Telegram Group & Telegram Channel
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
“ ትላንት ‘ለምርመራ ትፈለጋለህ’ ተብሎ እንደተደወለለት አሳውቆን ነበር። ዛሬ ግን ከቤቱ ወስደው እንዳሰሩት ነው ቤተሰቦች ደውለው ያሳወቁን ” - ማኀበሩ

የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች ማኅበር  ፕሬዜዳንት የሆኑት አቶ ዮናታን ዳኛው “ በጸጥታ ኃይሎች ” ተወስደው ዛሬ መታሰራቸውን ማኀበሩ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናገረ።

አቶ ዮናታን በጸጥታ ኃይሎች ከቤታቸው የተወሰዱት ዛሬ መሆኑን የገለጸው ማኅበሩ “  በአስቸኳይ እንዲፈቱ ”  ሲል አሳስቧል።

“ የማኀበርን ፕሬዝዳንትና ሌሎች አመራሮችን በማሰርና በማገላታት ‘እርቦኛል’ ብሎ አደባባይ የወጣን የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች ጥያቄ ማፈን አይቻልም፣ ፕሬዝዳንቱን በአፋጣኝ በመፍታት የጤና ባለሙያዎችን ጥያቄ በአፋጣኝ መመለስ እንዳለበት ማህበሩ ያምናል ” ሲል አክሏል።

አቶ ዮናታን ዛሬ እንደተወሰዱ የገለጸው ማኀበሩ “ ከዛ በፊት ትላንት ‘ለምርመራ ትፈለጋለህ’ ተብሎ እንደተደወለለት አሳውቆ ነበር ዛሬ ግን ከቤቱ ወስደው እንዳሰሩት ነው ቤተሰቦች ደውለው ያሳወቁን ” ብሏል።

“ ጥያቄው አጠቃላይ የጤና ባለሙያ ሆኖ ሳለ ጥያቄው በውይይት እንዲፈታ ያሳሰቡ ግለሰቦችን ማፈን ተገቢ ነውን ? ነገ እኛም ምን እንደምንሆን አይታወቅምና መልክታችን ይህ ነው ” ሲል ገልጿል።

“ ፕሬዝዳንቱ የታሰረው ለግል ጉዳዩ አደለምና ማህበሩን በመወከል ከፍተኛ ድምፅ እየሆነ ለነበረው ፕሬዝዳንት አጋርነታችሁን አሳዩ ”  ያለው የጤና ባለሙያዎች ማኅበሩ “ ሌሎች ጤና ባለሙያዎች ግለሰቦችን ማፈን የናንተን  ረሃብ አያስቀረውምና ፍትሃዊ ጥያቄያችሁን ከፖለቲካ በጸዳ መልኩ እንድትቀጥሉ አበረታታለው ” ብሏል።

“ በቅዱስ ጳውሎስ፤ አርባምንጭ፣ ወላይታ ሶዶ እና ሌሎች የተለያዬ አከባቢዎች ጤና ባለሙያዎች አፈናና ማዋከብ እየደረሰባቸው እንደሆነ እየሰማን ነው ” ሲልም ማኅበሩ ተናግሯል።

የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች ባለፉት ሳምንታት “ የቆዩና ምላሽ ያላገኙ ” ያሏቸውን 12 ጥያቄዎች ለጤና ሚኒስቴር ጭምር በማቅረብ የጊዜ ገደብ ሰጥተው ምላሽ እየጠበቁ እንደሆነ እና ምላሽ ካላገኙ ወደ ቀጣይ እርምጃ እንደሚገቡ እየገለጹ ናቸው።

የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች ማኅበር ከቀናት በፊት በሰጠን ቃል ፥ የጤና ባለሙያዎች ጥያቄ የዳቦ ጥያቄ መሆኑን በመግለጽ ሌላ መልክ ለማስያዝ፣ ወደሚፈልጉት አቅጣጫ ለመውሰድ፣ የፓለቲካ ትርፍ ለማግኘት የሚሯሯጡ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አሳስቦ ነበር።

ባለሙያዎች የሚነሱትን የመብት ጥያቄዎች መንግሥት አድምጦ እንዲመልስላቸው ጥያቄዎቻቸው ምንም አይነት የፓለቲካ አጀንዳ እንደሌላቸው ፤ ከዚህ የባለሙያዎች ጥያቄ ጋር በተያያዘ ነገሩን የራሳቸው በማስመሰል የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት የሚሞክሩ አካላትም አርፈው እንዲቀመጡ ነበር ጥሪ ያቀርበው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
😡2.26K😭290122🙏44😢32🕊26🥰13🤔13👏7😱5

group-telegram.com/tikvahethiopia/96670
Create:
Last Update:

BY TIKVAH-ETHIOPIA

Share with your friend now:
group-telegram.com/tikvahethiopia/96670

View MORE
Open in Telegram

Telegram | DID YOU KNOW?

Date: |

Artem Kliuchnikov and his family fled Ukraine just days before the Russian invasion. On February 27th, Durov posted that Channels were becoming a source of unverified information and that the company lacks the ability to check on their veracity. He urged users to be mistrustful of the things shared on Channels, and initially threatened to block the feature in the countries involved for the length of the war, saying that he didn’t want Telegram to be used to aggravate conflict or incite ethnic hatred. He did, however, walk back this plan when it became clear that they had also become a vital communications tool for Ukrainian officials and citizens to help coordinate their resistance and evacuations. On December 23rd, 2020, Pavel Durov posted to his channel that the company would need to start generating revenue. In early 2021, he added that any advertising on the platform would not use user data for targeting, and that it would be focused on “large one-to-many channels.” He pledged that ads would be “non-intrusive” and that most users would simply not notice any change. False news often spreads via public groups, or chats, with potentially fatal effects. However, the perpetrators of such frauds are now adopting new methods and technologies to defraud the investors.
from us

Telegram TIKVAH-ETHIOPIA
FROM American