#እስራኤል ከ #ኢራን ጋር የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ደረሰች፤ ትራምፕ ሁለቱም አገራት ስምምነቱን እንዳይጥሱት አሳሰቡ
የ #አሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በእስራኤል እና በኢራን መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት "አሁን በሥራ ላይ ነው" ሲሉ ገልጸው ሁለቱም አገራት ስምምነቱን እንዳይጥሱት አሳስበዋል።
የትራምፕን ንግግር ተከትሎ ከሰዓታት በኋላ የእስራኤል መንግሥት የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ መደረሱን ያረጋገጠ ሲሆን፤ ስምምነቱ ላይ ማንኛውም አይነት ጥሰት ቢያጋጥም አጸፋዊ ምላሽ እንደሚሰጥ አስጠንቅቋል።
ኢራን በበኩሏ ቀደም ሲል ጥቃቷን የምታቆመው እስራኤልም ጥቃቷን የምታቆም ከሆነ ብቻ እንደሆነ ተናግራ ነበር።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ኢራን በእስራኤል ላይ ሌሊቱን በፈጸመችው ጥቃት አራት ሰዎች መሞታቸውን እስራኤል አስታውቃለች። በአንጻሩ በቴህራን የሚገኙ የመንግሥት መገናኛ ብዙኃን ደግሞ የተኩስ አቁም ስምምነቱ ወደ ሥራ ከመግባቱ በፊት "የመጨረሻው የሚሳኤል ምት" መካሄዱን ዘግበዋል።
በተመሳሳይ ቴህራንም ሌሊቱን ከፍተኛ ጥቃት የደረሰባት ሲሆን አንድ ነዋሪ "የድንጋጤ ስሜት ተሰምቶኝ ነበረ" ሲሉ ገልጸዋል።
ይህ የተገለጸው ኢራን በሳምንቱ መጨረሻ በኒውክሌር ተቋሞቿ ላይ ለደረሰው ጥቃት የአጸፋ ምላሽ በመስጠት በኳታር በሚገኝ የአሜሪካ የጦር ሰፈር ላይ ሚሳኤሎችን ካስወነጨፈች በኋላ ነው ሲል ቢቢሲ ዘግቧል። ኳታር ሁሉም ሚሳኤሎች መመከት መቻላቸውን ገልጻለች።

group-telegram.com/AddisstandardAmh/5961
Create:
Last Update:

BY Addis Standard Amharic

Share with your friend now: