" ከኢትዮጵያ ውጪም ሃብት ፈጥረን ወደ ሌሎች ሃገሮች እና ገበያዎች በመሄድ እሴቶችን ጨምረን ገቢ የማግኘት እቅድ አለን " - ኢትዮ ቴሌኮም
ኢትዮ ቴሌኮም እ.አ.አ ከ 2022/23-2025 ሲመራበት የነበረው ሊድ ግሮውዝ ስትራቴጂ ባሳለፍነው በጀት አመት ያጠናቀቀ መሆኑ ይታወቃል።
ስትራቴጂ እቅዱን ማጠናቀቁን ተከትሎ ለሚቀጥሉት ሦስት አመታት የሚመራበትን ስትራቴጂክ እቅድ በዛሬው ዕለት ይፋ አድርጓል።
ከ 2018 እስከ 2020 ዓም የሚቆየው ስትራቴጂክ እቅድ "አድማስ" የሚል ስያሜ የተሰጠው ሲሆን ማሳካት ስላሰበው ዝርዝር ጉዳዮች ዋና ስራ አስፈጻሚዋ ፍሬህይወት ታምሩ ማብራርያ ሰጥተዋል።
በማብራሪያቸው " ኢትዮ ቴሌኮም በሚቀጥሉት ሦስት አመታት ከኢትዮጵያ ገበያ ውጪ ሃብት በመፍጠር ወደ ሌሎች ሃገሮች እና ገበያዎች በመሄድ እሴቶችን በመጨመር ገቢ የማግኘት እቅድ አለን" ብለዋል።
ኢትዮ ቴሌኮም በቀጣዩ አድማስ 2018 ዓም እስከ 2020 ዓም ስትራቴጂ እና የ 2018 ዓም የሥራ እቅድ ለማሳካት ያቀደው ዋና ዋና ጉዳዮች ምንድን ናቸው ?
° በሶስት ዓመታት ውስጥ 842.3 ቢሊዮን ብር ገቢ ለማግኘት ያቀደ ሲሆን ከቀደመው እና ከተጠናቀቀው የሊድ ግሮውዝ ስትራቴጂ ዘመን ገቢ ጋር ሲነጻጸር የ 154 በመቶ አድገት እንደሚኖረው ገልጿል።
° የገቢ እድገት ከቴሌኮም፣ ከፊንቴክ፣ ከደንበኛ መጠቀሚያ መሳሪያዎች ሽያጭ፣ ከኤንተርፕራይዝ ሶሉሽኖች እና ከሌሎች አገልግሎቶች አመነጫለሁ ብሏል።
° የውጭ ምንዛሪ ገቢም ወደ 976 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ለማሳደግ በእቅድ ይዟል።
° የኩባንያውን አጠቃላይ ሀብት 851 ቢሊየን ብር ለማድረስ አቅዷል።
° በሦስቱ ዓመታት ውስጥ ቀጥተኛና ቀጥተኛ ካልሆነ ታክስ በድምሩ 253 ቢሊዮን ብር እንዲሁም የትርፍ ድርሻ ክፍያ (ዲቪደንድ) በመፈጸም በድምሩ 111.3 ቢሊዮን ብር ለመንግስት ገቢ ለማድረግ አቅዷል።
° የ ሦስት አመት ስትራቴጂ ሲጠናቀቅ የ 4 ጂ ሽፋን 99 በመቶ እንደሚደርስ ተገልጿል።
° የቴሌ ብር ደንበኞች ደንበኞችን ቁጥር 75 ሚሊየን ለማድረስ አቅዷል።
በ2018 ዓም በጀት አመት :-
- የ4G አገልግሎት 2,270 የ4G ጣቢያዎችን በመጨመር የህዝብ ሽፋን ወደ 85 በመቶ በማሳደግ 550 ተጨማሪ ከተሞችን ያካተተ እንዲሆን።
- 5G አገልግሎት በ10 ተጨማሪ ከተሞች ለመዘርጋት ታቀደ ሲሆን የ5G ጣቢያዎች ቁጥር አሁን ካለበት 315 ወደ 490 ለማሳደግ።
- 1,228 አዲስ የሞባይል ጣቢያዎች ለመገንባት።
- 7.6 ሚሊዮን አዲስ የሞባይል አቅም በማከል አጠቃላይ የሞባይል ኔትዎርክ አቅሙን ወደ 112.4 ሚሊዮን ለማድረስ።
- 785 ሺህ የኮፐር መስመርን በፋይበር ለመተካት።
- 320,000 ደንበኞችን ከኮፐር ወደ ፋይበር ኔትዎርክ ለመዘዋወር።
- በዋና ዋና ከተሞች ለሚገኙ 1112 የሞባይል ጣቢያዎች በፋይበር ማገናኘት፣ 2000 ኪሎ ሜትር ተጨማሪ የሜትሮ ፋይበር ዝርጋታ ለማከናወን እና 356 አዳዲስFBB (OLT) መሳሪያዎችን ለመግጠም።
- የደንበኞችን ብዛት በ6 በመቶ በመጨመር 88 ሚሊዮን ለማድረስ የታቀደ ሲሆን በሞባይል ድምጽ 6% በመቶ በመጨመር 85.4 ሚሊዮን፣ በሞባይል ዳታና ኢንተርኔት በ13.3 በመቶ በመጨመር 52.8 ሚሊዮን እንዲሁም የመደበኛ ብሮድባንድ ደንበኛች በ23 በመቶ በመጨመር 1 ሚሊዮን በማድረስ አጠቃላይ የቴሌኮም ስርጸት መጠንን 77.2 በመቶ ለማድረስ።
- የ4ጂ ሽፋን ከ71 በመቶ ወደ 85 በመቶ በማሳደግ እና የ5ጂ አገልግሎት በማስፋፋት ለ1.8 ሚሊዮን ተጠቃሚዎች አገልግሎት መስጠት የሚችል አቅም ለመገንባት፡፡
- አጠቃላይ ገቢውን 235.8 ቢሊዮን ብር ለማድረስ እና የቴሌብር ተጠቃሚዎች ቁጥር በ14 በመቶ በማሳደግ 62.5 ሚሊዮን ለማድረስ በእቅድ መያዙን በዛሬው ዕለት በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ይፋ ተደርጓል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
@tikvahethiopia

❤604😡117🤔35😭16🙏10👏6💔3😱2😢2🥰1
group-telegram.com/tikvahethiopia/99475
Create:
Last Update:

BY TIKVAH-ETHIOPIA

Share with your friend now:
group-telegram.com/tikvahethiopia/99475