group-telegram.com/NatnaelMekonnen21/45671
Last Update:
ለ’’ሐገር እና ለህዝብ ህልውና ተቆርቋሪዎች ስብስብ’’
የሚለው ስማችሁ አልከበዳችሁም ወይ? 😂 ከጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ ለተሰብሳቢዎች የቀረበ ጥያቄ ነው !
ርዕዮት አለሙን ረዘም ላለ ግዜ አውቃታለሁ። ከነልዩነታችን ከማከብራቸው ሰዎች መሃከል አንዷ ነች። ብዙ የማልቀበላቸውን ሃሳቦች ስታነሳ አይቻለሁ። ነገር ግን አንድም ቀን ለነዋይ ብላ እውነትን ስትሸቅጥ አይቻት አላውቅም። አንድም ቀን ያላመነችበትን ነገር ሰውን ለማስደሰት ስትናገር አይቻት አላውቅም። አንድም ቀን በስመ “ተቃውሞ” ሐገሯ ላይ ስትቆምርና የባንዳ ስራ ስትሰራ አይቻት አላውቅም።
መንግስትን መቃወም መብት ነው። አንድን መንግስት ሁሉም ሰው ሊደግፈው አይችልም። ነገር ግን ገና ለገና መንግስትን ጠላሁ ብሎ በኢትዮጵያ ጥቅም ላይ የሚቆምረው ነው የኔ ጠላት። ርዕዮት ብዙ መስዋእትነት የከፈለች ሴት ነች። ወያኔ አንድ ቤት ውስጥ ለአመታት ከአእምሮ በሽተኛ ጋር አስሯት፣ ብዙ ኢሰብአዊ በደል ፈፅሞባት ሊሰብራት ያልቻለ ፅኑ ሴት ነች። ከሐገር እንኳን ለመውጣት እንደሌላው አልቅሳ ተለማምጣና ያላመማትን አመመኝ ብላ ሳይሆን በቄስና በዘመድ አዝማድ ተለምና ከሐገሯ የወጣች ሴት ነች።
ከርዕዮት ታናሽ እህት ጋር ቅርብ የሆነ የቤተሰባዊ አይነት የሚመስል ግንኙነት ስለነበረን አብዛኛውን የርዕዮትን ታሪክ አውቃለሁ በግዜው ብዙ ነገር ስናደርግም ነበር ርዕዮት ከወጣችም በኋላ አሜሪካ እግሯ እንደረገጠ ህመሟ ጨርሶ ሳይድን ወደኤርትራ በርሃ ካልወረድኩ ያለች ሴት ነች።
I wish ሐገሯ ገብታ ከነልዩነቷ በጋዜጠኝነትም ሆነ በመረጠችው ሙያዋ ሐገሯንና ህዝቧን ብታገለግል ምኞቴ ነው። እሱን ማድረግ ባትችል እንኳን ስብእናዋን ስለማውቀው ባለችበት አክባሪዋ ነኝ።
ለማንኛውም ከስር ያለውን ቪዲዮ ሰዎች ልከውልኝ ለማስታወስ ያክል ነው የፃፍኩት። ሃሳቡ ከኔ ተለየም አልተለየም ኢትዮጵያን የሚወድልኝንና በሐገሩ ብሔራዊ ጥቅም የማይደራደርን ሁሉ አከብራለሁ።
ልዩነት ለዘላለም ይኑር ኢትዮጵያዊነት ይለምልም #Ethiopiaዬ ለዘላለም ትኑር
BY Natnael Mekonnen
Warning: Undefined variable $i in /var/www/group-telegram/post.php on line 260
Share with your friend now:
group-telegram.com/NatnaelMekonnen21/45671