This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
መሬት ንቅት ሽርትት
እንደ ዘንድሮ ሰው
ደሞም ቅጥቅጥ ቅጥቅጥ
እንዳንዘረዘረው
ከመንቃት ተኗቁሮ
ደም የማይጠግብ ወለል
ጸሊም እንደ ሬንጁ
የሰው ልብን መሰል
ሁሌ ሚሞትለት
ደሞ ‘ሚሞትበት
የግዢ፣ የሊዙ
የኪራይ፣ የዳሱ
የመንግስት፣ ያራሹ
ማለፊያ፣ ግንባሩ
ኮሪዶር፣ ቡርቧሩ
የፓርኩው፣ የጫካው
የአዝመራ፣ የአሸዋው
የበረዶ ጭቃ
የአማልክቱ እቃቃ. . .
ጨረቃን ማያ
ምርጥ view
ሸከርካሪት፣ ዟሪት፣
ደሞም ተንሸራታቺት
አንቺው
ከአፈር እስከ አፈር እያዘገመ
ሰው ካንቺ ይህን ቀሰመ።
ከአፈር እስከ አፈር እያዘገመ
. . .
ሁሌ የውስጡ ሲደላደል
ይበጋል፤ ይረጋል ገል
ሲፈትን ግን ሲተናነቅ
ንዝረት ነው ገሞራ አመቅ
እንግዲህ ሀቅ ነው ምድር ያለ ፍራጅ
በል ሆዴ ቁረጠው እምነቴን በምላጭ
መሬትም ይሸሻል እንኳን የሰው ውላጅ
መሬትም ይጠጣል ይህን የሰው እራጅ
ተው ልቤ ረጋ በል፣
ተው ልቤ መሬት ሁን
ስለው የነበረ
እርሙን ሰማኝና
ተንሸራቶ አደረ
AW Credit: Hearts collection NFT by @egamberdiev.sh #seifetemam #poetryslam #poetry #ሰይፈተማም #ግጥም #ግጥምለምትወዱ
እንደ ዘንድሮ ሰው
ደሞም ቅጥቅጥ ቅጥቅጥ
እንዳንዘረዘረው
ከመንቃት ተኗቁሮ
ደም የማይጠግብ ወለል
ጸሊም እንደ ሬንጁ
የሰው ልብን መሰል
ሁሌ ሚሞትለት
ደሞ ‘ሚሞትበት
የግዢ፣ የሊዙ
የኪራይ፣ የዳሱ
የመንግስት፣ ያራሹ
ማለፊያ፣ ግንባሩ
ኮሪዶር፣ ቡርቧሩ
የፓርኩው፣ የጫካው
የአዝመራ፣ የአሸዋው
የበረዶ ጭቃ
የአማልክቱ እቃቃ. . .
ጨረቃን ማያ
ምርጥ view
ሸከርካሪት፣ ዟሪት፣
ደሞም ተንሸራታቺት
አንቺው
ከአፈር እስከ አፈር እያዘገመ
ሰው ካንቺ ይህን ቀሰመ።
ከአፈር እስከ አፈር እያዘገመ
. . .
ሁሌ የውስጡ ሲደላደል
ይበጋል፤ ይረጋል ገል
ሲፈትን ግን ሲተናነቅ
ንዝረት ነው ገሞራ አመቅ
እንግዲህ ሀቅ ነው ምድር ያለ ፍራጅ
በል ሆዴ ቁረጠው እምነቴን በምላጭ
መሬትም ይሸሻል እንኳን የሰው ውላጅ
መሬትም ይጠጣል ይህን የሰው እራጅ
ተው ልቤ ረጋ በል፣
ተው ልቤ መሬት ሁን
ስለው የነበረ
እርሙን ሰማኝና
ተንሸራቶ አደረ
AW Credit: Hearts collection NFT by @egamberdiev.sh #seifetemam #poetryslam #poetry #ሰይፈተማም #ግጥም #ግጥምለምትወዱ
Black History Month Extended
catch me live on Arada FM 95.1 along side the one and only Debbie Alamrew and Andre Amadi Saturday Afternoon 12:00-2:00
በአራዳ ኤፍ ኤም 95.1 ላይ እንከሰታለን
ቅዳሜ ከሰዓት ከ6- 8 ሰዓት
የጥበብ ሞገድ የሬጌ ሾው
#blackhistroymonth #የጥበብሞገድ #ግጥም #radio #seifetemam #reggaeshow #DebbieAlamrew #Andre_Amadi
catch me live on Arada FM 95.1 along side the one and only Debbie Alamrew and Andre Amadi Saturday Afternoon 12:00-2:00
በአራዳ ኤፍ ኤም 95.1 ላይ እንከሰታለን
ቅዳሜ ከሰዓት ከ6- 8 ሰዓት
የጥበብ ሞገድ የሬጌ ሾው
#blackhistroymonth #የጥበብሞገድ #ግጥም #radio #seifetemam #reggaeshow #DebbieAlamrew #Andre_Amadi
አልፈቅድለትም!
ይኼን ገሞራ እንዲኼድ የትም
እንዲሰነጠር እንዲላተምም
እንዲገነፍል እንዲበለትም
አልፈቅድለትም!
በዚህ ሁሉ ጣር
ሰው በሚሉት ጣር
ልብ እንዲታጠር
የንጹኃን ቃል
እንዲብጠለጠል
ከግጥሜ አንድ ቃል
እንዲገነጠል
ከልሳኔ እኩይ እንዲንቀለቀል
ከልቤ ዜማ እንዲገነጠል
በየቅያሱ ስሜ እንዲቀለል
በነገር ነፍሮ ውስጤ እንዲቀቀል
...
እንዲጠረጠር እምነቴ ላፍታ
ባላወኩት ጦስ ህልሜ እንዲገታ
የህጻናት ሳቅ በአዋቂ ሆታ
እንዲሸፋፈን የሴት ልጅ ዋይታ
አልፈቅድለትም!
ይኼን ልዩ ቃል እንዲባል የትም
ሳይል እንዳይቀር ያላልኩትንም
እንዲዝረከረክ እንዳይሆን ግጥም
ከምንም ጋራ ባልገባ ምንም
. . . እንዳይፖሰት
አልፈቅድለትም
ይኼን ገሞራ እንዲኼድ የትም
#ሰይፈተማም #አልፈቅድለትም #WorldPoetryDay
ይኼን ገሞራ እንዲኼድ የትም
እንዲሰነጠር እንዲላተምም
እንዲገነፍል እንዲበለትም
አልፈቅድለትም!
በዚህ ሁሉ ጣር
ሰው በሚሉት ጣር
ልብ እንዲታጠር
የንጹኃን ቃል
እንዲብጠለጠል
ከግጥሜ አንድ ቃል
እንዲገነጠል
ከልሳኔ እኩይ እንዲንቀለቀል
ከልቤ ዜማ እንዲገነጠል
በየቅያሱ ስሜ እንዲቀለል
በነገር ነፍሮ ውስጤ እንዲቀቀል
...
እንዲጠረጠር እምነቴ ላፍታ
ባላወኩት ጦስ ህልሜ እንዲገታ
የህጻናት ሳቅ በአዋቂ ሆታ
እንዲሸፋፈን የሴት ልጅ ዋይታ
አልፈቅድለትም!
ይኼን ልዩ ቃል እንዲባል የትም
ሳይል እንዳይቀር ያላልኩትንም
እንዲዝረከረክ እንዳይሆን ግጥም
ከምንም ጋራ ባልገባ ምንም
. . . እንዳይፖሰት
አልፈቅድለትም
ይኼን ገሞራ እንዲኼድ የትም
#ሰይፈተማም #አልፈቅድለትም #WorldPoetryDay
ቀባጥሩ
‘ማይደረግ አ’ርጉ
የማይባል በሉ
ተኝቶ ነው ያለው
ፍጥረቱ በሙሉ
በዕንቅልፍ ልብ ዓለም
እንደዚህ ነው ውሉ
እያዩ መጋደም
እየሰሙ መትፋት
ተቀምጦ መሮጥ
ዓይቶ አለመመልከት
ያልተወለደ ልጅ
እንደ ማጥባት አይነት
ያልተደፋ ዳቦ
እንደ መቁረስ አይነት
ባልጠባ መስከረም
እዮሃዬ አይነት
የታፈሰን ውሃ
እንደማፍሰስ አይነት
ይሳሳት ጀመረ እራሱ ልክነት!
ከተኛንበቱ ከዚ ዓለም መደብ ስር
የሚቀሰቅሰን በዓንዳች ተዓምር
እስኪደርስ ጊዜው
እስኪፈልቅ ጸበሉ
‘ማይደረግ አ’ርጉ
የማይባል በሉ
ቀ ባ ጥ ሩ!
2009
#ቀባጥሩ #SeifeTemam #poetry #poetrylovers #ሰይፈተማም #gitemsitem #ግጥምሲጥም #ግጥም #ግጥምለምትወዱ
‘ማይደረግ አ’ርጉ
የማይባል በሉ
ተኝቶ ነው ያለው
ፍጥረቱ በሙሉ
በዕንቅልፍ ልብ ዓለም
እንደዚህ ነው ውሉ
እያዩ መጋደም
እየሰሙ መትፋት
ተቀምጦ መሮጥ
ዓይቶ አለመመልከት
ያልተወለደ ልጅ
እንደ ማጥባት አይነት
ያልተደፋ ዳቦ
እንደ መቁረስ አይነት
ባልጠባ መስከረም
እዮሃዬ አይነት
የታፈሰን ውሃ
እንደማፍሰስ አይነት
ይሳሳት ጀመረ እራሱ ልክነት!
ከተኛንበቱ ከዚ ዓለም መደብ ስር
የሚቀሰቅሰን በዓንዳች ተዓምር
እስኪደርስ ጊዜው
እስኪፈልቅ ጸበሉ
‘ማይደረግ አ’ርጉ
የማይባል በሉ
ቀ ባ ጥ ሩ!
2009
#ቀባጥሩ #SeifeTemam #poetry #poetrylovers #ሰይፈተማም #gitemsitem #ግጥምሲጥም #ግጥም #ግጥምለምትወዱ
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የመሃል አገር ሰው
የዕድሜ ዕኩሌን ያህል
የለኝ በር ለባህር
ግን የሚታወሰኝ
ከየትኛው ዕድሜ እንጃ እንደተነነኝ
ባህር እያማታ ውሃን ከየብሱ ጋር
መርከቦች ሲጭኑ ሰውን እንደ ሰጋር
እንደ ባሪያ አድርገው
ሲቃ ስቅ እስኪለው
ሲያግዙ ሲያግዙ
ሲያግዙ ሲያግዙ
እንድም ሳያግዙ
ብረት እያስያዙ
ወረት እያናዙ
ቋንጃ ከፍንጅ አስረው
ሰው ባሪያ ባሪያ ሰው
ሰው ባሪያ ባሪያ ሰው
ሰው ባሪያ ባሪያ ሰው. . .
. . . እኔ አገሬ ነጣ
ሳይነጣ የነጣ
ኖሮት ኖኖት ያጣ
ግን በጊዜ ዱካ
ዘመንን ስድከው
ዛሬም እንደዚህ ነው
ሰው ሰው ሸጦ ከብሯል
'ሰውሰው' ሸቶ ከስሯል
ሰው፣ 'ሰው' ቃሉ ደቋል
ሰው ሰው ሰቅሎ ጸድቋል
. . .
በሰንሰለት ሆነ ስሞም ባሳለፈው
ከመኖርም ሆነ ከእኩይ የተረፈው
እውነትም መንገድም ሕይወትንም ሳለ
በ'የሱስ ዋጋ ነው ሁሉም የተሸጠ?
የዕድሜ ዕኩሌን ያህል
የለኝ በር ለባህር
ግን የሚታወሰኝ
ከየትኛው ዕድሜ እንጃ እንደተነነኝ
ባህር እያማታ ውሃን ከየብሱ ጋር
መርከቦች ሲጭኑ ሰውን እንደ ሰጋር
እንደ ባሪያ አድርገው
ሲቃ ስቅ እስኪለው
ሲያግዙ ሲያግዙ
ሲያግዙ ሲያግዙ
እንድም ሳያግዙ
ብረት እያስያዙ
ወረት እያናዙ
ቋንጃ ከፍንጅ አስረው
ሰው ባሪያ ባሪያ ሰው
ሰው ባሪያ ባሪያ ሰው
ሰው ባሪያ ባሪያ ሰው. . .
. . . እኔ አገሬ ነጣ
ሳይነጣ የነጣ
ኖሮት ኖኖት ያጣ
ግን በጊዜ ዱካ
ዘመንን ስድከው
ዛሬም እንደዚህ ነው
ሰው ሰው ሸጦ ከብሯል
'ሰውሰው' ሸቶ ከስሯል
ሰው፣ 'ሰው' ቃሉ ደቋል
ሰው ሰው ሰቅሎ ጸድቋል
. . .
በሰንሰለት ሆነ ስሞም ባሳለፈው
ከመኖርም ሆነ ከእኩይ የተረፈው
እውነትም መንገድም ሕይወትንም ሳለ
በ'የሱስ ዋጋ ነው ሁሉም የተሸጠ?
Unread
It’s like you read everything,
everything ever written
on the face of the earth,
the palm of each hand,
the lines of every vein,
all the lies in vain
it’s like you read everything.
Everything.
Not just my mind.
The drafts I never typed.
The thoughts I abandoned mid-sentence.
The made-up words I aborted.
You caught them
quiet, still warm
from the moment I left them.
You read both my inhale
and the breeze on my face.
It’s like you turn me page by page,
chapter after chapter,
tuck me under your pillow,
then hug me like a toddler.
You read me
like your most favorite series,
the way the sky looks down at Earth
until there’s nowhere else left to see.
Reading the publisher’s phone number
as if you’re about to publish
a whole story of me.
It’s like you read me
whenever you see me turning.
You scan my pages
to the unwritten poems
waiting for an activator to exist.
It’s not just me.
You read everything
every single stroke,
every beat, every note,
every unsilenced inbetween,
every unreleased release,
every sign, every squeeze,
every braille I might produce
fearing your love might blind me.
You read
everything
and everything.
But not
this.
@SeifeTemam
#gitemsitem #poetry #poetrylovers✒️ #poetryindustry #ግጥም #ግጥምለምትወዱ #ግጥምሲጥም
It’s like you read everything,
everything ever written
on the face of the earth,
the palm of each hand,
the lines of every vein,
all the lies in vain
it’s like you read everything.
Everything.
Not just my mind.
The drafts I never typed.
The thoughts I abandoned mid-sentence.
The made-up words I aborted.
You caught them
quiet, still warm
from the moment I left them.
You read both my inhale
and the breeze on my face.
It’s like you turn me page by page,
chapter after chapter,
tuck me under your pillow,
then hug me like a toddler.
You read me
like your most favorite series,
the way the sky looks down at Earth
until there’s nowhere else left to see.
Reading the publisher’s phone number
as if you’re about to publish
a whole story of me.
It’s like you read me
whenever you see me turning.
You scan my pages
to the unwritten poems
waiting for an activator to exist.
It’s not just me.
You read everything
every single stroke,
every beat, every note,
every unsilenced inbetween,
every unreleased release,
every sign, every squeeze,
every braille I might produce
fearing your love might blind me.
You read
everything
and everything.
But not
this.
@SeifeTemam
#gitemsitem #poetry #poetrylovers✒️ #poetryindustry #ግጥም #ግጥምለምትወዱ #ግጥምሲጥም
የሚያበቃበት ቀን:- ሚያዝያ 30 ምን ላይ? 👇🏾 በፌስቡክ፣ ኢንስታግራም እና ቲክቶክ ገጻችንን ታግ በማድረግ ለመወዳደር 👉🏾ከ21 ዓመት በላይ መሆን፣ የታደሰ ፓስፖርት እንዲሁም የመወዳደሪያው ግጥም ከተጻፈበት ቋንቋ ወደ አማርኛ፣ እንግሊዝኛ እና ፈረንሳይኛ ተተርጉሞ መቅረብ ይኖርበታል! በግጥማችሁ አብረን ታሪክ እንስራ! #Ethiopia_National_Slam_Championship #CASP #slampoetry #ethiopia #GitemSitem #poetry #poetrylovers #ግጥም #ግጥምለምትወዱ #ግጥም_ሲጥም #ግጥምሲጥም #poeticsaturdays