group-telegram.com/AddisstandardAmh/5347
Last Update:
ዜና: #የህወሓት አመራሮች ችግሮቻቸውን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የሚያስችላቸውን የስነምግባር መመሪያ መፈራረማቸው ተገለጸ
የህወሓት አመራሮች ሁሉን አቀፍ ችግሮቻቸውን በሰላምና በውይይት ለመፍታት ተስማምተዋል፤ ለዚህም ይረዳ ዘንድ የስነ ምግባር ደንብ አውጥተው ተፈራርመዋል ሲሉ #የትግራይ የሀይማኖት አባቶች ዛሬ የካቲት 7 ቀን 2017 ዓ.ም በመቀለ ከተማ በሰጡት መግለጫ አስታወቁ።
የሀይማኖት አባቶቹ በመግለጫው “ስምምነቱን ወደፊት ለማራመድ በሚል ሁለቱም ወገኖች የስነ ምግባር ደንብ አውጥተው ተፈራርመዋል” ማለታቸውን ከትግራይ ቴሌቪዢን ያገኘነው መረጃ ያሳያል፤ መመሪያዎቹ ምን ላይ እንዳተኮሩ መረጃው የገለጸው ነገር የለም።
ላለፉት ሁለት ወራት መሪዎቹ ልዩነቶቻቸውን በንግግር እንዲፈቱ ለማድረግ በተናጠልም ይሁን በጋራ በተደጋጋሚ ጥረት ስናደርግ ነበር ሲሉ የገለጹት የክልሉ ምስራቃዊ ዞን የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ሃገረ ስብከት ሊቀጳጳስ አቡነ መርሐ ክርስቶስ ሁሉንም ችግሮቻቸውን በውይይት እንዲፈቱ መግባባት ላይ ተደርሷል ብለዋል።
ከወራት በፊት ጥቅምት 22 ቀን 2017 ዓ.ም የትግራይ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አባቶች ሁለቱን የህወሓት ቡድን በማቀረራብ "ችግሮቻቸውን በመመካከር ለመፍታት ቃል እንዲገቡ ባቀረብነው ጥያቄ ላይ አዎንታዊ ምላሽ አግኝተናል" ሲሉ መግለጻቸው መዘገቡ ይታወሳል።
================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡ https://rb.gy/jgdsjm
BY Addis Standard Amharic

Share with your friend now:
group-telegram.com/AddisstandardAmh/5347