Telegram Group & Telegram Channel
የ #ኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን አቶ ኤርሚያስ አመልጋ ላይ ምርመራ እያደረገ እንደሚገኝ ገለጸ

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን አቶ ኤርሚያስ አመልጋ እና "ጀነሲስ ኢንቨስትመንት ሰርቪስ የተባለ ኩባንያን ጨምሮ በሌሎች ግለሰቦች እና ድርጅቶች ላይ ምርመራ እያደረገ እንደሚገኝ አስታወቀ።

ባለስልጣኑ በግለሰቦቹ እና ድርጅቶቹ ላይ ምርመራ መጀመሩን የገለጸው፤ “በሀገ ወጥ መንገድ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮችን ለሀዝብ በመሸጥ ገንዘብ ሲያሰባስቡ ነበሩ” የሚል ቅሬታዎች በመቅረባቸው መሆኑን ገልጿል።

ምርመራዎች የሚደረጉት በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገ መንግስት "የመሰማት መብት" መርህ መሰረት ሲሆን፤ በህገ መንግስቱም ሆነ በሌሎች ህጎች የተሰጡ መብቶች እና ጥበቃዎች በሙሉ ይከበራሉ ብሏል::

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን የምርመራ እና አፈጻጸም ስራ ክፍል ከማቋቋምም በዘለለ ከፍትህ ሚኒስቴር፣ ከንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር፣ የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት እና ከፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ጋር በመሆን የካፒታል ገበያ ሀግ ማስከበር የቴክኒክግብረ ኃይል እንዲቋቋም መደረጉን አስታውሷል።

በመሆኑም ግለሰቦች እና ድርጅቶች ከካፒታል ገበያ ጋር ተያያዥ የሆኑ እንቅስቃሴዎች ላይ ሲሳተፉ ተገቢ የሆኑ ጥንቃቄዎችን እንዲያደርጉ ትናንት ባወጣው መግለጫ አሳስቧል።

በተጨማሪም ህብረተሰቡ ፍቃድ አግኝተናል በሚል የሚንቀሳቀሱ ወይም የሚያስተዋውቁ ግለሰቦች እና ድርጅቶች ጋር ከመዋዋል እና ገንዘብ ከመክፈሉም በፊት ፈቃድ የተሰጣቸው መሆን አለመሆኑን ከባለስልጣኑ እንዲያረጋግጥ አስጠንቅቋል።

እንዲሁም ፍቃድ ሳይሰጣቸው የካፒታል ገበያ አገልግሎት የሚሰጡ፣ ለመስጠት የሚንቀሳቀሱ እና በማንኛውም ሚዲያ የሚያስተዋውቁ ግለሰቦች እና ድርጅቶች ላይ ባለስልጣኑ ተገቢውን እርምጃ እንደሚወስድ አሳስቧል።

group-telegram.com/AddisstandardAmh/5702
Create:
Last Update:

BY Addis Standard Amharic

Share with your friend now:
group-telegram.com/AddisstandardAmh/5702

View MORE
Open in Telegram

Telegram | DID YOU KNOW?

Date: |

Apparently upbeat developments in Russia's discussions with Ukraine helped at least temporarily send investors back into risk assets. Russian President Vladimir Putin said during a meeting with his Belarusian counterpart Alexander Lukashenko that there were "certain positive developments" occurring in the talks with Ukraine, according to a transcript of their meeting. Putin added that discussions were happening "almost on a daily basis." Telegram, which does little policing of its content, has also became a hub for Russian propaganda and misinformation. Many pro-Kremlin channels have become popular, alongside accounts of journalists and other independent observers. In view of this, the regulator has cautioned investors not to rely on such investment tips / advice received through social media platforms. It has also said investors should exercise utmost caution while taking investment decisions while dealing in the securities market. Investors took profits on Friday while they could ahead of the weekend, explained Tom Essaye, founder of Sevens Report Research. Saturday and Sunday could easily bring unfortunate news on the war front—and traders would rather be able to sell any recent winnings at Friday’s earlier prices than wait for a potentially lower price at Monday’s open. In 2014, Pavel Durov fled the country after allies of the Kremlin took control of the social networking site most know just as VK. Russia's intelligence agency had asked Durov to turn over the data of anti-Kremlin protesters. Durov refused to do so.
from es

Telegram Addis Standard Amharic
FROM American