Telegram Group & Telegram Channel
በአዋሽ ፈንታሌ ወረዳ ፤ በሳቡሬ ቀበሌ የሚገኙ ሁለት ት/ቤቶች በመሬት መንቀጥቀጥ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

ትምህርት ቤቶቹ ዑንጋይቱ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት እና ሳቡሬ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ናቸው።

የወረዳው ከተማ ልማት ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት እንዳለው ፥ ዑንጋይቱ  የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ካሉት 12 የመማሪያ ክፍሎች ስድስቱ ፤ ሳቡሬ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ካሉት 16 ክፍሎች ስምንቱ መስኮታቸው ረግፏል ፤ ግድግዳቸው የመሰንጠቅና የመፍረስ አደጋ ደርሶበታል፣ ወለላቸውም ሰርጓል።

የዑንጋይቱ ት/ቤት ፤ በመሬት መንቀጥቀጡ ምክንያት በመማሪያ ክፍሎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ከደረሰ በኋላ ተማሪዎችን በዛፍ ስር እና ድንኳን ውስጥ ሲያስተምር ነበር።

ማክሰኞ ታህሳስ 22 ቀን 2017 ዓ/ም ጠዋት 2፡30 የመሬት መንቀጥቀጡ በባሰ ሁኔታ በመከሰቱ  ተማሪዎች እና መምህራን በድንጋጤ ት/ቤቱን ለቀው ወጥተዋል ተማሪዎች  ከዚያ በኋላ አልተመለሱም።

ትምህርት ቤቱ ወላጆቻቸውን ጠርቶ ካነጋገረ በኋላ ወልጆች " ልጆቻችን አብረውን ቢቆዩ ይሻለናል " ስላሉ የመማር ማስተማር ሂደቱ ተቋርጧል።

በወረዳው ከሚገኙት 6 ቀበሌዎች በአራቱ ላይ የመሬት መንቀጥቀጡ በተደጋጋሚ መከሰቱን ተከትሎ ነዋሪዎችን ወደተሻሉ አካባቢዎች የማስፈር ስራ እየተሰራ ነው ተብሏል።

በሌላ በኩል ፥ በሃንሩካ ወረዳም በመሬት መንቀጥቀጥ ምክንያት በትምህርት ቤት ላይ ጉዳት ደርሷል።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እና የአፋር ክልል ትምህርት ቢሮ ነው።

@tikvahethiopia
😭432115🙏59🕊42😢33👏18🤔16😱15

group-telegram.com/tikvahethiopia/93450
Create:
Last Update:

BY TIKVAH-ETHIOPIA

Share with your friend now:
group-telegram.com/tikvahethiopia/93450

View MORE
Open in Telegram

Telegram | DID YOU KNOW?

Date: |

Anastasia Vlasova/Getty Images To that end, when files are actively downloading, a new icon now appears in the Search bar that users can tap to view and manage downloads, pause and resume all downloads or just individual items, and select one to increase its priority or view it in a chat. For example, WhatsApp restricted the number of times a user could forward something, and developed automated systems that detect and flag objectionable content. Under the Sebi Act, the regulator has the power to carry out search and seizure of books, registers, documents including electronics and digital devices from any person associated with the securities market. "There are a lot of things that Telegram could have been doing this whole time. And they know exactly what they are and they've chosen not to do them. That's why I don't trust them," she said.
from hk

Telegram TIKVAH-ETHIOPIA
FROM American