group-telegram.com/AddisstandardAmh/5870
Create:
Last Update:
Last Update:
ዜና፡ በፍቅር አጋሩ ሞት ተጠርጥሮ በእስር ላይ የነበረው ድምጻዊ #አንዷለም ጎሳ ከሶስት ወራት እስር በኋላ ተፈታ
የፍቅር አጋሩ በሆነችው ቀነኒ አዱኛ ሞት ተጠርጥሮ በእስር ላይ የነበረው ድምጻዊ አንዷለም ጎሳ ከሶስት ወር እስር በኋላ ትናንት ሰኔ 3 ቀን 2017 ዓ/ም መፈታቱን ጠበቃው ለአዲስ ስታንዳርድ ገለጹ።
የድምጻዊው ጠበቃ ሊበን አብዲ እንደገለጸው፤ አንዷልም በ50 ሺህ ብር ዋስ ከእስር የተለቀቀው፤ ፖሊስ ሲያደረግ የነበረውን ምርመራ ካጠናቀቀ በኋላ አቃቤ ህግ በተሰጠው ጊዜ ውስጥ ክስ ባለመመስረቱ ነው።
ይሁን እንጂ መዝገቡ እስካሁን ሙሉ በሙሉ አለመዘጋቱን ጠበቃው ተናግረዋል። “አቃቤ ህግ በተሰጠው ጊዜ ውስጥ ክስ አልመሰረትኩም ወይም የፖሊስ ምርመራ ውጤት ክስ ለመመስረት በቂ አይደለም ብሎ ጉዳዩን አልዘጋውም፤ ስለዚህ የአቃቤ ህግ ውሳኔ እየተጠበቀ ነው” ብሏል።
ተጨማሪ ያንብቡ፡ https://addisstandard.com/Amharic/?p=8066
BY Addis Standard Amharic

Share with your friend now:
group-telegram.com/AddisstandardAmh/5870