Telegram Group Search
»»»»

   ════ HUAWADA FELLOW════

  ውድ የጌታ ብሩካን!! ሰላም ለናንተ ይሁን🥰

እንኳን ጌታ ረድቷችሁ ፥ በሰላም የፍሬሽ-ማን ትምህርት አጠናቀቃችሁ ። እንደሚታወቀው ክረምቱ እየተገባደደ የትምህርት ጊዜ እየደረሰ  ይገኛል ። ስለዚህ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ዲፓርትመንት ደርሷችሁ ይርጋለም(አዋዳ) የምትመጡ ተማሪዎች ፌሏችንን ቀድማችሁ ተቀላቅላችሁ ፦ ስለ አከባቢው ፣ ግቢውና ህብረቱ መረጃ እንድታገኙ ፣ እኛ የአዋዳ ግቢ  ክርስትያን ተማሪዎች ጥሪ እናቀርባለን ።

ቀጥሎ የተጠቀሱ ስልኮችን በመጠቀም እንዲሁም መጨረሻ ያለውን ሊንክ በመጫን ተቀላቅላቅላችሁ የምትፈልጉትን መረጃ ማግኘት ትችላላችሁ ::

   ════ HUAWADA FELLOW════

Ephrata 09 40 24 39 99
Lemi 09 48 15 84 85
El roi 09 21 02 45 92
Binyam 09 54 64 34 82
Mintesnot 09 39 13 01 83

JOIN US ON : TELEGRAMTIKTOK
              »»-----------
              ፀጋና ሰላም ይብዛላችሁ🥰
12
ሰላም የፌሎኣችን ልጆች እንዴት ቆያችሁ 😍 የእፍረት ጊዜው እየተገባደደ ቢሆንም የቀሩትን ጥቂት ጊዜያት እራሳችሁን ለማነፅ እየተጠቀማችሁ እንድታሳልፉ ልናበረታታችሁ እንፈልጋለን።

ባለፉት ተከታታይ አራት ሳምንታት ከጋሽ ንጉሴ ቡልቻ ጋር የወንጌል አደራ በሚል ሀሳብ ከሁለተኛ ጢሞቲዎስ መልእክት ተምረናል።

ለሚቀጥሉት ሁለት ተከታታይ ሳምንታት ደግሞ ኢየሱስን ከመፅሐፍት ሁሉ በሚል ሀሳብ ከፓስተር በረከት በላይ ጋር እንቆያለን።

ስለሆነም ነገ ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ጀምሮ በቀጥታ የቴሌግራም ፕሮግራም ላይ
*በፀሎት
*በአምልኮ እና
*በትምህርት ህብረት እናደርጋለን። በሰዓታችን እንገናኝ 🏃🏃‍♀


“አንተ ፊቴን እሹት ባልህ ጊዜ፦ አቤቱ፥ ፊትህን እሻለሁ ልቤ አንተን አለ።”
— መዝሙር 27፥8



@HUFellow
#Friday_Service_Online
#የኢየሱስን_መንገድ_መከተል
18😍2👍1
ሰላም የፌሎሺፓችን ቤተሰቦች እንዴት ናችሁ ? ከዚህ ቀደም በሰመር ሚሽን ወደ ደቡብ ኦሞ ለወንጌል ስራ ተሰማርተን ነበር ። በእግዚአብሔር እርዳታ አመቱን ስንማር እንደቆየነው የኢየሱስን መንገድ የኢየሱስን ተልዕኮ በመፈፀም ለመከተል በመወሰን እንደ ፌሎሺፕ በደቡብ ኦሞ ኛንጋቶም ወረዳ ኛትሮማይ ከተማ ከነሀሴ 1 2017 ጀምሮ በእኛ ሐዋሳ ሜንካምፓስ ፌሎሺፕ የሚደገፍ  ሚሽነሪ ልከናል ። በመሆኑም እግዚአብሔር በብዙ ፍሬ እንዲባርከን ፣ ብዙ በወንጌል የሚለወጡና ደቀመዝሙር የሚሆኑ ሰዎችን እንዲያበዛልን አጥብቀን ስለ እግዚአብሔር መንግስት እንፀልይ እንዲሁም ስለ እግዚአብሔር እርዳታ አምላካችን እናመስግን  ። እግዚአብሔር ይመስገን 🙏

ይሔን የሚሽን ስራ ማገዝ የምትፈልጉ 👇 ከስር ባለው አድራሻ ልታገኙን ትችላላችሁ ።

ዳዊት ጳውሎስ +251976032509
ፊሊሞን ነጋ   +251945697795

#የኢየሱስን_መንገድ_መከተል
@hufellow
37🔥3
HUFELLOW pinned «ሰላም የፌሎሺፓችን ቤተሰቦች እንዴት ናችሁ ? ከዚህ ቀደም በሰመር ሚሽን ወደ ደቡብ ኦሞ ለወንጌል ስራ ተሰማርተን ነበር ። በእግዚአብሔር እርዳታ አመቱን ስንማር እንደቆየነው የኢየሱስን መንገድ የኢየሱስን ተልዕኮ በመፈፀም ለመከተል በመወሰን እንደ ፌሎሺፕ በደቡብ ኦሞ ኛንጋቶም ወረዳ ኛትሮማይ ከተማ ከነሀሴ 1 2017 ጀምሮ በእኛ ሐዋሳ ሜንካምፓስ ፌሎሺፕ የሚደገፍ  ሚሽነሪ ልከናል ። በመሆኑም እግዚአብሔር…»
HUFELLOW pinned a photo
ልንጀምር 1️⃣0️⃣ ደቂቃዎች ብቻ ስለቀሩን ሁላችንም Online ሆነን እንዘጋጅ እንዲሁም ለሌሎች እንዲገቡ እየጋበዝን እንቆይ።
@hufellow
#የኢየሱስን መንገድ መከተል
#live fellowship program
7🔥1
ሰላም የተወደዳችሁ ዛሬም ሌላ እድል የሰጠን አምላክ የተመሰገነ ይሁን። በመዝሙር መጽሐፍ እንዲህ እንደሚል

“በማለዳ ምሕረትህን እንጠግባለን፤ በዘመናችን ሁሉ ደስ ይለናል ሐሤትም እናደርጋለን።”
— መዝሙር 90፥14

ደስታችን ምህረቱ ነው በእርሱም እንታመናለን ክብር ለእርሱ ይሁን።

አስቀድመን ከገሜ ጋር ፀልየን ፕሮግራማችንን እንጀምራለን። እስከመጨረሻው አብረን እንቆይ ☺️



@HUFellow
#Friday_Service_Online
#የኢየሱስን_መንገድ_መከተል
6
Audio
10🔥2
በፀሎት ያገለገለን ወንድማችንን ጌታ ይባርከው 🙌



ቀጥለን ወደ ዝማሬ ነው የምናመራው ከኳየርስ ጋር አብረን ጌታን እናመልካለን

🎹🎹🎹🎤🎤🎤🎸🎸🎸🥁🥁🥁



@HUFellow
#Friday_Service_Online
#የኢየሱስን_መንገድ_መከተል
8
ስለ ዝማሬው እግዚአብሔር ይመስገን ኳየርስን ጌታ ይባርካቸው 🙌


አሁን ለአንድ የህዝብ ክፍል እንፀልያለን ሳምንቱንም በፀሎታችን እያሰብናቸው እንቆይ 🙏




@HUFellow
#Friday_Service_Online
#የኢየሱስን_መንገድ_መከተል
7
እግዚአብሔር ሆይ ታላቅ ስለሆነው የማዳን እቅድህ ተመስገን። ማንም እንዳይጠፋ ወደህ ትታገሳለህ እንጂ ለሀጥያተኛው የማትራራ አምላክ አይደለህም። ለሰው ልጆች ሁሉ የሀጢአት እዳ ኢየሱስን ከፈልከው። አሁን በእርሱ ስራ የሚያምን ሁሉ ታላቁ ስጦታህን ትቸረዋለክ።


በዚህ ሰዓት በተለያየ እስራት፣ ጨለማ፣ ቀንበር እና ግራ መጋባት ውስጥ ያሉ በአርሲ የሚገኙ ወገኖቻችንን እንድታገኝ እንጠይቅሀለን። አንተን ማወቅ የሀይማኖት ስርዓትን ከመፈፀም የሚልቅ ነው። ምክንያቱም አንተ ህይወት ነህ። ይህን ህይወት ላልተካፈሉ ሁሉ እንደቸርነትህ መጠን አካፍላቸው።
አይኖቻቸው ተከፍተው ታላቅ የሆነውን የፍቅርህን ጉልበት ያስተውሉ ዘንድ ቅዱሱ መንፈስ ሆይ እርዳቸው።


ብቻህን አምላክ ለሆንክ፣ ብቻህን ለምትገዛና ብቻህን ለምትመለክ እግዚአብሔር ክብር ይሁን። ታላቅ ሆነህ ሳለ ቀርበኸናልና ስለፍቅርህ እናመሰግንሃለን። በኢየሱስ ስም አሜን 🙏




@HUFellow
#Friday_Service_Online
#Unreached_area_pray
#የኢየሱስን_መንገድ_መከተል
🔥13🙏21
ቀጥለን በሚከተሉት አካውንት ቁጥሮች በመስጠት ጌታን እናገለግላለን ፌሎሺፓችንንም እንደግፋለን  💰💰


“... ፤ የሚሰጥ በልግስና ይስጥ፤ ....”
  — ሮሜ 12፥8



@HUFellow
#Friday_Service_Online
#የኢየሱስን_መንገድ_መከተል
👍11
አሁን ሰዓቱ የእግዚአብሔርን ቃል የምንሰማበት ነው። ኢየሱስን በመፅሐፍት ሁሉ ውስጥ ልንማረው ከፓስተር በረከት በላይ ጋር አብረን እንቆያለን።

📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖



@HUFellow
#Friday_Service_Online
#Word_of_God
#የኢየሱስን_መንገድ_መከተል
9
Audio
😍13🔥2
መፅሐፍት ሁሉ ስለኢየሱስ ይመሰክራሉ። ዩሐ 5:39
-> ኢየሱስ የትኩረት ሁሉ ዋና ነው።
-> እርሱን ስሙት ብሎ አብ የመሰከረው ስለ ልጁ ስለኢየሱስ ነው።
-> ኢየሱስ የአብን ደስታ የፈፀመ ነው።
-> ኢየሱስ ብቸኛው የመዳን መንገድ ነው።
->በእርሱ ህይወት አለ።


👉ሰማይ ትኩረት ያደረገበት ላይ ትኩረት ስናደርግ ህይወታችን በእውነተኛ ደስታ፣ ሰላምና እረፍት  ይሞላል። አብዝተን ኢየሱስን የማወቅ ረሀብ ይብዛልን።



ፓስተር ቤኪን ጌታ አብዝቶ ይባርከው። ትምህርቶቹን በሚገባ መስማታችንን አንዘንጋ። የዛሬው ፕሮግራማችንን ጨርሰናል። በተለያየ መንገድ ያገለገሉንን ጌታ አብዝቶ ይባርካቸው 🙌


ሳምንት በተመሳሳይ ሰዓት እንገናኛለን እስከዛው የጌታ ፀጋና ሰላም ይብዛላችሁ 😍😍😍



@HUFellow
#Friday_Service_Online
#የኢየሱስን_መንገድ_መከተል
11
digital purity week ደረሰ😊

ውድ የፌሎሺፓችን ልጆች እነደምን ቆያቹ digital purity week ከ ነሀሤ 20 ጀምሮ sexual purity በተመለከተ በየተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ትኩረት አድርገን እንማማራለን።


እንዳያመልጣቹ!!
⭐️share⭐️
  FACEBOOK | TIKTOK
INSTAGRAM | YOUTUBE

@hufellow
#Sisters_ministry
#Horeb_Ds
20🔥5
2025/08/23 20:34:33
Back to Top
HTML Embed Code: