Telegram Group & Telegram Channel
' አሻም ' ስያሜውን እንዲቀይር በፍርድ ቤት ለምን ተወሰነ ?

“ ተከሳሽ ' አሻም ' ሚለውን የንግድ ምልክት  መጠቀም ማቆም አለበት በማለት ተወስኗል ” - ፍርድ ቤት

አሻም ቴሌቪዝን ሲጠቀምበት የነበረውን  አሻም የሚለውን ስያሜ መጠቀም አንዲያቆምና እስከ ጥቅምት 10 ቀን 2017 ዓ/ም እንዲያሳውቅ በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኅን ባለሥልጣን በኩል ማሳሰቢያ እንደተሰጠው ቲክቫህ ኢትዮጵያ ባለሥልጣኑ ይፋ ካደረገው ደብዳቤ ተረድቷል።

ባለሥልጣኑ ተቋሙ የስም ቅያሬ እንዲያደርግ ያሳሰበው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፍ/ብሔር ምድብ ችሎትና የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የወሰኑት ውሳኔን መሠረት በማድረግ ነው፡፡

የስም ቅያሬ ማሳሰቢያው ምንን መሠረት ያደረገ ነው ?

የትዕዛዙ መሠረት አሻም ቴሌቪዥን በብስራት ኤፍ ኤም 101.1 ሬድዮ ላይ በሚተላለፈው “ አሻም  ” የተሰኘ ፕሮግራም ባቀረበበት የክስ መሠረት ነው።

ቲክቫህ ኢትየጵያ የተመለከታቸው ሰነዶች የስም ቅያሬ ጉዳዩ በይግባኝ እስከ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተኪዶበት ከሳሽ ያቀረቡትን ክስ አሸንፈው ፤ የካሳ ጉዳይ ተጣርቶ ወደፊት እንደሚወሰን ፤ ነገር ግን የቴሌቪዥን ጣቢያው ' አሻም ' የሚለውን ስም መጠቀም እንዲያቆም ውሳኔ የተሰጠበት መሆኑን ያስረዳሉ፡፡

በ2014 ዓ/ም የተጻፈው የፍርድ ቤት ሰነድ ከሳሽ ' አሻም ' የሚለውን ስያሜ በብስራት ኤፍኤም 101.1 እንደሚጠቀምበት፣ ለዚህም ከኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለሥልጣን የምስክር ወረቀት እንዳገኘበት፣ በንግድ ምልክቱ የመጠቀምና ሌሎች እንዳይጠቀሙ የመከልከል መብት በአዋጅ እንደተሰጠው መግለጹን ይተነትናል፡፡

“ ተከሳሽ የከሳሽን ፈቃድ ሳያገኝ እንዲሁም ፈቃድ ሳይጠቅይቅ ' አሻም ' በሚለው በከሻስ የተመዘገበ የንግድ ምልክት በመጠቀም የቴሌቪዥን ጣቢያ ከፍቶ ስርጭት ጅምሯል ” ይላል ሰነዱ።

ከሳሽ ተከሳሹን፣ “ ተከሳሽ የንግድ ምልክት መጠቀሙ ሆን ብሎ ያለአግባብ ለመበልጸግ የተደረገ ተግባር ነው ይህም ተግባር ያልተገባ የንግድ ውድድር ከመሆኑም ባሻገር በከሳሽ ንግድ ስራ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ይገኛል ” ሲልም ከሶታል፡፡

በዚህም ' አሻም ' የሚለውን የከሳሽን የንግድ ምልክት በቴሌቪዝን ጣቢያ ስያሜነት መጠቀም እንዲያቆም  ተከሽ የከሳሽን የንግድ ምልክት እየተጠቀመ በመቆየቱ ከሳሽ ላይ በደረሰው ጉዳት 1 ሚሊዮን ብር እንዲከፈል እንዲወሰን ሲጠይቅ ቆይቷል፡፡

ተከሳሽ (አሻም ቴሌቪዥን) በበኩሉ፣ ከ2009 ጀምሮ አሻም ሚዲያ ትሬዲንግ በሚል ስያሜ በቴሌቪዥን ማሰራጨት ሥራ እየተጠቀመበት እንደሆነ፣ እውቅና እንዳገኘበት በመግለጽ፣ “ ከሳሽ እኔን ሊከሰኝ የሚያስችለው የህግና የማስረጃ ድጋፍ የለውም ” ሲል አጸፋ መስጠቱን ሰነዱ ያስረዳል፡፡

' አሻም ' የሚለውን ስያሜ ያወጣው “ በህጋዊ መንገድ ከንግድ ቢሮ ” ክፍያ በመፈጸም መሆኑን፣ ቢሮው የሚጠቀምበት ሌላ ሰው ያለመኖሩን አጣርቶ የንግድ ስያሜን እንዲጠቀምበት እንደፈቀደለት በመግለጽ ምላሽ መስጠቱና ሌሎች ጉዳዮች በሰነዱ ተብራርተዋል፡፡

ጉዳዩ በእንዲህ አይነት በርካታ ሂደቶች ከተደረጉ በኋላም ተከሳሽ አሻም የሚለውን ስያሜ እንዲያቆም፣ ንግድ ባንክ በፍርድ ባለእዳ ስም የተከፈተ ሂሳብ ቁጥር ካለ እስከ 292 ሺሕ 850 ብር እንዲያግድ ውሳኔ ትዕዛዝ መሰጠቱ ታውቋል፡፡

የፍርድ ቤት ውሳኔው የክርክር ሂደቱን በዝርዝር ካስረዳ በኋላ፣ “ ተከሳሽ አሻም የሚለውን የንግድ ምልክት መጠቀም ማቆም አለበት በማለት ወስኗል ” ይላል።

ይህንንም የፍርድ ቤት ውሳኔ እንዲያስፈጽም የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኅን ባለሥልጣን ታዟል።

(ይህ በከፊል የቀረበ መረጃ ሲሆን፣ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ደርሶት የተመለከተው ሙሉ የፍርድ ቤት ሰነድ ከላይ ተያይዟል)

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
😡1.06K307🤔113🥰82👏63😢49🙏48🕊48😭33😱23

group-telegram.com/tikvahethiopia/91322
Create:
Last Update:

BY TIKVAH-ETHIOPIA

Share with your friend now:
group-telegram.com/tikvahethiopia/91322

View MORE
Open in Telegram

Telegram | DID YOU KNOW?

Date: |

"There are a lot of things that Telegram could have been doing this whole time. And they know exactly what they are and they've chosen not to do them. That's why I don't trust them," she said. Lastly, the web previews of t.me links have been given a new look, adding chat backgrounds and design elements from the fully-features Telegram Web client. At this point, however, Durov had already been working on Telegram with his brother, and further planned a mobile-first social network with an explicit focus on anti-censorship. Later in April, he told TechCrunch that he had left Russia and had “no plans to go back,” saying that the nation was currently “incompatible with internet business at the moment.” He added later that he was looking for a country that matched his libertarian ideals to base his next startup. The regulator said it had received information that messages containing stock tips and other investment advice with respect to selected listed companies are being widely circulated through websites and social media platforms such as Telegram, Facebook, WhatsApp and Instagram. On February 27th, Durov posted that Channels were becoming a source of unverified information and that the company lacks the ability to check on their veracity. He urged users to be mistrustful of the things shared on Channels, and initially threatened to block the feature in the countries involved for the length of the war, saying that he didn’t want Telegram to be used to aggravate conflict or incite ethnic hatred. He did, however, walk back this plan when it became clear that they had also become a vital communications tool for Ukrainian officials and citizens to help coordinate their resistance and evacuations.
from it

Telegram TIKVAH-ETHIOPIA
FROM American