ሰልሃዲን ሁሴን ሌሎችም አንጋፋ ማዲሆች ጋር ለረቢ የቀረበ…
MEDINA TUBE
ደጉ ሙሀመድ❤️|| አዲስ መንዙማ አሚር ሁሴን ሰልሃዲን ሁሴን ሌሎችም አንጋፋ ማዲሆች ጋር ለረቢ የቀረበ ስጦታ
@MEDINA_TUBE
@medinatube
ፈጥነው ይዘዙ ! በተለያዩ ዲዛይንና ከለር እንዳማራጫ ተሰርተው እርሶን የሚጠበሸቁ የመውሊድ ሂጃብና ቲሸርቶችን አዘጋጅተን እርሶን በመጠበቅ ላይ ነን ባሉበት ሆነው ባዘዙበት ጊዜ በፍጥነትና በጥራት አሰናቀርባለን! በተጨማሪ አረንጓዴ ሻል ይዘን ቀርበናል ይዘዙን!

ለማዘዝ 0938953867 ቴሌግራም @alifhitemat
ግሩፕአችን https://www.group-telegram.com/alifadvert
👍5
#ትኩረት ❗️❗️

ዛሬ እኛው የሱፍይ መሻይኽ ልጆች ነን የምንለው የሀድራ ወዳጅ ነን የምንል ሰዎች ይሄን ነገር አንድ ሆነን እነዚህን ልጆች ካልተቃወምነው ነገ ምን ሊመጣ እንደሚችል ማሰብ እንኳ አይቻልም!!!
የሰው ልጅ እንዴት ይሄን ያክል ይወርዳል ቆይ! እንዴት ሸሪአውን አያይም? እንዴት ለሚጠሩትስ ለትልቁ ሰው ለሰይዳችን صلى الله عليه وسلم ሀያዕ አይኖረውም!?

አላህን ፍሩ! ተሰዉፍ እና ሱፍያ ከነ ማዕረግና ክብሩ ከናነተ የጠራና ሃላፊነት የማይወስድ መሆኑን በስሜ ለመላው መድሕ ወዳድ ማረጋገጥ እንፈልጋለን ። የዚህ አይነቱን ስራ ከማንም በላይ ቅድሚያ የምቃወመው እኛው የሀድራ ወዳጆች ነን።

በመድህ ላይ ድንበር ታልፏል አስቸኳይ መልእክት! ይሄን ነሺዳ ቪዲዮ ለመስራት የተገደድነው የመድሁን አለም ለመታደግና ከመሸርሸር ለመጠበቅ ሲባል ነው። ቪዲዮውን አንሱት አልያ ዘመቻውን አጠናክረን ለመቀጠል እንገደዳለን ለወንድሞቻችን እንዲደርሳቸው ሼር ሼር

ብዙ ጊዜ በሚሰሩት ነሺዳ ላይ ትችት አይጠፋቸውም ሆኖም ግን እኔ በእራሴ ማሕበራዊ ሚድያ ላይ ወገቤን አስሬ ለእነዚህ ልጆች ተከራከራያለሁ ይህ ይታወቅልኝ ሆኖም ግን ትክክል ያልሆነ ነገር ስሰሩት ከመተቸት ወደኋላ አንልም።

ዛሬም ነገም ወደፊትም ለሱፊያ ማሕበረሰብ እና የመሻይኾቻችን መድህ በአደብ እንደሰሩ ለማሳወቅ እንፈልጋለን ይህን ነሺዳ ቪድዮ ከዩቲዩብ ቻናል ላይ ማታጠፉ ከሆነ አይታችሁ የማታውቁት ቅጣት እንቀጣቸዋለን።
@medinatube
😢10👍43🙏1
ወሀቢያዎች ከሚያናፍሱት ወሬ መካከል "መጀመሪያ መውሊድን የጀመሩት ዑበይዲዮች ናቸው የነሱን ፈለግ ነው የምትከተሉት ከነሱ ጋር ተመሳሰላችሁ"የሚለው ነው።በዚህም የሚፈልጉበት ለመውሊድ ያላቸውን ጥላቻ ለማንፀባረቅና በመውሊድ ዙሪያ መጥፎ ገፅታን ለመገንባት ነው።
ከመሰረቱ ዑበይዲዮች ማለት ከሞሮኮ አካባቢ ተነስተው እስከ ግብፅ ድረስ የተስፋፉ የጥመት አንጃዎች ነበሩ።
እኛ ለዚህ መልስ የምናቀርብላቸው በጥያቄ ይሆናል እሱም "እናንተ እንደምትሉት ከሆነ ኢብኑተይሚያ ስለ መውሊድ ሲናገር “መውሊድን ማላቅ ልዩ ቀን አድርጎ መያዝ የተወሰኑ ሰዎች እንደሚያደርጉት ማለት ነው፤ ለጥሩ እሳቤያቸውና ነቢዩን ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለምን ለማላቅ ለማክበር በመሆኑ ትልቅ አጅር አለው"ማለቱ የሚያሲዘው ዑበይዲዮች በግብፅ ምን ይሰሩ እንደነበር እያወቀ ነገር ግን የጀመሩት መወሊድ አጅር አለው እያለ ነው ማለት ነው።በዚህም አነሱን ያሞገሰና ያላቃቸው ሆነ ማለት ነው።እናንተ ደግሞ በተቃራኒው መውሊድን እነሱ ጀምረውታልና ጥመት ነው እያላችሁ ነው ሸይኻችሁ ደግሞ አጅር አለው እያለ ነው እንዴት ልትስማሙ ነው?

ወደኛ ስንመጣ መውሊድን ማክበር ለመቻሉ መረጃዎችን ስንጠቅስ ቁርኣንን ሐዲስንና ኢጅማዕን በማጣቀስ ነው የምናብራራው እንጂ በግብፅ የነበሩት እነንትና አክብረውታል በሚል አደለም።በመቀጠል ሙስሊም በዘገቡት ሶሒሕ ሐዲስ ላይ የዓሹራእ ቀንን ሱና ፆም እንድንፆም ከነቢዪ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም የመጣልን ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም አይሁዶችን በዛ ቀን ፆም ብለው ሲያሳልፉ አግኝተዋቸው ጠይቀዋቸው ከዛም እኛ ከናንት ለሙሳ የቀረብን ነን በማለት እሳቸውም ፆመው ኡመታቸውን እንዲፆሙ አመላከቱ ታዲያ ወሀቢያዎች ሆይ በናንተ አባባል መጀመሪያ አይሁዶች ስለቀደሙ ነቢዪ አይሁዶችን ተከተሉ ከነሱ ጋር ተመሳሰሉ እኛ አንፆምም ልትሉ ይሆን?

መውሊድን ባማረ ስብጥር እና በሃገር ደረጃ ማክበር የጀመሩት የኢርቢል ከተማ ንጉሱ አልመሊኩል ሙዞፈር አቡ ሰዒድ ኢብኑ ዘይኒዲን ኢብኒ በክተኪን እንደሆኑ ከጠቀሱ ዑለሞች መካክል አል ሓፊዙ አሲዩጢይ ሲሆኑ ከሱ በፊት መጀመሪያ አካባቢ በማክበር ከሚታወቁት መካከል ታላቅ ዓሊምና ሷሊሕ የሆኑት አልፈቂሁ አሻፊዒዩ ሙላ ዑመር አልመውሱሊይ አስከትሎም አል ቃዲ አለኽሚይ ይገኙበታል።

ወሀቢያዎች ለሙጃሂዱ #ሶላሑዲን አል አዩቢይ ጥላቻ እንዳላቸው ግልፅ ነው ምክንያቱም አሽዐሪይ ስለነበር።ለዛ የአል ሙጃሂድ ሶላሑዲን አል አዩቢይን እህት ያገቡት ንጉስ አል ሙዞፈረን ለማንቋሸሽ ደረጃቸውን በቻሉት መልኩ ለማውረድ ስብእናቸውን ለማጠልሸት የማይቆፍሩት ጉድጓድ የለም።ይሁንና ከራሳቸው ጎሳ የሆኑትን ወሀቢያዎች አጥብቀው የሚወዷቸውን የኢብኑ ተይሚያ ተማሪዎች ኢብኑ ከሲር እና አዘሀቢይ ስለ ንጉሱ አል ሙዞፈር የሚከተለውን በማለት የዚህን መልካም ጀግና መሪ ማንነት በኪታቦቻቸው አሰወፍረዋልና እሱን አጣቅሰን እንመልከት።ይህም ሁሌም ለወሀቢያዎች አንደሾህ ሆኖ ሲወጋቸው ይኖራል።

#ዘሃቢይ_ሲየር_አዕላሚ_ኑበላእ በሚባለው ኪታቡ ላይ 22ኛው ጁዝእ ከገጽ 335 እስከ 336 እንዲህ ሲል ስለ አመሊኩል ሙዞፈር ይጠቅሳል“አል መሊኩል ሙዞፈር...ሙጃሂዱን ሶላሁዲን አል አዩቢይን መኻደም ጀመረ አብሮትም ጂሃድ ወጣ ሶላሁዲን አል አዩቢይ አልመሊኩል ሙዞፈርን ወደደው በጣምም አስጠጋው እህቱንም ዳረው...ኢርቢልንም እንዲያስተዳድር ስልጣን ሰጠው...አል መሊኩል ሙዞፈር በጣም ሶደቃን ይወድ ነበር በየቀኑ ብዙ ዳቦ የሚያከፋፍል የነበረ ሲሆን...በየአመቱ ልብስ የሚያለብሳቸው፣ የሚመግባቸው፣ አንድ ዲናር ሁለት ዲናር የሚሰጣቸው ሰዎች ብዙ ናቸው...ለህመምተኞች ቤትን በመገንባት ሰኞና ሃሙስ ሁሌም እየመጣ ስለሁኔታቸው ይጠይቃቸዋል፣ይቀልዳቸዋል ከነሱ ጋርም ይውላል..."
ከዛም ሌሎች ስለሱ መልካም ነገሮችን ይዘረዝርና እንዲህ ይላል“በመውሊድ ላይ የሚያደርገውማ ለመግለጽ እጅጉን ይከብዳል...እንዳለ ኸልቁ ከዒራቅ እስከ አልጀሪያ ድረስ ወደሱ ይጎርፋሉ...ብዙ ዳሶች ይቆማሉ ይዋባሉምም...እዛም ላይ የውዳሴ ድምጾች ከፍ ይላሉ...እሱም በእያንዳንዱ ዳስ እየሄደ በቅርብ ሆኖ ይከታተላል ይመለከታል...ይህም ለቀናቶች ያህል የሚቀጥል ሲሆን...በመውሊዱ ላይ በጣም ብዙ ግመል፣በሬ፣በግ እና ፍየል ይታረዳሉ...ኢብኑ ዱህያ የሚባሉት ዓሊም የመውሊድ ኪታብ ጽፈው ለአልመሊኩል ሙዞፈር ሰጡት እሱም አንድ ሺህ ዲናር ሰጣቸው.........አልመሊኩል ሙዞፈር መልካም፣የሚተናነስ፣የሚወደስ ፈቂሆችን እና ሙሐዲሶችን የሚወድ ጥሩ ሰው ነበር”ይላል።

#ኢብኑ_ከሲር እስኪ ምን አለ? ኢብኑ ከሲር የኢብኑተይሚያ ተማሪና ወዳጅ ነው
አልቢዳየህ ወኒሃየህ በተባለ ኪታቡ 13ኛው ሙጀለድ ከገፅ 136 እሰከ 137 እንዲህ ይላል" የኢርቢል መሪ አልመሊኩል ሙዞፈር አቡ ሰዒድ ኩውከብሪይ ኢብኑ ዘይኒዲን ዐሊይ ሲሆን ከታላላቅ ፣ቸር እና የተከበሩ መሪዎች ውስጥ አንዱ ነው መልካም የሆኑ ነገራቶች ነበሩት እሱ ነው አል ጃሚዑ አል ሙዞፈሪይ የሚባለውን መስጊድ የገነባው........በረቢዑኒል አወል መውሊድን ያወጣ ነበር በሚገርም ሁኔታ ዝግጅትን ያዘጋጅ ነበር እሱ ጀግና ደፋር አቅለኛ ዓሊም ፍትሃዊ መሪ ነበር አሏህ ይዘንለት መኖሪያውንም ያማረ ያርገው........ አሸይኽ አቡል ኸጧብ ኢብኑ ዱህያ አንድ ሙጀለድ ኪታብ ስለመውሊድ በመጻፍ እና ስሙንም“አተንዊር ፊመውሊዲ አልበሺሪ አንነዚር” ሰይመው ለእሱ ሰጡት እሱም አንድ ሺህ ዲናር ሰጣቸው........ በ630 ሂጅራ አካባቢ ድረስ ማለትም እስከ ህልፈተ ሂወቱ ድረስ በስልጣን ላይ የቆየ ሲሆን በስልጣኑም ሆነ በስነምግባሩ ምስጉን ነበር”::ተመልከቱ እንግዲህ ወዳጃቸው ኢብኑ ከሲር እንዴት አመሊኩል ሙዞፈርን እያወደሰ እንደተናገረ።

#የኢብኑል_ጀውዚይ የልጅ ልጅ እንዲህ ይላሉ“ከአል ሙዞፈር መውሊድ ላይ የተገኙ እንዳሉት አምስት ሺህ ያህል በጎች፣አስር ሺህ ያህል ዶሮዎች፣በመቶዎች የሚቆጠሩ ፈረሶች፣መቶ ሺህ የሚሆን ቅቤ በእቃ ሆኖ፣ሰላሳ ሺህ ጣፋጭ ምግቦች በሳህን ሆነው ይቀርቡ ነበር.......ከመውሊዱ ላይ ታላላቅ ሱፊዮች፣ ሙሁሮች ይሳተፋሉ.....ከሱፊዮች ጋርም አብሯቸው በሃድራ ይወዛወዝ ነበር......በየአመቱ ለመውሊድ ሶስት መቶ ሺህ ዲናርን ያወጣል......ሚስቱ ራቢዐህ የሶላሁዲን አል አዩቢይ እህት እንዲህ ብላለች“የሚለብሰው ልብስ ሸካራና ዋጋው አምስት ዲናር የማይሞላ ልብስ ነበር”አንድ ጊዜ ላይ በዚህ ጉዳይ ላይ ስትወቅሰው እንዲህ አላት“እኔ የአምስት ዲናር ልብስ ለብሼ ሌላውን ሶደቃ ባወጣበት ይሻለኛል እኔ ውድ ልብስ ለብሼ ድሆችና ሚስኪኖችን ከምተዋቸው”አላት”ይላሉ።ተመልከቱ ምን አይነት ሰው እንደነበር....

አል ኢማሙ አሰኻዊይ እንዲህ ይላሉ“የመውሊድ ስራ የተጀመረው ከሶስቱ ክፍለ ዘመን በኋላ ነው ከዛ በኋላ ሙስሊሞች ከሁሉም አቅጣጫ በየትላልቅ አገሮች በመውሊድ መሰባሰባቸውን አላቆሙም በለይሎቹ የተለያዩ ሶደቃን ያወጣሉ፣የሰይዳችንን ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ታሪክ ያነባሉ.....በእነሱም ላይ የመውሊዱ በረካ በግልጽ ይታያል”አሉ::

ከመውሊዱ በረካ የምናገኝ አሏህ ያድርገን!

@Medinatube
10
#ያኢማመል ሀረም|| ማህፉዝ አብዱ
MEDINA TUBE
ያኢማመል ሀረም ሰላማለይኩሙ || ማህፉዝ አብዱ
@MEDINA_TUBE
@medinatube
3
ፈጥነው ይዘዙ ! በተለያዩ ዲዛይንና ከለር እንዳማራጫ ተሰርተው እርሶን የሚጠበሸቁ የመውሊድ ሂጃብና ቲሸርቶችን አዘጋጅተን እርሶን በመጠበቅ ላይ ነን ባሉበት ሆነው ባዘዙበት ጊዜ በፍጥነትና በጥራት አሰናቀርባለን! በተጨማሪ አረንጓዴ ሻል ይዘን ቀርበናል ይዘዙን!

ለማዘዝ 0938953867 ቴሌግራም @alifhitemat
ግሩፕአችን https://www.group-telegram.com/alifadvert
27 አመታት ማህበረሰብን በማገልገል ላይ

የነብያቸን ﷺ ማዲድህ የኑር መስጂድ ኢማም እና ኻጢብ ሸይኽ ሰኢድ አህመድ የመኪና ስጦታ ተበረከተላቸው ።

የመውሊድን መቃረብ በማስመልከት በተዘጋጀው ፕሮግራም በመስጂዳችን ኑር መስጂድ በ ኢማምነት በዳዕዋ ለዘመናት ለሰጡት አገልግሎት የ ኑር መስጂድ ወጣት ጀመዐ እና የኑር መስጂድ ኮሚቴ ከ አህለል ኸይሮች ጋር በመተባበር ባዘጋጀው የምስጋና እና የ እውቅና ፕሮግራም ላይ የመኪና ስጦታ ተበርክቶላቸዋል ።

ስጦታውን ከ ክቡር ዶ/ር ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጅ ኡመር እድሪስ እና ከሸይኽ ሙሀመድ ሰብዬ እጅ ተቀብለዋል ።
@medinatube
12
እንደ #ነቢﷺ ያለ አልተወለደም!! አይወለድም!!

ولم يولد كمثله
أحد من خلق الله
#MEDINA_TUBE
@medinatube
6
2025/08/23 16:37:19
Back to Top
HTML Embed Code: