✨ “በአልን ብቻዬን አላከብርም”
ዘመቻ በሰው ለበጎ የበጎ አድራጎት ድርጅት✨
ይህ ፕሮጀክት በዚህ አዲስ አመት በችግር ውስጥ ያሉ ቤተሰቦች በአልን በደስታ እንዲከብሩ በመርዳት በበዓል ሰሞን የሚታየውን መሳቀቅ እና በር ዘግቶ በብቸኝነት ማሳለፍ ለማስቀረት የተጀመረ ነው ።
❤️
በዚህ ፕሮጀክት ለ400 ቤተሰቦች የበዓል ፓኬጅ፣ ምግብና አልባሳት ለመድረስ የገንዘብና የቁሳቁስ ለማሰባሰብ አቅደን ተነስተናል።
👉 የሚያስፈልጉት ቁሳቁሶች፦ ሸንኩርት፣ ዘይት፣ ዱቄት፣ በርበሬ፣ ከሰል፣ እንቁላል እና አልባሳት
👉 የማጠናቀቂያ ቀን፦ ጻጉሜ 5
👉 ዋና አላማ፦ 400 ቤተሰቦች በደስታ አዲስ አመትን እንዲያሳልፉ ማድረግ
📌 ማንኛውም ልገሳ፣ ትንሽ ቢሆን ትልቅ ለውጥ ያመጣል!
📞 0912102591 / 0912441612
🌐 http://www.sewlebego.com
በገንዘብ ማገዝ ለምትፈልጉ 👇👇
💳 አካውንት ቁጥር፦
* 1000644753027 (ንግድ ባንክ)
* 1244 (ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ)
📍 ኮተቤ ካራ ስላሴ አካባቢ

2❤333🙏16👏8🕊6😭5😢1
ክቡራን ደንበኞቻችን! መጪው አዲስ ዓመት የሰላም፤የፍቅር እና የስኬት እንዲሆንላችሁ ከወዲሁ ከልብ እየተመኘን፡ ምቾታቸውን እና ጥራታቸውን የጠበቁ ምርቶቻችንን በሁሉም የማሳያ ቅርንጫፎቻችን ከአዲስ ዓመት ቅናሽ ጋር አዘጋጅተን እንጠብቅዎታልን!!
መልካም አዲስ ዓመት!
Visit us today @
📍 22 - ዋሪት ህንፃ
📍 ጉርድ ሾላ - ሴንቸሪ ሞል
📍 ለቡ - ቫርኔሮ ፊት ለፊት
📍 አዳማ - ሶረቲ ሞል
📍 ቡልቡላ- ልዑል ህንፃ ፊት ለፊት
📍 ወሎ ሰፈር- Ethiolife life real estate
📍 ጦር ሀይሎች- ኩዊንስ ፊት ለፊት
ዋሪት ፈርኒቸር
ትክክለኛ ምርጫ!
ለተጨማሪ መረጃ: ☎️ 0911210706/07
https://www.group-telegram.com/warytfurniture
tiktok:/warytzefurniture

❤149👏5😭4🥰1😡1
የዋጋ ግሽበት ምንድነው፣ እንዴትስ ይሰላል ?
" የዋጋ ግሽበት ማለት የሸቀጦች ዋጋ የጨመረበት ፍጥነት/መጠን ማለት ነው። የዋጋ ግሽበቱ ዝቅተኛ ነው ማለት፣ የሸቀጥ ዋጋ ቀነሰ ማለት ሳይሆን የሚጨምርበት ፍጥነት ቀንሷል ማለት ነው " - አረጋ ሹመት (ዶ/ር)
በኢትዮጵያ የነሐሴ ወር አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት መጠነኛ ቅናሽ አሳይቶ 13.6 በመቶ መድረሱን የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት አስታውቋል። አሃዙ በሐምሌ ወር ከነበረው 13.7 በመቶ ጋር ሲነፃፀር የ0.1 በመቶ ቅናሽ ያሳያል።
የምግብ ነክ ዋጋ ጭማሪ 12.7% ሲሆን ምግብ ነክ ያልሆኑ ሸቀጦች ዋጋ ጭማሪ 15.1 በመቶ ነው።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ " የዋጋ ግሽበት ቀነሰ " ሲባል ምን ማለት እንደሆነ ከወራት በፊት (ግንቦት ላይ) ከአንድ ባለሙያ ጋር ቆይታ አድርጎ ነበር።
የኢኮኖሚያዊ ትርጉሙን በተመለከተ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ማብራሪያ እንዲሰጡ የጠየቃቸው በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ባለሙያዎች ማህበር ከፍተኛ ተመራማሪ አረጋ ሹመት (ዶ/ር) ናቸው።
ተመራማሪው ፤ የዋጋ ግሽበት ማለት የሸቀጦች ዋጋ የጨመረበት ፍጥነት/መጠን መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ለምሳሌ ፦ አምና ግንቦት ወር ላይ የነበረው የሸቀጦች ዋጋ ጭማሪ 25.6 በመቶ ከነበረ፣ በዚህኛው አመት ግንቦት ወር ላይ በ12.1 በመቶ ጨምሯል፡፡ የሸቀጦች ዋጋ ጨምሯል፣ ዘንድሮ የታየው ጭማሪ ግን ከአምናው ያነሰ ነው እንደማለት ነው፡፡
ባለሙያው እንደሚሉት፣ የዋጋ ግሽበቱ ዝቅተኛ ነው ማለት፣ የሸቀጥ ዋጋ ቀነሰ ማለት ሳይሆን፣ የሸቀጦች ዋጋ ጨምሯል፣ የጭማሪው መጠን ግን ከአምናው ያነሰ ነው ማለት ነው፡፡
ሌላ ምሳሌ ፦ የዘንድሮው የዋጋ ግሽበት 14 ፐርሰንት ከሆነ፣ አምና 15 ብር የነበረው የእንቁላል ዋጋ፣ ዘንድሮ በ14 በመቶ ጨምሮ ዋጋው 17 ብር ይደርሳል ማለት ነው፡፡ አምና ግንቦት ወር ላይ እንቁላል ከ10 ብር ተነስቶ 15 ብር ከደረሰ፣ ዘንድሮ ግንቦት ወር ላይ ደግሞ በ2 ብር ጨምሮ ከ15 ብር 17 ብር ደርሶዋል ማለት ነው፡፡
የዘንድሮ የዋጋ ግሽበት ዝቅ ያለ ነው ሲባል፣ የዘንድሮ የዋጋ ጭማሪ መጠን ከአምናው የዋጋ ጭማሪ መጠን ያነሰ ነው፣ ወይም አምና እንቁላል ዋጋው በ5 ብር ሲጨምር ዘንድሮ ግን በ2 ብር ነው የጨመረው ማለት ነው ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድተዋል።
አረጋ ሹመት (ዶ/ር) በዝርዝር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን አሉ ?
" የዋጋ ግሽበት ምጣኔ ሲወጣ የሁሉም ሸቀጦች ዋጋ ተጨምቆ ነው የሚሰላው። ለምሳሌ ዋጋቸው የቀነሱ ሸቀጦች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ የእነሱ ዋጋ መቀነስ፣ የግሽበት ምጣኔውን ስሌት ወደታች ሊያወርዱት ይችላሉ፡፡
ለምሳሌ የብረት ዋጋ፣ የሲሚንቶ ዋጋ፣ የአሸዋ ዋጋ ቢቀንስ፣ ወይም ደግሞ ከውጭ የሚመጣ ሸቀጥ ዋጋው ቢቀንስ፣ ማህበረሰቡ ለዕለት የማይጠቀምበት ሸቀጥ ዋጋው ቢቀንስ፣ ነገር ግን ማህበረሰቡ በየቀኑ የሚጠቀምባቸው ሸቀጦች ዋጋቸው እየጨመረ፣ የአጠቃላይ የዋጋ ግሽበት መጠኑ ሊቀንስ ይችላል፡፡ ምግብ ነክ ያልሆኑት ሸቀጦች ዋጋቸው በመቀነሱ ምክንያት ማለት ነው፡፡
ምግብ ነክና ምግብ ያልሆኑ ሸቀጦች የዋጋ ጭማሪያቸው አንድ ላይ ተጨምቆ ነው የሚሰላው፡፡ ዋጋቸው የጨመረው ሸቀጦች፣ ዋጋቸው ከጨመረው ሸቀጦች ጋር ተደምሮ ሲሰላ ወደታች ሊጎትቱት ይችላሉ፣ የዋጋ ግሽበት ምጣኔውን፡፡
የየወሩ ደግሞ ስታሰላው 30 ምናምን የሚደርስበት ወቅት አለ፡፡ አንዳንዱ ወራት ላይ የሸቀጦች ዋጋ ረከስ ይላል፣ አንዳንዱ ወር ላይ ደግሞ ወደ ላይ ይወጣል፡፡ አመታዊው መጠን ሲሰላ፣ አነስተኛ ጭማሪ የታየባቸው ወራት፣ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ የታየባቸዋውን ወራት የዋጋ ጭማሪ ወደ ታች ይስቡትና አጠቃላይ የዋጋ ጭማሪው ሲሰላ በአመቱ ዝቅተኛ የዋጋ ጭማሪ/ግሽበት ዝቅተኛ ይሆናል፡፡
እንደ አብነት የዘንድሮ ግሽበት 14.4 በመቶ ነው ሲባል (ግንቦት ላይ ብሔራዊ ባንክ ይፋ ባደረገው) ከዚህ ቀደም በነበሩት አመታት በ20፣ 25፣ 28፣ 30 በመቶ እየጨመረ የነበረው የዋጋ ግሽበት፣ አሁን በ14.4 በመቶ ጨምሯል ማለት ነው ህብረተሰቡ ላይ፡፡
የህብረተሰቡ ገቢ ሳይጨምር፣ አምና በጨመረው 30 ፐርሰንት ዋጋ ላይ ዘንድሮ 14.4 በመቶ ዋጋ ጨመረበት ማለት ነው፡፡ ይህ የዋጋ ጭማሪ እንግዲህ ገቢው ምንም ሳይለውጥ/ሳያድግ ነው፡፡
የህብረተሰቡ ገቢ በ15 እና በ16 በመቶ አድጎ ቢሆን ኖሮ፣ የዘንድሮ የ14.4 በመቶ የዋጋ ግሽበት ብዙም ጉዳት አያስከትልም ሊባል ይችላል፡፡ የተሻሻለ ንግድ፣ የተሻሻለ ገቢ እና የተሻሻለ እንቅስቃሴ በሌለበት ሁኔታ፣ የዋጋ ግሽበቱ በ14 በመቶ ሲጨምር ግን በጣም ትልቅ ነው፡፡
ባለፉት ተከታታይ አመታት ከ 20 እስከ 30 በመቶ የሚደርስ የዋጋ ግሽበት ሲያሰቃየው የነበረ ማህበረሰብ አሁንም ሲጨመርበት ጫናው በጣም ትልቅ ነው፡፡
ግሽበቱ በሚያድግበት ደረጃ፣ ያንተ ገቢ ካላደገ፣ ኢኮኖሚያዊ ጉዳቱ ከፍተኛ ይሆናል፡፡ ያንተ ገቢ ባለበት ቆሞ፣ የሸቀጦች ዋጋ ግን ዝም ብሎ ይጨምራል፡፡ የመግዛት አቅምህን በጣም ያዳክሞዋል፡፡
እንደ ኢትዮጵያ ያለ እያደገ ላለ ኢኮኖሚ እስከ 7 በመቶ የዋጋ ግሽበት፣ ብዙም ከባድ አይባልም፡፡ ለሌሎች ሀገራት 2፣ 3፣ እና 4 በመቶ የዋጋ ግሽበት በጣም ከባድ ነው፡፡ እስከ 5 በመቶ የዋጋ ግሽበት ኢኮኖሚውን የሚያሰራ ግሽበት (ዎርኪንግ ኢንፍሌሽን) ይባላል፡፡ ከዛ በላይ እየጨመረ እስከ 10 በመቶ ከደረሰ ችግር የሚያስከትል ግሽበት ይባላል፡፡
ከ20 በመቶ በላይ ከሆነ በጣም አስቸጋሪ የሆነ ግሽበት ነው፡፡ ጋሎፒንግ ኢንፍሌሽን ይባላል፡፡ ከ100 ፐርሰንት በላይ ከሆነ ደግሞ ሃይፐር ኢንፍሌሽን ይባላል፡፡ ቀውስ የሚያስከትል ግሽበት ማለት ነው፡፡ እነ ጀርመን በ 1929 ዓ.ም ሲያስተናግዱት የነበረ አይነት ነው፡፡
ስለዚህ አሁን በእኛ ሀገር ያለው የዋጋ ግሽበት ከ10 በመቶ በላይ ስለሆነ፣ ችግር ውስጥ ነው ያለው፡፡ የገቢ እድገት በሌለበት ሁኔታ፣ የመግዣ ዋጋው ላይ በሆነ ፐርሰንት ሲጨመርበት በጣም ትልቅ ነው፡፡ ህብረተሰቡ ላይ እፎይታ እንዲመጣ ከተፈለገ፣ ምግብ ነክ የሆኑ ሸቀጦች ላይ ዋጋ እንዲቀንስ ነው መሰራት ያለበት። "
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamliyAA
@tikvahethiopia

1❤634😡75😭23🤔20🕊7💔6🙏5😢2
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update
ሰሞኑን በጸጥታ አካላት ታሰሩ የተባሉ የጉሙዝ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ጉህዴን) አመራሮች ዛሬ ምሽት መፈታታቸውን ፓርቲው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።
ዛሬ ሁለት ሰዎች ተጨምረው የታሰሩ ሰዎች 7 ደርሶ የነበረ ቢሆን ፓርቲው አመሻሹን በሰጠው መረጃ ሁሉም ከእስር ተለቀዋል።

❤197👏36🤔26🕊22😭15🥰6😱4😢4
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#MoE
ትምህርት ሚኒስቴር ከ2018 የትምህርት ዘመን ጀምሮ ተማሪዎች ሞባይል ስልክ፣ ታብሌት እና መሰል ኤሌክትሮኒክስ ቁሶችን ይዘው ወደ ትምህርት ቤት እንዳይሔዱ ከልክሏል፡፡
ትምህርት ሚኒስቴር በ2018 የትምህርት ዘመን አጀማመር ላይ ከክልል እና ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች ጋር የበይነ-መረብ ምክክር አድርጓል።
የ2018 ትምህርት ዘመን የመማር ማስተማር ሥራ ሰኞ መስከረም 05/2018 ዓ.ም እንደሚጀመር ተገልጿል።
ተማሪዎች ተንቀሳቃሽ ስልክ፣ ታብሌት እና መሰል ኤሌክትሮኒክስ ቁሶችን ይዘው በትምህርት ቤት መገኘት ክልክል መሆኑን ሚኒስቴሩ አሳስቧል።
በሌላ በኩል፤ ባለፈው ዓመት ከትምህርት ገበታ ውጪ የሆኑ ተማሪዎችን ጨምሮ ሁሉም ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ህጻናት እና ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት እንዲመጡ ወላጆች፣ መምህራን እና የዘርፉ ባለድርሻዎች የሚጠበቅባቸውን እንዲወጡ ተጠይቋል።
Via @tikvahuniversity

2❤2.07K👏543😡147😭125🙏112🤔47💔40🕊31🥰18😢16😱10
#Tecno_Camon_40_Pro
ውይ! ስልኬ ከእጄ ላይ አመለጠኝ ይተርፍ ይሆን? ይህ Tecno Camon 40 Pro ጋር ጥያቄ አይደለም! 360 ዲግሪ ዙሪያውን ቢወድቅ እንክዋን መውደቅን እንዲቋቋም ተደርጎ ስለተሰራ ምንም ሳይሆን እንዲነሳ የሚያስችል ጥንካሬን አብሮ ይዟል፡፡ Tecno Camon 40 Pro ያለምንም ስጋት የሚመርጡት!
#Camon40Pro #FlashSnap #TecnoAI #TecnoCamon40Series
@tecno_et

❤147😱10🙏6💔6😢2
አዲስ አበባ ምን አለ ? የሀገራት መሪዎች እየገቡ ያሉትስ ለምንድነው ?
የተለያዩ አገራት መሪዎች እና ልዑካን ወደ አዲስ አበባ እየገቡ ነው።
ኢትዮጵያም እንግዶቿን እየተቀበለች ነው።
መሪዎች እና ልዑካን አዲስ አበባ እየገቡ ያሉት ለ2ተኛው አፍሪካ-ካረቢያን ማህበረሰብ ጉባኤ እና ለአፍሪካ አየር ንብረት ጉባኤ ለመሳተፍ ነው።
እስካሁን ፦
- የአንቲጓና ባርቡዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር አልፎንዞ ብራውን ፣
- የሴንት ቪንሴንትና ግሪናዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር የተከበሩ ራልፍ ጎንሳልቬስ
- የባህማስ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ፍሊፕ ኤድዋርድ
- የሰይንት ኪትስ እና ኔቪስ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ቴራንስ ድሩ
- የባርባዶስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚያ ሞተሊ
- የግሪናዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ዲክን ሚሸል
- የአንጎላ ፕሬዚዳንት ዣዎ ሎሬንስ
- የሳህራዊ አረብ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ብራሂም ጋሊ
- የኬንያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ
- የአፍሬክሲም ባንክ ፕሬዝዳንት ቤኔዲክት ኦኬቹቹ ኦራማህ
- የጋምቢያ ምክትል ፕሬዝዳንት ሞሃመድ ጃሎ
- የጅቡቲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ሁሴን አብዱልቃድር ፣
- የጋና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሙኤል ኦኩዴዜቶ አብላክዋ አዲስ አበባ ገብተዋል።
#TikvahEthiopiaAddisAbaba

❤497😡45👏30🕊19🤔12😭11😢4🙏4😱3
TIKVAH-ETHIOPIA
" 2017 ዓም የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ያመነጨው 29.5 ጊጋ ዋት ሰአት ሃይል ውስጥ 33 በመቶ የሚሆነው ከታላቁ የህዳሴ ግድብ የተገኘ ነው " - የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ምርቃት አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል። ቲክቫህ ኢትዮጵያም መግለጫውን ተከታትሏል። መግለጫውን የሰጡት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር…
#ETHIOPIA🇪🇹
" የአፍሪካ ራሷን የመቻል ምልክት በሆነው የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ምርቃት ላይ ይገኛሉ " - የኬንያ ስቴት ሀውስ
የኬንያው ፕረዚዳንት ዊሊያም ሩቶ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ምርቃት ላይ በክብር እንግድነት ይገኛሉ።
ዛሬ አዲስ አበባ የገቡት የኬንያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ምርቃት ላይ እንደሚገኙ የኬንያ ስቴት ሀውስ አሳውቋል።
የኬንያ ስቴት ሀውስ ፕረዚዳንቱ " የአፍሪካ ራሷን የመቻል ምልክት እና ለኢትዮጵያ ትልቅ ምዕራፍ በሆነው የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ምረቃ ላይ ዋና እንግዳ ሆነው ይገኛሉ" ሲል ነው የገለጸው።
#Ethiopia🇪🇹
#GERD 💪
Via @TikvahethMagazine

#Ethiopia
#GERD 💪
Via @TikvahethMagazine
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤1.56K👏222🙏57🥰34😡30🕊18😭18🤔17💔13😢8😱4
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ሸይኽ ሀጅ ኢብራሂም ቱፋ በድጋሜ ፕሬዝደንት ሆነው ተመረጡ።
ሸይኽ ሀጅ ኢብራሂም ቱፋ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝደንት በመሆን በድጋሜ መመረጣቸውን ጠቅላይ ምክር ቤቱ ዛሬ አስታወቀ።
" ምርጫችን በመስጂዳችን " በሚል ትላንት ጀምሮ በተካሄደው ምርጫ ጠቅላይ ም/ቤቱን ለ5 ዓመታት የሚመሩ ከፍተኛ አመራሮች እና ስራ አስፈፃሚ አባላት ታውቀዋል ተብሏል።
ከሰኔ 12፣ ጅምሮ በየመስጂዱ ምዝገባ ሲከናወን ቆይቶ ከ13 ሚሊዮን በላይ የሚሆን ሰው ተመዝግቦ ከትግራይ ክልል ውጭ በመላው ሀገሪቱ ከነሃሴ 9 እስከ 30 ፣2017 ዓ.ል ድረስ ድምፅ የመስጠት ሂደት ከተከናወነ በኋላ ከወረዳ ጀምሮ በየደረጃው ምክርቤቶች ተመስርተው ለቀጣዩ እርከን ተወካዬች እንደተመረጡ ተገልጿል።
ትላንት የተመሰረተው የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክርቤት ጠቅላላ ጉባኤ 195 አባላት ያሉትና ከየዘርፉ ክልሎቹን የወከሉ ሁሉ የተካተቱበት እንደሆነ ተገልጿል።
በትግራይ ክልል ምርጫ ለማካሄድ አመች ሁኔታ ባለመኖሩ ምክንያት ምርጫ ባለመካሄዱ በጠቅላላ ጉባኤ በፀደቀው መሰረት በፌደራል መጅሊስ ያለው ውክልና ባለበት የሚቆይ ይሆናል ተብሏል።
እነማን ተመረጡ ?
1. የክቡር ዶክተር ሼይኽ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ - ፕሬዝዳንት
2. ሼይኽ አብዱልከሪም ሼይኽ በድረዲን- ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት
3. ሼይኽ ጁነይድ ሀምዛ-ምክትል ፕሬዝዳንት
4. ሼይኽ ሀሚድ ሙሳ- ምክትል ፕሬዝዳንት
5. ዑስታዝ ተምኪን አብዱላሂ- ዋና ፀሀፊ (ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ) ምሁር
6. ሸይኽ አሚን ኢብሮ-የስራ አስፈፃሚ አባል (ከድሬዳዋ )
7. ዶ/ር ሙሐመድ ሳሊህ - የስራ አስፈፃሚ አባል (ከኦሮሚያ)
8. ሸይኽ ሙሐመድ አሚን አያሽ - የስራ አስፈፃሚ አባል (ከሐረሪ)
9. ሸይኽ ሙሐመድ አህመድ ያሲን የስራ አስፈፃሚ አባል (ከአፋር)
10. ሸይኽ ኢድሪስ ደጋን- የስራ አስፈፃሚ አባል (ከአማራ ክልል)
11. ዑስታዝ ፋሪስ ግርማ- የስራ አስፈፃሚ አባል (ከደቡብ ምዕራብ) ምሁር
12. ዑስታዝ ፋይሰል ኢማም - የስራ አስፈፃሚ አባል (ከጋምቤላ) ምሁር
13. ዑስታዝ ፋሪስ ጀማል - የስራ አስፈፃሚ አባል (ከደቡብ ኢትዮጵያ) ምሁር እና
14- ዑስታዝ ሽኩር ቃሲም- የስራ አስፈፃሚ አባል (ከሲዳማ ክልል) ምሁር
15 ኢንጅነር አንዋር ሙስጠፋ (ትግራይ) ምሁር ሆነው መመረጣቸውን ምክር ቤቱ አሳውቋል።
በተጨማሪም 7 አባላት ያለው የጠቅላይ ምክር ቤቱ ዑለማ ጉባኤ አባላት የተመረጡ ሲሆን
በዚሁ መሰረት፦
1. ሸይኽ አሊ መሀመድ- ሰብሳቢ
2. ዶክተር ማህሙድ ሁሴን - ምክትል ሰብሳቢ
3. ዶክተር መሀመድ ከማል- ጸሀፊ
4. ሸይኽ ኤልያስ አህመድ -አባል
5. ሸይኽ አብዱሰላም አንዋር - አባል
6. ሸይኽ ዚያድ አሊይ- አባል
7. ሸይኽ አድናን መሀመድ -አባል
ሆነው ተመርጠዋል።
ጠቅላይ ምክርቤቱን ለቀጣይ አምስት አመታት እንዲመሩ ትላንት የተመረጡ ከፍተኛ አመራሮች ዛሬ በታላቁ አንዋር መስጂድ ቃለመሃላ መፈጸማቸው ተገልጿል።

2❤803😡232👏34😭25🕊17💔17🤔16😢13😱10🥰9🙏9