የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን አመራሮችና ሰራተኞች የብልፅግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ በቀጣይ ለመስራት ባስቀመጣቸው አቅጣጫዎች መሰረት መንግስት በትኩረት በሚሰራቸው ስራዎች ዙሪያ ላይ ውይይት አደረጉ።
የካቲት 17/2017:- መንግስት ከፖለቲካ፣ ከሰላም፣ ከልማትና ከዴሞክራሲ ጋር በተያያዘ ቀጣይ ሊሰራቸው ባሰባቸው እቅዶቹ ዙሪያ ከመንግስት ሰራተኛው ጋር ለመወያየት በተጠራው የውይይት መድረክ ላይ የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ሔራን ገርባ እንደተናገሩት መንግስት የጀመራቸውን መጠነ ሰፊ የልማት፣ የሰላምና የዴሞክራሲ ስራዎች ለማስቀጠል የመንግስት ሰራተኛው እንደአስፈፃሚ አካልና እንደዜጋ ትልቅ ኃላፊነት እንዳለበት ገልፀው ባለስልጣኑ በቀጣዩ 6 ወራት ሊያሳካው ያሰበውን የአለም ጤና ደርጅት ማቹሪቲ ሌቭል 3 ጋር በተያያዘ የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥሉ ዘንድ የአደራ መልዕክት በማስተላለፍ ከስራ ሰዓት ውጪ ሌሊት ጭምር ስራዎችን እየሰሩ የሚገኙትን ሰራተኞች አመስግነዋል።
ከሁለተኛው የብልፅግና ጉባኤ ላይ የተቀመጡ የመንግስት አቅጣጫዎችን ለሰራተኛው ያቀረቡት የባለስልጣኑ የምግብ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ነጋሽ ስሜ በበኩላቸው ሁሉም ዜጋ በብሄራዊነት ገዢ ትርክት መንፈስ ለሀገር ሰላም፣ ልማትና እድገት የመንግስት ሰራተኛው ላቅ ያለ ሚና እንዳለው በመግለፅ በመንግስት የተዘጋጀውን የመወያያ ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን የቁጥጥር ዘርፉ ህዝቡን ጥራቱ ካልጠበቀ ምግብ፣ ሀሰተኛና ጥራት ከሌላቸው የጤና ግብዓቶች፣ ከትንባሆ፣ ከአልኮልና ተያያዥነት ካላቸው የጤና አደጋዎች በመጠበቅ የህዝብ አመኔታን መፍጠር እንደለበት ተናግረዋል።
በቀረበው ሰነድ ላይ የባለስልጣኑ ሰራተኞች ውይይት ካደረጉ በኋላ በጋራ መግባባት ውይይቱ ተጠናቋል።

👍9
የምግብና ጤና ግብዓቶች ደህንነትና ጥራት ለማስጠበቅ የቅንጅታዊ ስራዎች የበለጠ በማጠናከር መስራት እንደሚያስፈልግ ተገለፀ፡፡
የካቲት 18 /2017 ዓ.ም በአዳማ ከተማ የምግብና የጤና ግብዓቶች ቁጥጥር ዘርፍ የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የዕቅድ አፈፃጸም ግምገማ መድረክ ሲጀመር የባለስልጣኑ የምግብ ቁጥጥር ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ነጋሽ ስሜ እንደተናገሩት ከጤና ዘርፍ ዋነኛ የሆነው የምግብና የጤና ግብዓቶች ዘርፍ የተጣለበትን ሕብረተሰቡን ከሕገወጥ ምርቶች የመከላከል ጤና የመጠበቅ ኃላፊነት ለመወጣት ተቆጣጣሪ አካላት ከባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ በቅንጅት ተናቦ መስራት ምርጫ ሳይሆን ግዴታ ነው ብለዋል፡፡
ምግብና የጤና ግብዓቶች ሕገወጥ ዝውውር በሰዎች ጤና ላይ ከባድ ጉዳቶችን በማስከተል ለሕመም ብሎም ለሞቶ እንደሚዳርጉ በመግለጽ ፤ የምግብና የጤና ግብዓት ዘርፍ ቁጥጥር በማድረግ ሕገወጥ ተግባሩን ለመግታት ታቅዶና አፈፃጸሙ በየጊዜው እየተገመገመ መሄዱ ጥሩ ስራዎች እየተሰሩ ቢሆንም እነዚህ ተግባራት የበለጠ ተጠናክረው መቀጠል አለባቸው ብለዋል፡፡
እየተካሄደ ያለው የዕቅድ አፈፃጸም ግምገማ መድረክ የግማሽ በጀት ዓመት በመሆኑ ጠንካራ ስራዎችን በማስቀጠል በዝቅተኛ ደረጃ የሚታዩ አፈፃጸሞችን በቀጣይ ስድስት ወራት የበለጠ አሻሽሎ ለመፈፀም ዕድል የሚፈጥር በመሆኑ ርብርብ ሊደረግ ይገባል ነው ያሉት፡፡
የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ መድረኩ ዛሬን ጨምሮ በነገው ዕለት የሚቀጥል ሲሆን የባለስልጣኑ መሪ ስራ አስፈፃሚዎች፣የቅርንጫፍ ፅ/ቤት ኃላፊዎች፣ የክልል ጤናና ጤና ነክ ተቆጣጣሪ አካላት ኃላፊዎች እንዲሁም የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ተወካዮች እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡

👍6