" ' ህወሓት እና የትግራይ ህዝብ አንድ ናቸው ' የሚለው አመራሩ የሚጠቀምበት ማጭበርበሪያ ነው " - አቶ ጌታቸው ረዳ
" ህወሓት እና የትግራይ ህዝብ አንድ ናቸው " የሚለው አመራሩ የሚጠቀምበት ማጭበርበሪያ እንደሆነ የቀድሞ የትግራይ ጊዜዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንትና የአሁኑ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ ተናገሩ።
ይህ የተናገሩት ከ ' ፋና ቴሌቪዥን ' ጋር በነበራቸው ዘልግ ያለና ጠንካራ ሃሳቦች በሰነዘሩበት ቃለምልልስ ነው።
በህወሓት ውስጥ ያለውን አመራር " ወደጠባብ ቡድናዊ ፍላጎት ብቻ ትኩረት ያደረገ ፤ የህዝብ አጀንዳ አጀንዳው ያልሆነ ፤ ምን እንደሚል እንኳን ሳይታወቅ ' እኔ ያልኩት ብቻ ነው ትክክል ' በሚል ከእንቅልፍ ባኖ በተነሳ ቁጥር የሚመጡለት ጉዳዮችን የህዝብ አጀንዳ እያስመሰለ የሚያደናግር ፣ በህዝብ ስም እየማለ እየተገዘተ የህዝብን አጀንዳና ጉዳይ ወደጎን ትቶ የራሱን ጥቅም ወደማሳደድ የመጣ ነው " ብለዋል።
" ይሄን ውጭ ወጥቼ እገሌ እገሌ ብዬ ለመውቀስ አይደለም ሁላችንም ባለፍንበት ሂደት የህዝብ አጀንዳ ከማስቀመጥ አኳያ ምን አደረግን ? ብለን መጠየቅ አለብን " ሲሉ ተናግረዋል።
አቶ ጌታቸው ረዳ ፥ " ህወሓት እና የትግራይ ህዝብ አንድ ናቸው " የሚለው የአመራሩ ማጭበርበሪያ እንደሆነ ገልጸዋል።
ይህን ማጭበርበሪያ አመራሩ የሚጠቀምበት ከስርቆት፣ ከሌሎች በመንግሥት ስልጣን ላይ ተኩኖ ከሚፈጸሙ በደሎች ተጠያቂ ላለመሆን እንደሆነ አስረድተዋል።
በዚህ ማጭበርበሪያ " የሚሰራቸውን ስራዎች በሙሉ ከህዝቡ ይሁንታ በመነጨ የሚሰራቸው አድርጎ ለማሳመን ይሞክራል " ሲሉም ተደምጠዋል።
" አመራሩ እራሱን የህዝቡ ወኪል አድርጎ፣ ህዝብም እንዲሰግድለት አድርጎ ፣ ህብዙ አንድም አይነት የተቃውሞ ምልክት እንዳያሰማ አፍኖ የስርቆት አጀንዳ ውስጥ በደምብ ተነክሮ ግን ደግሞ ህወሓት እና ድርጅት አንድ ስለሆንን ብሎ በዛ ማጭበርበሪያ እራሱን ነጻ ለማድረግ ይሞክራል " ብለዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia

❤462👏124😡110🤔67🙏25🕊22😢14😱13😭9🥰8💔3
group-telegram.com/tikvahethiopia/96706
Create:
Last Update:

BY TIKVAH-ETHIOPIA

Share with your friend now:
group-telegram.com/tikvahethiopia/96706