Telegram Group & Telegram Channel
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ስለ ግዕዝ ቋንቋ ትምህርት ምን አለ ?

በአማራ ክልል በመጪው የትምህርት ዘመን ከሦስተኛ ክፍል ጀምሮ በሁሉም ትምህርት ቤቶች የግዕዝ ቋንቋ መሰጠት ሊጀምር ነው።

የክልሉ ትምህርት ቢሮ ለሁሉም የዞን እና ከተማ አስተዳዳር ትምህርት መምሪያዎች በጻፈው ደብዳቤ ትምህርቱን ለመስጠት አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት እንዲደረግ አሳስቧል።

የክልሉ ትምህርት ቢሮ የሥርዓተ የትምህርት ዝግጅት እና ትግበራ ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ይገርማል አያሌው ለቢቢሲ  አማርኛ በሰጡት ቃል ምን አሉ ?

" በመጪው የትምህርት ዘመን በክልሉ በሚገኙ ሁሉም ትምህርት ቤቶች የግእዝ ቋንቋ እንደ አንድ የትምህርት ዓይነት ይሰጣል።

የግእዝ ቋንቋ ትምህርት በሙሉ ትግበራ ከሦስተኛ ክፍል ጀምሮ መሰጠት የተጀመረው ባለፈው ዓመት 2017 ዓ.ም. ነው።

በክልሉ 16 ዞኖች እና በ45 ወረዳዎች ውስጥ በሚገኙ የአንደኛ ደረጃ እና በመለስተኛ ትምህርት ቤቶች በመደበኛነት ሲሰጥ ቆይቷል።

ነገር ግን በመምህራን እጥረት ምክንያት በክልሉ በሚገኙ ሁሉም ትምህርት ቤቶች ማዳረስ ሳይቻል ቀርቷል።

ትምህርቱ ባለፈው ዓመት በሙሉ ትግበራ ደረጃ ሲሰጥ የቆየው ከ2015 ዓ.ም. ጀምሮ በሙከራ ደረጃ ሲሰጥ ከቆየ በኋላ ነው።

ያን ጊዜ የጀመሩት ተማሪዎች በዚህ ዓመት ስድስተኛ ክፍል ደርሰዋል። ሙከራ እየተደረገ እና በተማሪዎቹ ላይ ግምገማ እየተካሄደ ሥርዓተ ትምህርቱ እየዳበረ እና እየተዘጋጀ ነው የመጣው።

በመሆኑም ከሙከራ ፕሮግራሙ እና ባለፈው ዓመት ከተጀመረው መደበኛ የትግበራ ግምገማ በመነሳት በመጪው ዓመት በስፋት እንዲሰጥ ታቅዷል።

በትምህርት ፖሊሲ መሠረት ተማሪዎች ተጨማሪ ቋንቋ ወይም ሁለተኛ ቋንቋ እንዲማሩ የሚፈቀደው ከሦስተኛ ክፍል ጀምሮ በመሆኑ ትምህርቱ ከዚህ የክፍል ደረጃ መሰጠት እንዲጀምር ተደርጓል። " ብለዋል።

ግእዝ ቋንቋ በዓለማችን ረጅም ዕድሜ ካስቆጠሩ ጥንታዊ ቋንቋዎች መካከል አንዱ ሲሆን፣ በኢትዮጵያ ለሚነገሩ በርካታ ቋንቋዎች መሠረት እንደሆነ ይነገራል።

በግእዝ ቋንቋ ከጥንታዊው ዘመን አንስቶ በተለያዩ የዕውቀት ዘርፎች የተዘጋጁ ጽሁፎች እና እውቀቶች ያሉ ሲሆን፣ በበርካታ የዓለማችን ዩኒቨረስቲዎች እና የምርምር ተቋማት ውስጥ ይገኛሉ።

ከጊዜ ወደ ጊዜ የቋንቋው ተናጋሪዎች ቁጥር እየቀነሰ በመምጣቱ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስተ ተዋሕዶ ቤተ ክርስትያን ውስጥ ብቻ የተገደበ ሆኗል።

መረጃው የቢቢሲ አማርኛ አገልግሎት ነው።

@tikvahethiopia
243.39K👏615😡509🙏165😭54🕊32🥰31🤔27💔21😢19😱17

group-telegram.com/tikvahethiopia/99479
Create:
Last Update:

BY TIKVAH-ETHIOPIA

Share with your friend now:
group-telegram.com/tikvahethiopia/99479

View MORE
Open in Telegram

Telegram | DID YOU KNOW?

Date: |

Despite Telegram's origins, its approach to users' security has privacy advocates worried. WhatsApp, a rival messaging platform, introduced some measures to counter disinformation when Covid-19 was first sweeping the world. "Your messages about the movement of the enemy through the official chatbot … bring new trophies every day," the government agency tweeted. The regulator said it has been undertaking several campaigns to educate the investors to be vigilant while taking investment decisions based on stock tips. Since its launch in 2013, Telegram has grown from a simple messaging app to a broadcast network. Its user base isn’t as vast as WhatsApp’s, and its broadcast platform is a fraction the size of Twitter, but it’s nonetheless showing its use. While Telegram has been embroiled in controversy for much of its life, it has become a vital source of communication during the invasion of Ukraine. But, if all of this is new to you, let us explain, dear friends, what on Earth a Telegram is meant to be, and why you should, or should not, need to care.
from us

Telegram TIKVAH-ETHIOPIA
FROM American