Telegram Group & Telegram Channel
በምዕራብ ዕዝ ቴዎድሮስ ኮር 4ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ላይ ለመታደም ሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን ሻምቡ ከተማ የገቡት የጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል አበባው ታደሠ በበዓሉ ላይ በክብር እንግድነት ተገኝተው ባደረጉት ንግግር እኛ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የቁርጥ ቀን ልጆች እያለን ኢትዮጵያን መበተን አይቻልም፤ አይታሠብምም ብለዋል።

በውጭ ያሉ ጠላቶቻችን እና ውስጥ ያሉ ጠላቶቻችን ተሰባስበው እንመጣለን እያሉ ሲመክሩና ሲፎክሩ ይሰማል። እኛም የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ከመላ ህዝባችን ጋር ሆነን ምን ሊያደርጉ እንደሚመጡ ስለምናስብና ስለምናውቅ ተዘጋጅተን እንጠብቃቸዋለን፤ ያኔ የተለመደውን ዋጋ ከፍለን ኢትዮጵያን ካሰቡላት ጥፋት እንደ ትናንቱ እንታደጋለን ብለዋል።

በህጋዊ መንገድ በህዝብ የተመረጠ መንግስትን ህገ ወጥ በሆነ መንገድ በአፈሙዝ ለማስወገድ የሚደረግ ማናቸውም ሙከራ ጀግናው ሠራዊታችን እያለ አይሳካም ያሉት ጄኔራል አበባው ታደሠ ለህዝብ የሚጠቅም አማራጭ ሃሳብ ያለው ማንኛውም አካል ህጋዊ እና ሠላማዊ መንገዶችን ተጠቅሞ ምኞቱን ለማሳካት መስራት እንደሚችል እና የዘመኑ ብቸኛ አማራጭም ይህ ብቻ እንደሆነ አስገንዝበዋል።

ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹሙ በዕለቱ ባደረጉት ንግግር 4ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን ያከበረው የ401ኛ ቴዎድሮስ ኮር በተለያዩ የሃገራችን ክፍሎች የተሠጠውን ወታደራዊ ግዳጅ እንደሌሎች የጦር ክፍሎች በድል መጨረስ የቻለ መቺ የጦር ክፍል መሆኑን ተናግረዋል።

ቴዎድሮስ ኮር በሠሜኑ ህግ የማስከበር ተልዕኮ ግዳጁን በላቀ ውጤት ከፈፀመ በኋላም አሁን ተሰማርቶበት በሚገኘው የሆሩ ጉድሩ ወለጋ ዞን፤ አሸባሪውን የሸኔን ቡድን በመምታት እና ተገዱ ወደ ሰላም እንዲገባ በማድረግ ለአካባቢው ህዝብ አንፆራዊ ሰላም ማስፈን የቻለ ኮር ነው በማለት የኮሩን የላቀ ግዳጅ አፈፆፀም ገልፀውታል።

ጄኔራል አበባው ታደሠ በመጨረሻም የሆሮጉድሩ ወለጋ ዞን ህዝብና አስተዳደር በአሸባሪው ሸኔ የነበረበትን ከባድ ጫና ተቋቁሞ ከሠራዊታችን ጋር በፅናት በመቆም ላሳየው ቁርጠኝነትና ለከፈለው መስዋዕትነት ሁሉ በመከላከያ ሠራዊት ስም ከፍ ያለ ምስጋና አቅርበዋል።

በዕለቱም ጄነራል አበባው ታደሠ እና ጄኔራል ጌታቸው ጉዲና የሆሮጉድሩ ወለጋ ዞን አባገዳዎች እና ሃደስንቄዎች ፤ የሃገር ሽማግሌዎች እና ወጣቶች የተበረከተላቸውን የፈረስ ፤ ጋሻና ጦር ስጦታ ከዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ምሬሳ ፊጤ እና ከአባገዳዎች እጅ ተቀብለዋል።

group-telegram.com/NatnaelMekonnen21/45662
Create:
Last Update:

BY Natnael Mekonnen

Share with your friend now:
group-telegram.com/NatnaelMekonnen21/45662

View MORE
Open in Telegram

Telegram | DID YOU KNOW?

Date: |

Telegram has become more interventionist over time, and has steadily increased its efforts to shut down these accounts. But this has also meant that the company has also engaged with lawmakers more generally, although it maintains that it doesn’t do so willingly. For instance, in September 2021, Telegram reportedly blocked a chat bot in support of (Putin critic) Alexei Navalny during Russia’s most recent parliamentary elections. Pavel Durov was quoted at the time saying that the company was obliged to follow a “legitimate” law of the land. He added that as Apple and Google both follow the law, to violate it would give both platforms a reason to boot the messenger from its stores. "The result is on this photo: fiery 'greetings' to the invaders," the Security Service of Ukraine wrote alongside a photo showing several military vehicles among plumes of black smoke. Lastly, the web previews of t.me links have been given a new look, adding chat backgrounds and design elements from the fully-features Telegram Web client. On Telegram’s website, it says that Pavel Durov “supports Telegram financially and ideologically while Nikolai (Duvov)’s input is technological.” Currently, the Telegram team is based in Dubai, having moved around from Berlin, London and Singapore after departing Russia. Meanwhile, the company which owns Telegram is registered in the British Virgin Islands.
from ms

Telegram Natnael Mekonnen
FROM American