Telegram Group & Telegram Channel
" ' ህወሓት እና የትግራይ ህዝብ አንድ ናቸው ' የሚለው አመራሩ የሚጠቀምበት ማጭበርበሪያ ነው " - አቶ ጌታቸው ረዳ

" ህወሓት እና የትግራይ ህዝብ አንድ ናቸው " የሚለው አመራሩ የሚጠቀምበት ማጭበርበሪያ እንደሆነ የቀድሞ የትግራይ ጊዜዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንትና የአሁኑ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ ተናገሩ።

ይህ የተናገሩት ከ ' ፋና ቴሌቪዥን ' ጋር በነበራቸው ዘልግ ያለና ጠንካራ ሃሳቦች በሰነዘሩበት ቃለምልልስ ነው።

በህወሓት ውስጥ ያለውን አመራር "  ወደጠባብ ቡድናዊ ፍላጎት ብቻ ትኩረት ያደረገ ፤ የህዝብ አጀንዳ አጀንዳው ያልሆነ ፤ ምን እንደሚል እንኳን ሳይታወቅ ' እኔ ያልኩት ብቻ ነው ትክክል ' በሚል ከእንቅልፍ ባኖ በተነሳ ቁጥር የሚመጡለት ጉዳዮችን የህዝብ አጀንዳ እያስመሰለ የሚያደናግር ፣ በህዝብ ስም እየማለ እየተገዘተ የህዝብን አጀንዳና ጉዳይ ወደጎን ትቶ የራሱን ጥቅም ወደማሳደድ የመጣ ነው " ብለዋል።

" ይሄን ውጭ ወጥቼ እገሌ እገሌ ብዬ ለመውቀስ አይደለም ሁላችንም ባለፍንበት ሂደት የህዝብ አጀንዳ ከማስቀመጥ አኳያ ምን አደረግን ? ብለን መጠየቅ አለብን " ሲሉ ተናግረዋል።

አቶ ጌታቸው ረዳ ፥ " ህወሓት እና የትግራይ ህዝብ አንድ ናቸው " የሚለው የአመራሩ ማጭበርበሪያ እንደሆነ ገልጸዋል።

ይህን ማጭበርበሪያ አመራሩ የሚጠቀምበት ከስርቆት፣ ከሌሎች በመንግሥት ስልጣን ላይ ተኩኖ ከሚፈጸሙ በደሎች ተጠያቂ ላለመሆን እንደሆነ አስረድተዋል።

በዚህ ማጭበርበሪያ " የሚሰራቸውን ስራዎች በሙሉ ከህዝቡ ይሁንታ በመነጨ የሚሰራቸው አድርጎ ለማሳመን ይሞክራል " ሲሉም ተደምጠዋል።

" አመራሩ እራሱን የህዝቡ ወኪል አድርጎ፣ ህዝብም እንዲሰግድለት አድርጎ ፣ ህብዙ አንድም አይነት የተቃውሞ ምልክት እንዳያሰማ አፍኖ የስርቆት አጀንዳ ውስጥ በደምብ ተነክሮ ግን ደግሞ ህወሓት እና ድርጅት አንድ ስለሆንን ብሎ በዛ ማጭበርበሪያ እራሱን ነጻ ለማድረግ ይሞክራል " ብለዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
462👏124😡110🤔67🙏25🕊22😢14😱13😭9🥰8💔3

group-telegram.com/tikvahethiopia/96706
Create:
Last Update:

BY TIKVAH-ETHIOPIA

Share with your friend now:
group-telegram.com/tikvahethiopia/96706

View MORE
Open in Telegram

Telegram | DID YOU KNOW?

Date: |

Under the Sebi Act, the regulator has the power to carry out search and seizure of books, registers, documents including electronics and digital devices from any person associated with the securities market. The Russian invasion of Ukraine has been a driving force in markets for the past few weeks. Anastasia Vlasova/Getty Images The Securities and Exchange Board of India (Sebi) had carried out a similar exercise in 2017 in a matter related to circulation of messages through WhatsApp. It is unclear who runs the account, although Russia's official Ministry of Foreign Affairs Twitter account promoted the Telegram channel on Saturday and claimed it was operated by "a group of experts & journalists."
from ms

Telegram TIKVAH-ETHIOPIA
FROM American