በኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን የተጀመሩ የበጎ አድራጎት ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተገለፀ
ሐምሌ 29 ቀን 2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን የማኔጅመንት አባላት እና የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ስራ አስፈፃሚ እና አመራሮች በተገኙበት የመኖሪያ ቤት እድሳት የማስጀመሪያ ፕሮግራም ተካሄዷል፡፡ በማስጀመሪያ ፕሮግራሙ ላይ የባለስልጣኑ የምግብ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ነጋሽ ስሜ እንደተናገሩት ባለፉት 7 አመታት እየተሰሩ ያሉት የበጎ አድራጎት ስራዎች አጠቃላይ የማህበረሰብ የፖሊሲ አቅጣጫዎች አንዱ አካል በሆነው እራስን በራስ የመቻል እንቅስቃሴዎ ውስጥ እንደሚካተት ገልፀው ባለስልጣኑ ከሌሎች በበጎ አድራጎት ስራዎች ላይ ከተሰማሩ አካላቶች ጋር በመሆን በዛሬው እለት የ3 አባወራ መኖሪያ ቤቶችን የማደስ ስራ በይፋ ያስጀመሩ ሲሆን በቀጣይም ይህ ተግባር ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በተመሳሳይም የቂርቆስ ወረዳ 2 ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ወይዘሮ ብሩክታዊት ምትኩ ለወረዳው ነዋሪዎች ለተደረገው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበው በቀጣይም በሚከናወኑ የበጎ አድራጎት ስራዎች ወረዳው ከባለስልጣኑ ጋር ለመተባበር ዝግጁ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

👍5👎1
የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን የ2017 በጀት አመት የክረምት የበጎ ፈቃድ ተግባር እቅድ የሆነው የመማሪያ ቁሳቁሶች ከአመራሩና ከሰራተኛው በማሰባሰብ አስረከበ፡፡
ነሀሴ 3/2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን አመራሮችና ሰራተኞች የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተግባራት ጋር ተያይዞ የጤና ሚኒስቴር በስሩ ከሚገኙ ተጠሪ ተቋማት በማሳተፍ እየሰራ ለሚገኘው የክረምት የበጎ አድራጎት ስራ አካል የሆነውን የተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ የማሰባሰብ ስራን በማጠናቀቅ አስረክቧል፡፡
ከባለስልጣን መስሪያ ቤቱ አመራረሮችና ሰራተኞች በተሰበሰበ የገንዘብ ድጋፍ አነስተኛ ገቢ ላላቸው ተማሪዎች የሚሆኑ 360 ደርዘን ደብተር፣600 እስኪርቢቶ እና 600 እስራሶችን በአጠቃላይ ግምታቸው 277,200ብር የሚያወጣ ሲሆን በዛሬው ዕለት የባለሰልጣን መ/ቤቱ የበጎ አድራጎት ኮሚቴ አባል ወ/ሮ ውብናት ቢራራ የመማሪያ ቁሳቁሱን አስረክበዋል::

👍3
ነሐሴ 8/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ፡ የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ሄራን ገርባ የባለስልጣኑን የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀምን አስመልክተው ለመንግስትና ለግል መገናኛ ብዙኃን ጋዜጣዊ መግለጫ በሰጡበት ወቅት እንደተናገሩት በ2017 በጀት የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ሰፊ የሪፎርም ስራዎችን በመስረት የተያዙ የልማት ዕቅዶች እንዲሳኩ ሲሰራ መቆየቱን አውስተው በዚህም በአብዛኛዎቹ መልካም አፈፃጸሞች ታይተዋል፡፡
የምግብን ጥራትና ደህንነት ቁጥጥርን ከማጠናከር አንፃር አስፈላጊውን መስፈርቶች ላሟሉ 4186 ምግብ አይነቶች ምዝገባ በማካሄድ የገበያ ፈቃድ የተሰጠ ሲሆን ከ2016 ዓ.ም ጋር አንጻር ሲነፃፀር በ26.2 ፐርሰንት መጨመሩን የጠቆሙት ዋና ዳይሬክተሯ መስፈርቱን ላሟሉ አዲስ የምግብ ተቋማት ለ128 አምራች እና ለ1354 የምግብ ላኪ፣ አስመጪና አከፋፋይ ተቋማት የብቃት ማረጋገጫ መስጠት ተችሏል፡፡ ይህም ከአምናው አንጻር ሲታይ በ6 ፐርሰንትና በ42 ፐርሰንት ጨምሯል ነው ያሉት፡፡
በሌላ በኩል በዚሁ በጀት ዓመት ለ746 አዳዲስ መድኃኒቶች የገበያ ፍቃድ መሰጠቱንና የመድኃኒት ጥራትን ለመቆጣጠር የቅድመ ፈቃድ ኢንስፔክሽን በማካሄድ ለ591 አስመጪና አከፋፋይ ተቋማት እና ለ51 ጥቃቅንና አነስተኛ አምራች ድርጅቶች የብቃት ማረጋገጫ መሰጠት መቻሉን ዋና ዳይሬክተሯ አብራርተው ይህም ከቀዳሚው ዓመት ጋር ሲነፃጸር ከ24 እስከ 45 በመቶ እድገት አሳይቷል ብለዋል፡፡
የህክምና መሳሪያዎችን ጥራትና ደህንነት ከመቆጣጠር አንፃር ለ927 የህክምና መሳሪያዎችን በበጀት ዓመቱ የገበያ ፈቃድ መሰጠቱን ያአስረዱት ዋና ዳይሬክተሯ 39.8 ዕድገት ማስመዝገቡን ጠቁመው ከ40 በሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው የህክምና መሣሪያዎችና መገልገያዎች ላይ አስፈላጊዉን የጥራት ቁጥጥር በማድረግ የመልቀቂያ ፍቃድ መስጠት ተችሏል፡፡

👍10
የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን አማካሪ ቦርድ ትኩረት በሚሹና ስትራቴጂካዊ በሆኑ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አካሄደ፡፡
ነሐሴ 9/2017 ዓ/ም አዲስ አበባ፡ የኢትዮጵያ ምግብ እና መድኃኒት ባለሥልጣን አደረጃጀት፣ ሥልጣንና ተግባር መወሰኛ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 531/2015 መሠረት የተቋቋመው አማካሪ ቦርድ በዛሬው ዕለት ስብሰባውን አካሂዷል፡፡
የባለስልጣን መስሪያ ቤቱን አፈፃፀም በመገምገም ትኩረት በሚሹና ስትራቴጂካዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ምክረ ሀሳብ በመስጠት ተቋሙን ለማጠናከርና ለማሳደግ ታስቦ የተቋቋመው አማካሪ ቦርዱ የሚመራበትን መመሪያ ላይ ሰፊ ውይይት አድርጎ አፅድቋል፡፡
የአማካሪ ቦርድ በቋሚነት በየሦስት ወሩ የሚሰበሰብ መሆኑና የቦርዱ አባላትም ከጤና ሚኒስቴር፣ ከንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር፣ ከፍትህ ሚኒስቴር፣ ከትምህርት ሚኒስቴር፣ ከኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን፣ ከኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት፣ ከኢትዮጵያ ፖሊስ ኮሚሽን፣ ከአርማወር ሃንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት፣ ከኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን፣ ከኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ባለስልጣን እና ከኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን የተወጣጡ 11 ከፍተኛ የመንግስት ኃላፊዎችን በአባልነት የያዘ መሆኑ ታውቋል፡፡
በስብሰባው ላይ የ2017 በጀት ዓመት የእቅድ አፈፃጸም እና የ2018 በጀት ዓመት እቅድ እንዲሁም ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የዓለም ጤና ድርጅት የተቋማት የዕድገት ደረጃ ሶስት (Maturity Level 3) ለመድረስ ያለበት ደረጃ እና እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ቀርበው ውይይት ተካሂዶባቸዋል፡፡

👍12