Telegram Group & Telegram Channel
#FreeNaima

" ገንዘቡን ካላገኘን በቀር እንዳንደውልላቸው አስጠንቅቀውናል። በጣም ተጨንቀናል " - ቤተሰብ

በሊቢያ ታጣቂዎች በርካታ ስደተኞችን አግተው የማሰቃየት ድርጊት እየፈጸሙባቸው ይገኛል።

ከእነዚህ ታጋቾች መካከል የሀገራችን ልጅ ነሒማ ጀማል አንዷ ናት።

ነሒማ ከኦሮሚያ ክልል፤ ሻሸመኔ በመሰደድ ነው ወደ ሊቢያ ያቀናችው።

' ሬፊዩጂስ ኢን ሊቢያ ' የተሰኘው ተቋም በኤክስ ገፁ እንዳስታወቀው ነሒማ እና ሌሎች ስደተኞች ' ኩፍራ ' በምትባለው የሊቢያ ግዛት በታጣቂዎች ቁጥጥር ሥር ይገኛሉ።

ነሒማ በፎቶዎቹና በቪዲዮዎች ላይ አፏ በጨርቅ ተለጉሞ ስቃይ ሲደርስባት ትታያለች።

የነሒማ ጀማል ቤተሰቦች ቪዲዮዎች እና ፎቶዎች ተልኮላቸው የማስለቀቂያ ገንዘብ እንዲከፍሉ ማስጠንቀቂያ ደርሷቸዋል።

የነሒማ እህት ኢፍቱ ጀማል ፤ ነሒማ ከ8 ወራት በፊት ከሻሸመኔ ከተማ የ11ኛ ክፍል ትምህርቷን አቋርጣ ወደ ሊቢያ እንደተሰደደች ለቢቢሲ አማርኛ አገልግሎት ተናግራለች።

" ፎቶዎች እና ቪዲዮዎች ይልኩልናል። ስትሰቃይ ያሳዩናል። የድምፅ መልዕክትም ልከውልናል። እህታችን ' ገንዘብ ላኩላቸው ካልሆነ ይገድሉኛል ' ስትል ይሰማል " ስትል አስረድታችለች።

ነገር ግን ኢፍቱ እንደምትለው ቤተሰቡ አጋቾቹ የጠየቁትን ገንዘብ የመላክ አቅም የለውም።

' ሬፊዩጂስ ኢን ሊቢያ ' የተባለው ሊቢያ የሚገኙ ስደተኞችን ጉዳይ የሚከታተለው ተቋም እንዳለው የ20 ዓመቷ ነሒማ ጀማል ባለፈው ግንቦት ሊቢያ ከገባች ከቀናት በኋላ ነው በታጣቂዎቹ እጅ ውስጥ የገባችው።

በቁጥጥር ሥር ከዋለች በኋላ ስቃይ ሲደርስባት እና ስትደበደብ የሚያሳዩ ፎቶዎች እና ቪዲዮዎች ለቤተሰቦቿ ተልከዋል።

ኢፍቱ እንደምትለው ቤተሰቡ የተጠየቀውን ገንዘብ ለማሰባሰብ እርዳታ ቢጠይቅም እስካሁን ድረስ ሊሞላላቸው አልቻለም።

ቤተሰቡ የነሒማን ድምፅ ከሰማ ሁለት ሳምንት እንዳለፈው እህቷ ተናገራለች።

" ገንዘቡን ካላገኘን በቀር እንዳንደውልላቸው አስጠንቅቀውናል። በጣም ተጨንቀናል " ስትል አክላለች።

' ሬፊዩጂስ ኢን ሊቢያ ' ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ስቃዩ እና ማስፈራራቱ እንደተጠናከረ እና ይህ ደግሞ ቤተሰቦች ላይ ከፍተኛ ጫና እያሳደረ እንደሆነ ገልጿል።

አጋቾቹ ለነሒማ ማስለቀቂያ የጠየቁት ገንዘብ 6 ሺህ ዶላር ነው።

የነሒማ ቤተሰብ ይህንን ሁሉ ገንዘብ ለማሰባሰብ የሚችለውን ሁሉ እያደረገ ይገኛል።

ለነሒማ ቤተሰብ የተላኩ ቪዲዮዎች በርካታ ስደተኞች በአሰቃቂ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኙ ያሳያሉ።

ነሒማ እጅና እግሯ ተጠፍሮ፤ አፏ በጨርቅ ታፍኖ ትታያለች። ስቃይ ሲደርስባት እና ደም በደም ሆና የሚያሳዩ ቪዲዮዎች እና ፎቶዎችም አሉ።

ድርጅቱ በለቀቃቸው ቪዲዮዎች እና ፎቶዎች ላይ ነሒማ ብቻ ሳትሆን 50 ገደማ ሌሎች የአጋቾቹ ሰለባዎች ከጀርባዋ ተደርድረው ይታያሉ።

የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች በሊቢያ እየተካሄደ ያለውን የባርነት ንግድ ዓለም ረስቶታል ሲሉ ዓለም አቀፉን ማኅበረሰብ እየወቀሱ ናቸው።

በእርስ በርስ ጦርነት እየታመሰች ወዳለችው ሊቢያ በስደት የተጓዙት ነሒማ እና ሌሎች ስደተኞች መጨረሻቸው ምን ሊሆን እንደሚችል አይታወቅም።

በርካታ ኢትዮጵያውያንና ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ስደተኞች ሕይወታቸውን ለመቀየር በሚል ወደ አውሮፓ በሚያደርጉት ጉዞ የሜዲቴራኒያን ባሕርን ከማቋረጣቸው በፊት ሊቢያን ይረግጣሉ።

መረጃው ከሪፊውጂስ ኢን ሊቢያና ቢቢሲ አማርኛ አገልግሎት ነው የተገኘው።

#FreeNaima

@tikvahethiopia
8😢2.58K😭1.24K246😡204🙏115🕊65🤔37😱27🥰23👏23

group-telegram.com/tikvahethiopia/93707
Create:
Last Update:

BY TIKVAH-ETHIOPIA

Share with your friend now:
group-telegram.com/tikvahethiopia/93707

View MORE
Open in Telegram

Telegram | DID YOU KNOW?

Date: |

As the war in Ukraine rages, the messaging app Telegram has emerged as the go-to place for unfiltered live war updates for both Ukrainian refugees and increasingly isolated Russians alike. You may recall that, back when Facebook started changing WhatsApp’s terms of service, a number of news outlets reported on, and even recommended, switching to Telegram. Pavel Durov even said that users should delete WhatsApp “unless you are cool with all of your photos and messages becoming public one day.” But Telegram can’t be described as a more-secure version of WhatsApp. Multiple pro-Kremlin media figures circulated the post's false claims, including prominent Russian journalist Vladimir Soloviev and the state-controlled Russian outlet RT, according to the DFR Lab's report. READ MORE Telegram boasts 500 million users, who share information individually and in groups in relative security. But Telegram's use as a one-way broadcast channel — which followers can join but not reply to — means content from inauthentic accounts can easily reach large, captive and eager audiences.
from no

Telegram TIKVAH-ETHIOPIA
FROM American