group-telegram.com/Yemankiya_Dewel_Eth/1234
Last Update:
""ሞተረኛው ቶማስ "" ሞተረኛው ቶማስ ከከተማ እሩቅ የሆነና አዲስ የተተከለ ቤተክርስቲያን ጉባኤ አዘጋጅቶ ሲጠራን፣በሞተሩ ቀድሞ እየበረረ ሄዶ፣ ቦታውን በማየት ማታ ላይ ቦታው ግር ብሎ እንዳይጠፋንና፣ከእግዚአብሔር ጉባኤ እንዳንዘገይ መንገድ ይመራናል።ቤቱን ቤተሰቡን ሥራውንና የራሱን ነገር ትቶ ባለውና በተሰጠው ጸጋ ቤተክርስቲያንን ያገለግላል። ራሳቸውን ሳይሰጡ V8 ከሚሰጡ ባዕለጠጎች ይልቅ፣ እራሱን ሳይሰስትና ሳይታበይ ለቤተክርስቲያን አገልግሎት ያቺን ነዳጅ እንኳን አስታውሰን እንሙላልህ ሳንለው እየዞረ ቤተክርስቲያንን የሚያገለግልባት የቶማስ ሞተር ትበልጣለች።ይሄ ምድርን እንኳን ለመርገጥ የማይደፍር፣ ሰውን ቀና ብሎ የማያይ፣ድህነቱና ጎስቋላ ኑሮው ማህተብ ያላስፈቱት፣ትሁቱ፣ተዋህዶ ቤቱ፣ፍቅር ሕይወቱ፣ደግነት ሀብቱ፣የወጣት ምሳሌ፣ተወዳጅ በቦሌ፣የሆነው ቶማስ ምኑ ይታሰራል።በእውነት የዚህ ልጅ ትልቁ በደል አጠገቤ ቆሞ እግዚአብሔርን ማገልገሉ ነው።ታድኖ እንዲያዝ ያደረገው፣ ፓሊስ ጣቢያ ያሳደረው፣ችሎት ፊት ያቆመው። እንዲህ ያሉ ለቤተክርስቲያን እና ለሀገር የሚጠቅሙ ጨዋ ባለ ማህተቦችን ከአጠገቤ ለይቶ በማሰር የሚታሰር ወንጌል የለም።አሁንም እላለሁ አጠገቤ የቆሙ ወንድሞች እንኳን በመታሰራቸው በመሞታቸውም ቢሆን ለቤተክርስቲያን ክብር ከመቆምና ከመጮህ ወደኃላ አልልም። ስለዚህ የታሰሩትን የቤተክርስቲያን ልጆች ፍቱልን!!!!!! (ይህ የምትመለኩቱት ምስል፣ ቶማስ ወንድሙ ሞቶበት ለቅሶ ላይ እያለ፣ የቤተክርስቲያን እና የጉባኤው ናፍቆት አላስችልህ ብሎት ወደ ጉባኤ ሲመጣ የሚያሳይ ነው።) የሌሎች ታሳሪዎችን ማንነት ደግሞ በቀጣይነት እንመጣበታለን።
BY የማንቂያ ደወል / Yemankiya Dewel
Warning: Undefined variable $i in /var/www/group-telegram/post.php on line 260
Share with your friend now:
group-telegram.com/Yemankiya_Dewel_Eth/1234