" ማንም ባለሙያ ቢሆን እንዲገደል አይገባውም፤ በተለይ ትዕዛዝ መስጠት የማይችሉ ዳኞች ባለሙያዎችም ሲሆኑ እጅግ ያሳዝናል " - የሟች የቀድሞ ሥራ ባልደረባ
🚨" ዳኛውን ‘ከቤት ሚስቱና ልጁ ካሉበት ወስደው ቴዎድሮስ አደባባይ ላይ ገደሉት’ አሉኝ። ባለሙያዎችም ታግተዋል፤ የፍትህ ጽ/ቤት ኃላፊውን ጨምሮ !! "
በአማራ ክልል የምዕራብ ጎንደር ከፍተኛ ፍርድ ቤት የቋራ ወረዳ ፍርድ ቤት የፍትሃብርሄር ዳኝነት አገልግሎት ሂደት አሳጣጥ አስተባባሪ ዳኛ በአካባቢው ታጣቂዎች መገደላቸውን እናየጽ/ቤት ኃላውን ጨምሮ ሌሎች ባለሙያዎች መታገታቸውን የሟች የቀድሞ የሥራ ባልደረባ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
የአንድ ልጅ አባት እና ዳኛ የዓለምብርሃን በርሄ ገ/ህይወት፣ ነሐሴ 11ቀን 2017 ዓ/ም መገዳቸውን የገለጹት የሥራ ባልደረባቸው፣ " ጓደኞቼም ስለነበሩ በዚሁ ቀን ደውለው ‘እኛም ተደብቀን ነው ያለነው’ አሉኝ። ፋኖ ከተማ ገብቶ ዳኛውን ከቤት ሚስቱና ልጁ ካሉበት ወስደው ቴዎድሮስ አደባባይ ላይ ገደሉት አሉኝ " ሲሉ ነግረውናል።
ታጋቾችን በተመለከተ " ባለሙያዎችን አላውቃቸውም የፍትህ ጽ/ቤት ኃላፊው ግን አቶ ሀብታሙ ይባላል፤ ታግቶ እየተደራደሩበት ብር አምጡ እየተባለበት ነው። ሌሎችም አሉ የፖሊስ ሚስቶች እንደዚሁ ታግተዋል " ሲሉ ተናግረዋል።
ሟቹን በቅርበት ካወቁት ታዲያ ለዚህ የሚያደርሳቸው ጉዳይ ነበር ? ብለን ስንጠይቃቸው፣ " ምንም ነገር የለም፤ አሁን ፋኖ ባለበት አካባቢ እኔም ዳኛ ነኝ። ገለልተኛ ነን ብለን ስለምናስብ የፖለቲካ እጀባም የለንም። አስፈፃሚም ይጎስመናል፤ ተመሳሳይ ደግሞ የታጠቀ አካል እንደዚህ ያደርጋል ብለን አንጠብቅም " ሲሉ አዝነዋል ላ።
ጥቃቱን የፈጸሙት ታጣቂዎች 'ፋኖ' ስለመሆናቸውስ በምን እርግጠኛ ሆናችሁ ? በሚል ለተነሳላቸው ጥያቄ "አዎ በደምብ እሱማ የታወቀ ነው " ሲሉ መልሰዋል።
" ማንም ባለሙያ ቢሆን እንዲገደል አይገባውም፤ በተለይ ትዕዛዝ መስጠት የማይችሉ ዳኞች ባለሙያዎችም ሲሆኑ እጅግ ያሳዝናል " ሲሉም ተናግረዋል።
" አንድ ዳኛ ከፖለቲካ፣ ከገዢው መንግስት ጭምር ገለልተኛ ሆኖ ህግና ህግን መሰረት አድርጎ እንዲሰራ ነው ተሹሞ የሚወጣው። እኛም እንግዲህ በችሎት ተሰይመን የምንሰራው ይሄን ነው " ሲሉ ሙያዊ አስተያዬት ሰጥተዋል።
በክልሉ ያሉ ዳኞች ብዙ አይነት እንግልት እያስተናገዱ መሆኑን አክለዋል።
ስለግድያው ተጨማሪ ማብራሪያ የጠየቅነው የምዕራብ ጎንደር ዞን ዳኞች ንዑስ ጉባኤ ስለግድያው ኦፊሻሊ እንዳሳወቀ ገልጾ፣ ተጨማሪ ማብራሪያ ከመስጠት ተቆጥቧል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia

❤394😢177😭53💔23👏12😡8🤔7🕊5🙏4🥰1😱1
" ጊዜያዊ የማስጠንቀቂያ ምልክቶችና የጥንቃቄ ማመላከቻዎች በናዳዉ አቅራቢያ ተቀምጠዋል " - ፖሊስ
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል በካፋ ዞን በጊምቦ ወረዳ ዉሽዉሽ ቀበሌ ልዩ ስም " ቦጫች " ተብሎ በሚጠራበት አከባቢ የካፋ ዞንን ከቦንጋ ፣ ሺሾእንዴ ወረዳ፣ ጨና ወረዳ፣ ሚዛን ፣ ቴፒ፣ ምዕራብ ኦሞ ዞን የሚያገናኘዉ ዋናዉ የአስፋልት መንገድ ሰሞኑን በአከባቢዉ እየጣለ ባለዉ ከባድ ዝናብ መንሸራተቱን ተከትሎ መንገዱ በአንድ በኩል ከባድ ጉዳት አስተናግዷል።
መስመሩ የተሽከርካሪዎች ምልልስ የሚበዛበት በመሆኑ ለችግሩ ዘላቂ መፍትሔ እስኪበጅለት የትራፊክ አደጋ እንዳያስከትል ጊዜያዊ የማስጠንቀቂያ ምልክቶችና የጥንቃቄ ማመላከቻዎች በአቅራቢያዉ መቀመጣቸው ተገልጿል።
በመስመሩ የሚንቀሳቀሱ አሽከርካሪዎች ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ማሳሰቢያ ተላልፏል።
ይህን መረጃ በአከባቢው ለሚያሽከረክሩ አሽከርካሪዎች በማዳረስ ሁሉም ተባባሪ እንዲሆንም ተጠይቋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

❤275🙏37😢11🕊9🥰4😭4😱3💔3
" ዜጎች ከማያውቁት ሰው ጋር በማንኛውም የማህበራዊ ሚዲያ መተግበሪያዎች ምንም ዓይነት ግንኙነት ባለመፍጠር ከመሰል ወንጀሎች ራሱን ሊጠብቅ ይገባል " - ፖሊስ
የተለያዩ ሴቶችን ፎቶ ግራፍ ከቴሌግራምና ከቲክቶክ በማውረድ በከፈተው ሀሰተኛ አካውንት እለቃለሁ ብሎ በማስፈራራት ክብርን በማዋረድና የፆታ ግኑኝነት በመጠየቅ የተጠረጠረን ግለሰብ ይዞ ምርመራ እያጣራ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ገለፀ።
ሀምሌ 30 ቀን 20017 ዓ/ም ከምሽቱ 12 ሰአት ተኩል ሲሆን በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 5 ልዩ ቦታው ብሔረ ፅጌ መናፈሻ እየተባለ ከሚጠራው አካባቢ ነው ወንጀሉ የተፈፀመው።
አንተን አየሁ ሞላ የተባለው ተጠርጣሪ ራሱ ባዘጋጀው ሰቦንቱ ኤጀንት ሰርቪስ የሚል ሀሰተኛ የቲክቶክ አካውንት በመክፈት የግለሰቦችን ፈቃደኝነት ሳይጠይቅ ከቴሌግራም፣ ከቲክቶክ እንዲሁም ሴቶችን መንገድ ላይ በሚጓዙበት ወቅት ፎቶ በማንሳትና ቪዲዮ በመቅረፅ ራሱ በከፈተው አካውንት ላይ አቀናብሮ በመልቀቅ ግለሰቦችን በማስፈራራትና በማስገደድ የፆታ ግኑኝነት ጭምር የሚጠይቅ ግለሰብ መሆኑን የምርመራ መዝገቡ ያስረዳል፡፡
ተከሳሹ ወይዘሮ ሰላማዊት ታደሰን የቤት ተከራይ መስሎ በመቅረብ ስልክ ቁጥሯን በመውሰድ የራሱ ባልሆነ ስልክ ቁጥር በመጠቀም ከቴሌግራም ላይ ፎቶዋን በማውረድና በማቀናበር ግላዊ የፆታ ግኑኝነት ከሷ ጋር እንድትፈፀም ያቀናበረውን ሰነድ በማስፈራሪያነት በመጠቀም ያስገድዳታል።
የግል ተበዳይም " ባለትዳርና የልጆች እናት ነኝ ይህንን ድርጊት ለመፈፀም ፈቃደኛ አይደለሁም " ብትለውም ማስፈራራቱን ባለማቋረጥ ባዘጋጀው ሀሰተኛ የቲክቶክ አካውንት " ሹገር ማሚ " ስለሆነች በእኔ አካውንት ማግኘት ትችላላችሁ በማለት ከአንድ ሺ በላይ ተከታይ ባለው የቲክቶክ አካውንት በማጋራቱ የግል ተበዳይ ለፖሊስ አመልክታለች፡፡
የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የደረሰውን አቤቱታ መነሻ በማድረግ ግለሰቡን በቁጥጥር ስር አውሎ ለአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የሴቶች እና ህፃናት ወንጀሎች ምርመራ መላኩን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ገልጿል።
በተጠርጣሪው ግለሰብ ላይ ፖሊስ ባደረገው ምርመራ የማስፋት ተግባር ከሃያ በላይ የሚሆኑ ሴቶች ላይ ተመሳሳይ ድርጊት ለመፈፀም ካዘጋጃቸው ፎቶዎች ጋር መያዙንም ፖሊስ አስታውሷል፡፡
ዜጎች ከማያውቁት ሰው ጋር በማንኛውም የማህበራዊ ሚዲያ መተግበሪያዎች ምንም ዓይነት ግንኙነት ባለመፍጠር ከመሰል ወንጀሎች ራሱን ሊጠብቅ እንደሚገባም የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ መልዕክቱን ያስተላልፋል፡፡
#AddisAbabaPolice

❤1.18K👏284😡125🤔103😭78🙏36😱30💔27😢17🕊11🥰2
" በጭጋጋማ የአየር ጸባይ ምክንያት በርከት ያሉ የሃገር ውስጥ በረራዎች መስተጓጎል ገጥሟቸዋል "- የኢትዮጵያ አየር መንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ባለው ለበረራ አመቺ ያልሆነ ጭጋጋማ የአየር ፀባይ ምክንያት በርከት ያሉ የሀገር ውስጥ በረራዎች ነሐሴ 13 ቀን 2017 ዓ.ም መስተጓጎል እንደገጠማቸው ባወጣው መግለጫ አሳውቋል።
አየር መንገዱ በዛሬው ዕለትም ተመሳሳይ የአየር ፀባይ በተወሰኑ ጣቢያዎች ላይ ስለተስተዋለ ወደ እነዚህ ጣቢያዎች የሚደረጉ በረራዎች ማድረግ አንዳልተቻለ ገልጿል።
የአየሩ ሁኔታ ሲሻሻል መደበኛ በረራዎች ወዲያውኑ እንደሚጀመሩ የተገለጸ ሲሆን በዚህ ምክንያት ለተፈጠረው የደንበኞች መጉላላት ደንበኞቹን ይቅርታ ጠይቋል።

1❤813👏76🕊61🤔46😱30💔25🙏18😭14🥰9😢7😡6
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በሽ ጥቅል የሚገዙ ዕድለኞችን የሚያንበሸብሽ የገንዘብ ሽልማት ይዞ መጣ!
ዕድሉ እንዳያመልጠን፤ በሽ ጥቅል እንግዛ በሽሽሽሽ… ሽልማት እናሸንፍ *777*0# ላይ አሁኑኑ ይደውሉ!
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በአብሮነት ወደፊት!
#SafaricomEthiopia
#Besh
#FurtherAheadTogether

❤88😡12💔2
TIKVAH-ETHIOPIA
ወንድማችንን እናግዘው !! ኖሆም ብርሃኑ ይባላል። በተፈጥሮ እግር እና እጅን የመቆጣጠር ችግር ያለበት ተማሪ ነው። በአሁኑ ሰዓት ጀሞ በሚገኘው ሆኘ ዩኒቨርስቲ ትምህርቱን በመከታተል ላይ የሚገኝ ሲሆን በትምህርቱም የደረጃ ተማሪ ነው። ይህ ጎበዝ ተማሪ ካለበት የጤና ችግር የተነሳ መኖሪያ ቤቱ ከሚገኝበት አየር ጤና ኪዳነምህረት ጀሞ ወደሚገኘው ሆኘ ዩኒቨርስቲ ለመመላለስ በወር ከ15,000 ብር በላይ የትራንስፖርት…
ሁላችሁም ተመስግናችኋል !
ተማሪ ናሆም ብርሃኑ በተፈጥሮ እጅና እግሩን የመቆጣጠር ችግር ያለበትና ሆፕ በተባለ የግል ዩኒቨርሲቲ የሚማር ተማሪ እንደሆነ በመግለጽ እገዛ እንዲደረግለት ጥሪ ቀርቦ ነበር።
ያለበት የጤና ችግር ሳይገድበው በትምህርቱ ከፍተኛ ውጤት እያስመዘገበ ያለው ይኸው ተማሪ መኖሪያ ቤቱ ከሚገኝበት አየር ጤና ኪዳነ ምህረት ቤተክርስቲያን ጀሞ ወደሚገኘው ዩኒቨርስቲ ለመመላለስ በወር ከ15 ሺህ ብር በላይ የትራንስፖርት ወጪ ቤተሰቡ እንደሚያወጣ ፤ ቤተሰቦቹም አሁን ባሉበት ሁኔታ ይህን ከፍተኛ የሆነውን የትራንስፖርት ወጪ መሸፈን ስለማይችሉ እገዛ እንዲደረግላቸው እናተኑ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላትን ጠይቀው ነበር።
በገንዘብ እጥረት ልጃቸው ትምህርቱን ሊያቋርጥ በመሆኑ ህልሙ እንዳይጨልም እገዛ እንዲደረግ ነበር ጥሪ ያቀረቡት።
ጥሪው ተከትሎ ለተማሪው እስካሁን ድረስ በደጋግ አሳቦ ኢትዮጵያውያን ብር 194,758.00 ድጋፍ እንደተደረገ ቤተሰቦቹ ገልጸዋል።
እገዛ ላደረጋችሁ ሁሉ በእግዚአብሔር ስም ከፍተኛ ምስጋና አቅርበዋል።
#TikvahEthiopiaFamily❤️

❤785👏164🙏31🥰18😭4😢2🕊2💔1
“ ድልድዩ በመሰበሩ ህሙማንን ወደ ህክመና መውሰድ፤ ማዳበሪያ ማግኘት አልቻልንም ” - ነዋሪዎች
➡️ “ ሪፈር ተጽፎለት ለሚሄድ ህብረተሰብ የመንገዱ መሰበር ችግር ፈጥሯል ” - ምሥራቅ ጎጃም ዞን መንገድ መምሪያ
በአማራ ክልል ምሥስራቅ ጎጃም ዞን ማቻከል ወረዳ የውላ ቀበሌ የሚገኘው ትልቅ ድልድይ ባለፈው ሳምንት በጎርፍ ሳቢያ መሰበሩን ተክተሎ ሕሙማንን ወደ ህክምና ለመውሰድ፣ ማዳበሪያን ወደ አርሶ አደሩ ለማድረስ እንቅፋት መሆኑን ዞኑና ነዋሪዎቹ ገልጸዋል፡፡
በዚሁ መንገድ ተጠቃሚ የሆኑት የምሥራቅ ጎጃም ዞንና የአካባቢው ነዋሪዎች፣ ድልድዩ በመሰበሩ ህሙማንን በወቅቱ ወደ ህምምና መውሰድም ሆነ ማዳበሪያ ማግኘት እንዳልቻሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል፡፡
ከዚህም ባሻገር የድልድዩ መሰበርና በቶሎ አለመጠገን በሸቀጦች ላይ የዋጋ ንረት እያስከተለ መሆኑን፣ እንደ በርበሬ፣ ሙዝና መሰል ሸቀጦች ላይ በአንዳንድ አካባቢዎች እስከ 50 ብር ድረስ ጭማሪ እየተስዋለ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
ከነዋሪዎቹ በተጨማሪ የአፈር ማዳበሪያ ጭነው የቆሙ አሽከርካሪዎች ማዳበሪያውን በወቅቱ ከማድረስ አኳያ መስተጓጎላቸውን የገለጹ ሲሆን፣ ቅሬታው ደርሶት እንደሆንና ምን ጥረት እየተደረገ እንዳለ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የጠየቀው የኢትዮጵያ ከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማኀበር “አዎ ይቆማሉ፡፡ አንድ ድልድይ ሲሰበር ተሽከርካሪዎች መሄጃ ሲያጡ ይቆማሉ፡፡ ለድልድዩ ደግሞ መንግስት አፋጣኝ የሆነ መንገድ ሲፈጥር ይንቀሳቀሳሉ” ብሏል፡፡
የነዋሪዎቹን ቅሬታ በፍጥነት ለመፍታት ምን እየተሰራ እንደሆነ ለመጠየቅ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ወደ ምሥራቅ ጎጃም ዞን መንገዶች መምሪያ ኃላፊ አቶ ማናዬ አዳነ በተደጋጋሚ ስልክ ቢደውልም ስልካቸውን ለማንሳት ፈቃደኛ ያልሆኑ ሲሆን፣ ለአሻም ቴሌቪዥን ሰሞኑን በሰጡት ገልጻ ግን፣ መንገዱ እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰው፣ የነዋሪዎቹን ቅሬታም ተጋርተዋል፡፡
“ ድልድዩ ከፍተኛ የሆነ ዝናብ ጥሎ ከጮቄ ተንደርድሮ የመጣ ጎርፍ ሲመታው ተድርምሶ ነው የገባው” ያሉት ኃላፊው፣ ይህም የትራንስፖርት አገልግሎት ብቻ ሳይሆን የሚወጡና የሚገቡ ምርቶችን ጭምር ማስተጓጎሉን አንስተው፣ “ ሸማቾች ላይም ያደረው ጫና አለ ” ብለዋል፡፡
ወደ ማቻከል ወረዳና ወደ ደብረ ኤልያስ ወረዳ የአዞኑ አፈር ማዳበሪያ የሚጓጓዝበት ወቅት መሆኑን የገለጹት አቶ ማናዬ፣ “ በሌላ መንገድ የሰሜን ጎጃም፣ የምዕራብ ጎጃም እና ወደ ጎንደር አቅጣጫ የሚሄድ የአፈር ማዳበሪያ ነበር ተጭኖ የመጣ። ማዳበሪያ በወቅቱ ተጓጎዞ ለአርሶ አደሩ እንዳይደርስም እንቅፋት ፈጥሮብናል ” ሲሉ ተናግረዋል፡፡
“ ሌላው ከህክምና ጋር በተያያዘ ሪፈር ተጽፎለት ለሚሄድ ህብረተሰብ የመንገዱ መሰበር ችግር ፈጥሯል ” ሲሉ ያከሉ ሲሆን፣ የብረት ድልድይ በማንጠፍ አገልግሎቱን ክፍት ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን በተዘው ሳምንት ለማጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡
መምሪያ ኃላፊው የተሰበረው ድልድይ ከደብረ - ማርቆስ - ደንበጫ - ፍኖተሰላም - ዳንግላ - ባሕርዳር ያሉትን አካባቢዎች የሚያገናኝ የአዲስ አበባ - ድብረ ማርቆሱ ድልድይ መሆኑን ጠቅሰው፣ በ1935 ዓ/ም የተገነባ እንደነበርም አስታውሰዋል፡፡

❤200💔49🙏15😢11😭10🕊9😡5👏4
በመብረቅ አደጋ የሁለት ሰዎች ህይወት አልፏል።
ነሀሴ 12/2017 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 በትግራይ ምስራቃዊ ዞን ክልተ ኣውላዕሎ ወረዳ ታሕታይ ዓድቕሳንድድ ቀበሌ " ሞፅቖ " በተባለ ልዩ ቦታ ጎድጓዳማና ሀይለኛ ዝናብን ተከትሎ በወደቀው መብረቅ የሁለት ሰው ህይወት ጠፍቷል።
የአከባቢው ተወላጆች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ - መቐለ በሰጡት መረባ የመብረቅ አደጋው በእረኝነት ላይ የነበሩ የ13 እና 19 ዓመት ዕድሜ ያላቸው የሁለት ወንዶችን ህይወት ወዲያው አጥፍቷል።
መብረቁ በአከባቢው ባለው ሰፊ ዋሻ ተጠልለው ከነበሩት እንስሳት በ21 ጉዳት አድርሷል።
ከመብረቅ አደጋ ራሳችንን እንዴት መጠበቅ እንችላለን ?
(ተባባሪ ፕሮፌሰር ታደሰ ተረፈ የዘርፉ ተመራማሪ - ለኢቢሲ ተናግረው ከነበረው)
- በዝናብ ወቅት የቤት በርና መስኮትን መዝጋት፣
- ከከፍታ ቦታ መራቅ፣
- በመኪና ውስጥ ከሆኑ ዘጋግቶ መቀመጥ፣
- ሜዳ ላይ ለብቻ አለመገኘት፣
- መብረቅ ወደ የኤክትሪክ ገመድ ገብቶ ተጨማሪ የኤሌክተሪክ ፍሰት በመጨመር ኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን ሊያቃጥል ይችላል፡፡ ስለዚህ ሬጉሌተር መግጠም ወይም በመብረቅ ሰዓት ሶኬቶችን መንቀል ያስፈልጋል።
- ህንጻዎች እንዳይመቱ አናታቸው ላይ የብረት ገመድ ተዘርግቶ አንዱን ጫፍ ወደመሬት በመቅበር መከላከል ይቻላል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

2❤616😢330😭146🙏66🕊55💔46🤔11🥰6😱6👏4