Telegram Group & Telegram Channel
ዜና: ሶማሊያ በህንድ ውቅያኖስ ዳርቻ #ለኢትዮጵያ የወደብ መዳረሻ ለመስጠት አያጤነቸ መሆኑ ተጠቆመ

#ሶማሊያ በህንድ ውቅያኖስ ዳርቻ ለጎረቤቷ ኢትዮጵያ የወደብ መዳረሻ ለመስጠት ከኢትዮጵያ ጋር እየተነጋገረች መኾኗን የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ደኤታ ዓሊ ሞሐመድ ኦማር መናገራቸው ተገለጸ።

ሁለቱ ሀገራት በጉዳዩ ዙሪያ አየመከሩ መሆናቸውን የጠቆሙት ሚኒሰተር ዴኤታው እስከ መጪው ሰኔ ወር የስምምነቱን ማዕቀፍ ለማጠናቀቅ እየተነጋገሩ ነው ማለታቸውን ከብሉንበርግ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

“ማዕቀፉ ምን አይነት ወደብ እንደሚሰጥ ውሳኔ ይሰጣል፣ በትክክል የትኛው የህንድ ውቅያኖስ ዳርቻ እንደሚሻል ምክረ ሀሳብ ያቀርባል እንዲሁም ለወደቡ ግንባታ አጠቃላይ ስለሚያስፈልገው የገንዘብ ወጭ የውሳኔ ሀሳብ ያቀርባል” ሲሉ ሚኒስትር ዴኤታው አመላክተዋል።

በጉዳዩ ዙሪያ አሰተያየት እነዲሰጡት የጠ/ሚኒስትር ጽ/ቤት ሴክረተሪ ብለኔ ስዩምን እንዲሁም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባዩ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው ያደረገው ሙከራ አለመሳካቱነ ብሉንበርግ በዘገባው አስታውቋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) ከቀናት በፊት ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ወደ ሞቃዲሹ ማቅናታቸው ይታወቃል፤ የካቲት 20 ቀን 2017 ዓ/ም ወደ ሶማሊያ ያመሩት ጠ/ሚ አብይ በሞቃዲሾ ቆይታቸው ከፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀመድ ጋር የፀጥታ ትብብርን በማጠናከር፣ የንግድ አጋርነት በማጠናከር እና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቶችን በማጠናከር ላይ ትኩረት ያደረገ ውይይት ማድረጋቸውን መዘገባችን ይታወሳል።

የአንካራውን ስምምነት ተከትሎ የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሃመድ በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ የመጡ ሲሆን በወቅቱ ከ/ሚ አብይ አህመድ ጋር ውይይት በማድረግ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን ለመመለስ መስማማታቸውን ይታወሳል።

group-telegram.com/AddisstandardAmh/5423
Create:
Last Update:

BY Addis Standard Amharic

Share with your friend now:
group-telegram.com/AddisstandardAmh/5423

View MORE
Open in Telegram

Telegram | DID YOU KNOW?

Date: |

"Like the bombing of the maternity ward in Mariupol," he said, "Even before it hits the news, you see the videos on the Telegram channels." As such, the SC would like to remind investors to always exercise caution when evaluating investment opportunities, especially those promising unrealistically high returns with little or no risk. Investors should also never deposit money into someone’s personal bank account if instructed. Ukrainian President Volodymyr Zelensky said in a video message on Tuesday that Ukrainian forces "destroy the invaders wherever we can." Perpetrators of these scams will create a public group on Telegram to promote these investment packages that are usually accompanied by fake testimonies and sometimes advertised as being Shariah-compliant. Interested investors will be asked to directly message the representatives to begin investing in the various investment packages offered. The Securities and Exchange Board of India (Sebi) had carried out a similar exercise in 2017 in a matter related to circulation of messages through WhatsApp.
from us

Telegram Addis Standard Amharic
FROM American