group-telegram.com/islam1670/397
Last Update:
╔═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╗
....... #በርሲሳ ......
╚═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╝
┎━─━─━─━─━─━─━─━┒
በ𝐖𝐎𝐑𝐋𝐃 𝐈𝐒𝐋𝐀𝐌 𝐂𝐇𝐀𝐍𝐍𝐀𝐋 የተዘጋጀ
┖━─━─━─━─━─━─━─━┚
╔═══•| ✿ |•═══╗
#ክፍል_ሶስት
╚═══•| ✿ |•═══╝
በርሲሳ በተደጋጋሚ ማይፈቀድለትን እያየ ልቡ ላይ ፍላጎት መጣበት። ከገነቡ በኋላ ከማፍረስ አላህ ይጠብቀን። በመጨረሻም ከሷ ጋር ዝሙት ፈፀመ። አንዴም ብቻ አደለም ያደረገው ደጋገመ። አንዴ ወንጀልን ከቀመሱት መውጣት ከባድ ነው!! ከዛ እንደሚታወቀው ከዝሙት በኋላ እርግዛ መጣ። ልጂቷ አረገዘች። ይሄ ክፉውና ተንኮለኛው ሸይጧን ይህን ጊዜ የልጂቷ እርግዝና ከታወቀ ቦሃላ ወደ በርሲሳ መጣ። ማንኛውም ሰው ሰሃባ ይሁን አሊም ማንኛውም ሰው ቢሆን በዚ ሊፈተን ይችላል። የሴት ፈተና ከባድ ነው። ለዛ ነው ነብያችን አንድ ወንድ ከሴት ጋር አይነጠልም ሶስተኛቸው ሸይጧን ቢሆኝ እንጂ ያሉት። ይሀው እዚ ጋር ሶስተኛቸው ሸይጧን ሆነ።
ከዛም ሸይጧኑ ይመጣና ለበርሲሳ
" በርሲሳ ሆይ!! ጉድህ ፈላ! ተዋረድክ! እሷን ገድለሀት ተውበት ብታደርግ ምን ይመስልሀል።" አሁንም ሌላ ወንጀል ሊያሰራው። "ቤተሰቦቿ ከጠየኩህ።' ያ ያሳመማት ሸይጧን አሳመማት እና አልቻልኩምና ይዟት ሄደ' በላቸው"እስካሁን ዝሙት ሰርቷል አሁን ደግሞ ሰውን ሊያስገድለውና ሊዬስዋሸው ነው። እሱም የሱን ትእዛዝ ተቀብሎ ገደላት። ከዛ ወስዶ ጋራ ስር ቀበራት። ሸይጧን ይህኔ የተንኮል መረቡን አሰፋ።
የሷ ወንድሞች ጋር በህልም ተመስሎ ሄዶ ለታላቅየው " እህታችሁን በርሲሳ ገድሏታል" አላቸው። በሌላ በኩል በርሲሳ ስራውን ጨርሶ የለመዳትን ኸይር ስራ አላቆመም። እሷን ገድሎ ቀብሮ ተመልሰና ሰላት እየሰገደ ነው። ታላቅየው በርሲሳ እንደዚ አደረገ ብሎ አሳለፈ በርሲሳ እንዲ ያደርጋል ብሎ አላሰበም። ኸደ መካከለኛው ሄዶ በህልሙ ታየውና ይሄም እንደታላቁ በርሲሳ እንዲ አያደርግም አለ። ታናሻቸው ጋርም መጥቶ በህልም ነገረው። እህታቹን ደፍሯታል ከዛም ገድሏት ጋራ ስር ቀብሯታል ብሎ ነገራቸው። በፍፁም ሊያምኑ አልቻሉም ይሄ የሸይጧን ቅዠትና ተንኮል ነው አሉ። መጨረሻ ላይ "ካላመናቹን ሂዱ እርሱ ያለበት ስፍራና ልብሷ ጫፉ ከውጭ ይታያል። ሂዱ አረጋግጡ" አላቸው
ልክ ስፍራው ሲሄዱ የእውነቱን እንደነገራቸው አወቁና ወዲያውኑ ተመለሱና ሰራዊቶቻቸውን አገልጋያቸውን የኢባዳ ጎጆውን አፈረሱት። ከዛም እሱን አውጥተው አስረው ንጉሱ ጋር ወሰዱት። አድርገሀል ተብሎ በተጠየቀም ጊዜ አሁንም የተወሰነ የአላህ ፍራቻ ስላለው አልሸመጠጠም አመነ። ይሄን ጊዜ ሸይጧን ይመጣና "ያጠፋሀው ጥፋት ሁሉ ሳይበቃህ መጨረሻ ላይ ደሞ ገድያለሁ ትላለህ እንዴ?! ቢያንስ ቢያንስ እኔ አላደረኩም አትልም!!!" አለው።
መጨረሻ ላይ ንጉሱ እንዲገደል ውሳኔ ያቀርባል። ተሰቅሎ እንዲገደል አዘዘ። እንደገና ይሄን ጊዜ ሸይጣኑ መጥቶ "በርሲሳ ሆይ ታውቀኛለህ እንዴ!?"
"አይ አላውቅህም" አለው
"እኔ ያኔ እነዚያ መፈወሻ ዱዐዎችን ያስተማርኩህ ሰው ነኝ። ምን ሆነው አማናህን አልጠበቅክም? አላህን አልፈራህም? ቤተሰቦቿንም ካድክ!! 'ከኢስራኤል ልጆች ሁሉ ይበልጥ አሏህን ፈሪ ነኝ' ትል ነበረ፡፡" እያለ እየወቀሰው ያሸማቀዋል።
መጨረሻ "በዚ ወንጀል ተይዘህ የተገደልክ እንደሆነ ባንተ አምሳያ የሚታወቁ ሰዎችን በሙሉ ስም ማጥፋትህ ነው" አሁንም ተመልሶ መካሪ መሰለ። ለኢባዳ ሰዎች ተቆርቋሪ እየመሰለ ነው። "ስለዚህ አንድ ነገር እነግርሀለው እሱን ካደረግክ የሰቀሉህ ሰዎች ሳያዩህ አይናቸው ተጋርዶ ከዚ ይዠህ እጠፋለው" አለው።
"እሺ ንግረኝ ምንድነው ምትነግረኝ" ይለዋል። ይሄን ጊዜ ሸይጧኑ
"ለኔ ብቻ ስገድልኝ አድንሀለው" ይለዋል። ይሄን ጊዜ ያልጠበቀው መልስ ይገጥመዋል በርሲሳ ግን እኔ ይሄን አላደርግም ይለዋል። ሸይጣኑም ይሄኔ....
...... የመጨረሻ ክፍል ይቀጥላል ......