group-telegram.com/bilalmedia2/6824
Last Update:
ለነፀብራቅ 1 ፊት ብቻ ያለው የሚመስልህ ወንድሜ ሆይ ...... ጨረቃ ግማሽ አካሉ በጥላ ስር ሲደበቅ በዛ ጨረቃ ማስተንተንን ምክረህ ታውቃለህ 🧐 ??
በኢስላም ውስጥ ሴቶች ለንግግር ማማር የተደረጉ ጌጦች አይደሉም 🙄 ፤ እንደዉም ሴቶች የተፈጠሩት በፍጥረተ አለሙ ላይ ለሚዛናዊነት ሚስጥር እንዲሆኑ ነው 😌 ። ምድር ያለ ዉሀ ምድረ በዳ እንደምትሆነው ሁላ ህይወትም ያለ ሴት መዋዠቅ እና ወና መሆን ነው 🥺 ።
ሴት ማለት ያለሷ ትርጉም ማይሟላበት የሆነች ድብቅ ፊደል ናት 😇 ፣ እሷም ያለሷ ህይወት ማይቆም የሆነች ድብቅ እስትንፋስ ናት 🥹፣ ተራው ሰው ማያያት የሆነች መድረሳ ናት ፤ ነገር ግን በጨለማ እንኳን መንገዳቸው የሚያውቁ የሆኑ ትውልዶችን አንፃ የምታስመርቅ ተቋም ናት 🤩።
ኢስላም ሴትን በስም ብቻ አላላቃትም ፣ እንደውም በአይን የማይታይ የሆነ እና በአቅል ብቻ ሊታይ የሚችል ድርሻን በኢስላም ሰጥቷቷል 😊 ።ሴት ማለት ሰይፎች በሚወድቁ ጊዜ ያለች ሰላማዊ መሸሸጊያ ናት ❤️ ። ውለታዎች በሚረሱ ጊዜ ያለች የማትረሳ ትዝታ ናት ❤️🩹 ፣ እናም ደግሞ የማይሰማ ነገር ግን ትውልድን ማንቀሳቀስ የሚችል ድምፅ ናት ።
ሴት በኢስላም ውስጥ ድብቅ ሚዛን ናት እሷ ከተዘነበለች ሁሉ ነገር ሲያዘነብል እሷ ቀጥ ካለች ደግሞ ሁሉ ነገር ቀጥ ይላል 😊።
ይህንንም በኢስላም ውስጥ ያለን የሴት ሚና ማየት ያልቻለ ምንጊዜም በሴት ላይ ጉድለትን ብቻ ይመለከታል 😢 ። ምክንያቱም የልቡ አይን እስካሁን አልተከፈተችምና 🥲.........
ሴት እናት ፣ እህት ፣ ልጅ ፣ ሚስት ፣ አያት እናም የማህበረሰብ መፍለቂያ ጭምር ናት 😍 ።
ሴትን እንዲው እያሞገስጓት ሳይሆን ጥልቅ ከሆነው የሚስጥር ባህሯ በማንኪያ ልንካ ብዬ ነው 🥰 ።
BY ቢላል ሚዲያ
Warning: Undefined variable $i in /var/www/group-telegram/post.php on line 260
Share with your friend now:
group-telegram.com/bilalmedia2/6824