✍የፍቅር ሐይል ግን ዐጂይብ ነው.. ሩሀችንንና ጀሰዳችንን የሚያጣምር አንዳች ውበት... ናፍቆቱ የማያልቅ፤ ውዴታው የማይሰለች፤ ትውስታው የሚነዝር አንዳች ነገር!
🌹ያ..የዘይነልዉጁድﷺ ፍቅር...ዱንያ ላይ በሚኖረን ቆይታ ህይወታችንን ሙሉ እሳቸውን አለመናፈቅ አይቻለንም። የናፍቆታችንን ሮሮ ለማስታገስ...አሏህ ይወፍቀንና ጀነት ላይ እስክናገኛቸው በትንሹም የሚያረግብልን ደግሞ ሰለዋት ነው!
« أَوْلَى النَّاسِ بِي يَوْمَ الْقِيَامَةِ أَكْثَرُهُمْ عَلَىَّ صَلاَةً »
«የዉመል ቂያማ ላይ ለኔ ቅርቡ ሰው ማለት እኔ ላይ ሰለዋትን የሚያበዛው ነው»አሉ ዘይነልዉጁድﷺ♥️
✍🌹اللهم صلّ وسلم وبارك على سيدنا محمد النبى الأمي الزكي البهي الصفي النجي الوفي وأمطر علينا سحائب لطفك الخفي وحبك الجلي وعلى آله وصحبه وسلم🌹
@MEDINATUBE

❤12👍1
✍
ሰላት የሌለው በምን ይረጋጋል??
ሰላት ባይኖረንስ በምን እንረጋጋ ነበር??
«يا بلالُ، أقِمِ الصَّلاةَ، أرِحْنا بها»
«ቢላል ሆይ! እስኪ ኢቃም በልና በሰላት አሳርፈን።»

👍10
ጭንቅ የበዛበት ሰለዋት ያብዛ የጋለ ብረት ውሃ ውስጥ እንደ መንከር እያየው ያሁሉ ጭንቅ ይወገዳል ።
@MEDINATUBE
@MEDINATUBE
❤12👍6🥰1
ዐርባ የሶለዋት ጥቅሞች
===============
ኢማም ኢብኑል‐ቀዪም [ረሒመሁላህ] እንዲህ ብለዋል: ‐
«ዐርባ ሶላት ዐለን‐ነቢይ [ﷺ] ጥቅሞች: ‐
❶ የአላህን ትእዛዝ መፈፀም።
❷ አላህም በነቢዩ [ﷺ] ላይ ሶለዋት ስለሚያደርግ ከአላህ ድርጊት ጋር መሳሰል። በእርግጥ የእኛና የአላህ ሶለዋት የተለያየ ነው። [የአላህ ሶለዋት እዝነት ሲሆን ከኛ ሲሆን ደግሞ ዱዓ ነው።]
❸ ከመላኢካዎች ጋር መመሳሰል።
❹ አንድ ጊዜ ሶለዋት ያደረገ ሰው አላህ ዐስር ሶለዋት ያደርግበታል።
❺ ሰውየውን አላህ በዐስር ደረጃዎች ከፍ ያደርገዋል።
❻ ዐስር ሐሰና (የበጎ ሥራ ምንዳ) ይፃፍለታል።
❼ ዐስር ኃጢኣት ይሰረዝለታል።
❽ የዱዓን ተቀባይነት ያስገኛል።
❾ የሙስጦፋን [ﷺ] ምልጃ ያገኛል።
❿ ወንጀልን ለማሰረይ ምክንያት ይሆናል።
⑪ ሰውየውን አላህ ከጭንቀት ይገላግለዋል።
⑫ በቂያማ ቀን ሰውየው ከነቢዩ [ﷺ] ቅርብ ይሆናል።
⑬ ድኻ ለሆነ ሰው ሶለዋት የሶደቃን ቦታ ይሸፍናል።
⑭ አስቸጋሪ ጉዳይን ያገራል።
⑮ የአላህና የመላኢካዎችን ሶለዋት ያስገኛል።
⑯ ሰውየውን ከወንጀል ያፀዳዋል። ንፅህናን ያላብሰዋል።
⑰ ሰውየው ከመሞቱ በፊት በጀነት እንዲበሰር ያደርጋል።
⑱ ከቂያማ ቀን ድንጋጤ ይጠብቃል።
⑲ ሰውየው የረሳውን ነገር እንዲያስታውስ ያደርገዋል።
⑳ ለሰላምታው የነቢዩን [ﷺ] ምላሽ እንዲያገኝ ያደርገዋል።
21. ስብሰባን ያሳምራል። ሶለዋት የተደረገበት ስብሰባ በቂያም ቀን ቁጭት አይከተለውም።
22. ድህነትን ያስወግዳል።
23. ስስትን ያስወግዳል።
24. አፍንጫው ይታሽ (ውርደት ይንካው) ብለው ነቢዩ [ﷺ] ካደረጉት ርግማን ይድናል።
25. ወደ ጀነት መንገድ ያስገባል። ሶለዋት የተወ ሰው ደግሞ ከጀነት መንገድ ይርቃል።
26. ከስብሰባ ክርፋት ያድናል። ምክንያቱም አላህና መልክተኛው [ﷺ] የማይወሱበት ስብሰባ ሁሉ የከረፋና የገማ ነው።
27. ኹጥባንም ሆነ ሌላን ንግግር ያሳምራል።
28. ሰውየው በሲራጥ ላይ የሚኖረውን ብርሃን ያበዛለታል።
29. ሰውየውን ከጭካኔ ያፀዳዋል።
30. ሶለዋት የሚያደርግ ሰው በምድርም ሆነ በሰማይ መልካም ስም እንዲኖረውና እየተወደሰ እንዲኖር ያደርገዋል።
31. ሶለዋት የሚያበዛ ሰው የተባረከ ይሆናል። ስራውና እድሜውም በረካ ይሆንለታል።
32. የአላህን እዝነት ያገኛል።
33. ሰውየው ለአላህ መልክተኛ ﷺ ያለው ፍቅር ዘውታሪ እንዲሆን ያደርጋል።
34. ዘውታሪ የሆነ የአላህ መልክተኛን [ﷺ] ውዴታ ያገኛል።
35. ቀና መንገድ መመራትን (ሂዳያ) ያገኛል። ቀልቡም ህያው ይሆንለታል።
36. የሰውየው ስም በነቢዩ [ﷺ] ፊት እንዲጠራ ያደርጋል።
37. በሲራጥ ላይ የሰውየው እግር እንዲፀና ያደርጋል።
38. ሰውየው የነቢዩን [ﷺ] ሐቅ በከፊል እንዲወጣ ያግዘዋል።
39. ሶለዋት አላህን መዝከርና ማመስገንን ያካተተ በመሆኑ ሰውየው ከአመስጋኞችና ከዛኪሮች ተርታ እንዲመደብ ያደርገዋል።
40. ሶለዋት ዱዓም ነው። ምክንያቱም በሶለዋቱ ሰውየው አላህ በሚወዳቸው እና በመረጣቸው ነቢይ ላይ ውዳሴውን እንዲያደርግ መለመን ማለት ነው። በዚያውም ሰውየው ጉዳዩ እንዲፈፀምለትና ጭንቀቱ እንዲወገድለትም እየተማፀነ ነው።
--------------------------
📚 «ጀላኡል‐አፍሃም ፊ ፈድሊስ‐ሶላቲ ወስ‐ሰላሚ ዐላ ኸይሪል‐አናም ﷺ»
አህባቦቼ በዱኣ እና በዚክረ ሶላት ዓለ ነብይ ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንበርታ
ፋጢመቱ✍️✍️✍️

👍7❤4
ይህ መቃብር የማን ይመስልሀል?
10.4 ቢሊዮን ዶላር ባለቤት ባለፀጋ የኩዌታዊ ታዋቂው ነጋዴ የናስር አል-ከራፊ መቃብር ነው።
ተመልከት አንድ ሳንቲም አብሮት አልተቀበረም ገንዘቡ ለወራሾች ጥሎት ነው የሄደው አላህ ይዘንለት መቃብሩም ከሌሎች የተለየ አይደለም ኢስላም የሀብታም እና የድሀ መቃብር ልዩነት የለውም።
ሀብት ያላችሁ አብሯችሁ ለማይቀበረው ገንዘብ ለተቸገሩት አጉርሱ ለታረዙት አልብሱ ሞት ሳይቀድማችሁ።
ሰጥቸህ ነበር ምን ሰራህበት ጥያቄ አለብህና።

❤9😢7
አብሬት || አብሬድ
____የጦሪቃው አውራድ ጎርፍ መፍሰሻ
አብሬድ ማለት ከአውራድ የተያዘ ሲሆን የጦሪቃችን አውራድ ጎርፉ የሚፈስበት ቦታ ነው::
<ቀደሠላሁ ሢረሁ>
▪️
አብሬቶች ድቅድቅ ባለው ጨለማ ወቅት 7ቤት ጉራጌ ሁላ ለአምልኮ ከሚጟዝላቸው ፥ ከሚገብርላቸው ፥ እንደ ንጉስ ከሚያዩዋቸው ከጣኦት አምላኪያን መሪ ቤተሰብ የወጡ ፀሀይ ናቸው:: ተተኪ የሀይማኖቱ መሪ ይሆናሉ ተብሎ ሲጠበቁ ኑረል ኢማንን ይዘው ብቅ ያሉ ፥ ሺርክን ከስሩ መንግለው የጣሉ ፥ ለኸልቁ እንደ ፀሀይ የበሩ የአላህ ኑር ናቸው:: ሠይዲ አባ ራሙዝ በአንዱ መድሀቸው መሽረብ ሸይኻቸውን ሠይድ ባኡ ሳኒ <በድቅድቁ ጨለማ መካከል የበሩ ፍጹም የሆኑ ሙሉ ጨረቃ> ብለው ያወድሷቸዋል::
▪️ሠላም ዐለይከ ሸምሠል ዲነል ኪራሚ
▪️በድሩል ዘማን ፊ ወሰጢ ዞላሚ
በጉራጌ እና አጎራባቾቹ ላይ ያለ ሙስሊም ሁሉ የሁዋላ ታሪኩን ቢያጤን አራት እና አምስት አባቱን ወደሁዋላ ቢቆጥር ከመቶ መቶ ወይንም ዘጠና ዘጠኝ ፐርሰንቱ ጨለማ ላይ የነበረ ህዝብ ነበር:: ሙሉ ሰባት ቤት ጉራጌ ማለት ይቻላል መብረቅ አምላኪ ህዝብ ነበር:: በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ መልኩ ለዛሬው ማንነታችን ለሂዳያችን ሰበብ ከአብሬት ሸይኾች አንዱ ሆነው እናገኛዋለን:: በተለይም ለጉራጌ ማህበረሰብ:: ነገር ግን ከአብሬት የወጣው ፀሀይ በጉራጌና አጎራባቾቹ ብቻ ተገድቦ የቀረ አይደለም:: ብዙሀኑን የሀገራችንን ክፍሎች አካሎ ከሀገር ውጪም ፀሀያቸው በርቷል::
▪️
በታላቁ የረጀብ ወር በእነዚህ ከዋክብቶች ሀሪማ ሐረመል አብሬት የከውኑ ሁላ ንጉስ የነብያችንﷺ መውሊድ እጅግ ደማቅ በሆነ መልኩ ይከበራል:: የጦሪቃው አውራድ እንደ ጎርፍ ይፈሳል ፥ የአላህ ራሕመት ይዘንባል ፥ የነብያችንﷺ ኑር ይንቧቧል ፥ መላይካው እንደ ጉድ ይወርዳል ፥ የታላላቅ አውሊያዎች ሩሕ ይሀደራል። ከሚታየው የማይታየው ታዳሚ ይበልጣል:: እናልህ ወዳጄ አብሬት ለመግባት ጟዝህን ጠቅልል ከዚህ ማኢዳ ተቋደስ::
አ ብ ሬ ት ..... ረ ጀ ብ
አላህ ይውስደን እዚህ የተከበረ ቦታ🤲🤲

👍18❤10
ሰይዲና ዑመር በአንድ ወቅት ወደ ረሱል ሄዱና ሰይዲና አባበክርን እንዲህ ሲሉ ከሰሱ...
"ሁሌም አባ በክር እኔ ሰላምታ ካለቀረብኩለት ሰላምታን ቀድሞ አያቀርብልኝም አላቸው"
ረሱሉም አባ በክር ሲመጣ ጠየቁት ለምን እንዲህ
ታደርጋለህ አባበክር አሉት ....አባ በክርም እንዲህ ሲል መለሰላቸው...
እርሶ ሙስሊም ወንድሙን ሰላምታ ቀድሞ
ያቀረበለት ሰው ጀነት ላይ ህንፃ ይገነባለታል ስትሉ
ሰምቻለሁና ያ ህንፃ ለዑመር እንዲገነባለት ፈልጌ ነው አላቸው ...ዑመርም ይህን ሲሰሙ አለቀሱ🥺😊
እንዲህ ነበሩ በረሱሉ ተርቢያ የተገነብ ሰሀቦች
በዲን የተሳሰረ ውብ ወንድማማችነታቸው
ይህ ነው እንግዲህ ውብ ኢስላም ይህ ነው
እውነተኛው ወንድማማችነች ....
አላህ ይህንን ምርጥ ትውልድ በማይሻለው
ውብ ቃሉ በማረ አገላለፅ ፈለጋቸውን እንከትል
ዘንዳ እንዲህ ይገልፅልናል አስተውሉትማ...😊
{مُّحَمَّدٌ رَّسُولُ اللَّهِ ۚ وَالَّذِينَ مَعَهُ أَشِدَّاءُ عَلَى الْكُفَّارِ رُحَمَاءُ بَيْنَهُمْ ۖ تَرَاهُمْ رُكَّعًا سُجَّدًا يَبْتَغُونَ فَضْلًا مِّنَ اللَّهِ وَرِضْوَانًا ۖ سِيمَاهُمْ فِي وُجُوهِهِم مِّنْ أَثَرِ السُّجُودِ ۚ ذَٰلِكَ مَثَلُهُمْ فِي التَّوْرَاةِ ۚ وَمَثَلُهُمْ فِي الْإِنجِيلِ كَزَرْعٍ أَخْرَجَ شَطْأَهُ فَآزَرَهُ فَاسْتَغْلَظَ فَاسْتَوَىٰ عَلَىٰ سُوقِهِ يُعْجِبُ الزُّرَّاعَ لِيَغِيظَ بِهِمُ الْكُفَّارَ ۗ وَعَدَ اللَّهُ الَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ مِنْهُم مَّغْفِرَةً وَأَجْرًا عَظِيمًا}
"የአላህ መልክተኛ ሙሐመድ እነዚያም ከእርሱ ጋር ያሉት (ወዳጆቹ) በከሓዲዎቹ ላይ ብርቱዎች በመካከላቸው አዛኞች ናቸው፡፡ አጎንባሾች፣ ሰጋጆች ኾነው ታያቸዋለህ፡፡ ከአላህ ችሮታንና ውዴታን ይፈልጋሉ፡፡ ምልክታቸው ከስግደታቸው ፈለግ ስትኾን በፊቶቻቸው ላይ ናት፡፡ ይህ በተውራት (የተነገረው) ጠባያቸው ነው፡፡ በኢንጂልም ውስጥ ምሳሌያቸው ቀንዘሉን አንደአወጣ አዝመራና፣ (ቀንዘሉ) እንዳበረታው፣ እንደወፈረምና፣ ገበሬዎቹን የሚያስደንቅ ኾኖ በአገዳዎቹ ላይ ተስተካክሎ እንደ ቆመ (አዝመራ) ነው፡፡ (ያበረታቸውና ያበዛቸው) ከሓዲዎችን በእነርሱ ሊያስቆጭ ነው፡፡ አላህም እነዚያን ያመኑትንና ከእነርሱ በጎዎችን የሠሩትን ምሕረትንና ታላቅ ምንዳን ተስፋ አድርጎላቸዋል፡፡"
[ሱረቱል ፈትህ:29]
በዚህ ፍቅር የዚህ ስነምግባር ችቦ ለኳሽ በሆኑት
اللَّهُــمَّ صَلِّ وَسَـــلِّمْ وَبَارِك علــى نَبِيِّنَـــا مُحمَّدﷺ
💚💚💚
@medinatube

❤15
"ረቢኢል አወል" 3"
መውሊድ ማክበር የተጀመረው አንዳንድ ሰዎች እንደሚሉት በፋጢሚይ ስርዓት ሳይሆን በራሳቸው በነብዩ ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም ነው።
ሰኞ ቀንን ለምን እንደሚፆሙ ተጠይቀው የተወለድኩበት እና የተላከሁበት ቀን ስለሆነ ነው። ብለዋልና (ሶሂህ ሙስሊም)
ከዚህ ሐዲስ ዕለቱን ማላቅ እና በኢባዳ ማሳለፍን እንማራለን። [ በመውሊድ ፕሮግራሞች ላይ የሚደረገውም ይኼው ነው ]
እለተ ሰኞን የምንፆመው የነብዩን መውሊድ ለማክበር ሲሆን በየአመቱ ደግሞ በረቢዕ ወር ነቢን በማስታወስ እናከብረዋለን።
*መውሊድ በኦፊሻላዊ ደረጃ እንዲከበር በመጀመሪያ ፈር የቀደደው የአዩባዊው ሱልጣኔት አካል የታላቁ ሙጃሂድ የሰልሃዳን አል-አዩቢ የእህት ባል የሆነው የኤርቤሉ አስተዳደር መሊክ ሙዞፈር ( 549-630) ሂጅሪያ ነው።
<<ንጉስ ሙዞፈር አቡሰኢድ አልከዋኪቢ ቸርና የተከበሩ ከሆኑ ትላላቅ ንጉሳን መካከል አንዱ ሲሆን ፣ ብዙ መልካም አሻራዎች አሉት። በወርሃ ረቢዑል አወል የተላቀውን የመውሊድ ስራ ይሰራ ነበር ። ታላቅ በዓልም ያዘጋጅ ነበር። ከዚህ ምግባሩ ጋር አይበገሬ ጀግና ፣ ጠንካራ ፣አስተዋይ ፣ ዓሊምና ፍትሐዊ ነበር። አሏህ ይዘንለት። ማረፊያውንም ያሳምርለት ። ለመውሊድ 300ሺ ዲናር ወጪ ያደርግ ነበር ።>>(ኢብን ከሲር፣አልቢዳየቱ ወልኒሃያ ገጽ 13/136

❤14🥰1
የጋሩ ሂራ ሲር 💚
የአላህ መልዕክተኛ ﷺ ወህዩ ከመምጣቱ በፊት ቀን በቀን እውን የሚሆኑ ህልሞችን መመልከት ጀመሩ። አያታቸው አብዱልሙጠሊብ አግኝተውታል ተብሎ ወደሚነገርለት የጋሩ ሂራ ዋሻ መገለልንም መረጡ። አንዳንዴ ለሳምንታት፤ አንዳንዴም ለወራቶች ይቆዩ ነበር ይላሉ። ይህንን የመገለል ተግባር «التحنث» ይሉታል። ልክ እንደ እናታችን ኸዲጃ አጎት ወረቃ ወደ አንድ አምላክ ብቻ ተቅጣጩ። ጥሞናን መረጡ። ከማህበረሰቡ ተገለው ማስተንተንን ወደዱ 💚
የጋሩ ሂራ ዋሻ ልክ እንደሌላ ዋሻ ሰፊ ቀዳዳ ያለው አይነት ሳይሆን አንድ ሰው ብቻ የሚያስቀምጥ ነው፤ ወደ ከዓባ'ም የዞረ መሆኑ ይበልጥ ይደንቃል። ዋሻው ካለበት ተራራ በታች ከዓባ ግልፅ ሆኖ ደምቆ ይታያል። የሪሳላው መጀመሪያ ከሆነ ቦታ ላይ የመልዕክታቸው ማገባደጃ የሆነውን ከብዙ መከራ በኃላ ድል የሚያደርጉትን የአላህ ቤት ይመለከታሉ። 😍
የነህጀል ቡርዳ ሻዒር አህመድ ሸውቂ ስለ ጋሩ ሂራና ስለነበረው እንዲህ በማለት ይገጥማሉ:
****
سائل حراء وروح القدس هل علما
مصون سر عن الإدراك منكتم
كم جيئة وذهاب شرفت بهما
بطحاء مكة في الإصباح والغسم
💚
ሐቢበላህ ﷺ ስለ ዋሻው ጊዜ ቆይታቸው እንዲህ በማለት ይናገራሉ: «ወህይ ከመምጣቱ በፊት ድንጋዬችና ጠጠሮች ወደ ጋሩ ሂራ በምሄድበት መንገዴ ላይ ሰላምታን ያደርሱልኝ ነበር።» ይላሉ!
በዚህ የዋሻ ቆይታቸው መሐል ረሱሊﷺ ለብዙ ጊዜያቶች ሚስታቸውን እና ልጆቻቸውን ጥለው መውጣታቸውን ያስተዋሉ የመካ ሴቶች እናታችን ኸዲጃ ላይ ያፌዙ ጀመር። «ሁሉም ነገርሽን ሰጥተሽው አሁን አንቺን ጥሎሽ ሄደ።» ይሏታል። ውዷ ሚስታቸው ግን የእነሱን ወሬና አሉባልታ ከቁብ አትቆጥረውም ነበር! «ለምን ሄዱ? ዋሻው ውስጥ ምን አለ? ዝምታን ለምን ወደዱ?» ብላ ጠይቃ አታውቅም። ፍቅር የሚገለፀው በዚህም አይደል? አላህ ከሁሉም ሴቶች የመረጣትም ለዚህ አይደል?! ✨💚
ይልቅ እንደውም ያንን ረጅም ተራራ፤ ፀሐዩና አቧራው ሳይበግራት ቀን በቀን እየወጣች ምግብ ትወስድላቸው ነበር። በሁሉም እንቅስቃሴያቸው ላይ አጋዣቸው ናት፤ ታምናቸዋለች፤ ከነፍሷ በላይ ታፈቅራቸዋለች። ኣህ ያ ኸዲጃ!
ጊዜው መጣ፤ ከብዙ ወራቶች መገለል በኃላ በህልማቸው በተደጋጋሚ የሚያዩት አካል(ሰይዲና ጂብሪል) ሒራ ዋሻ ውስጥ ባሉበት ወደእርሳቸው ይመጣል። በዚህ ድንቅ ዋሻ የመጀመሪያው የአላህ ቃል ይነበባል!... ነቢየላህ'ም ጨለማውን በተሰጣቸው መለኮታዊ ብርሓን ሊያበሩ የነብይነት ተልዕኮ እዚህ ቦታ ላይ ተሰጣቸው! ... ይህ ቦታ የዓለሙን መድኅን አቅፎ ያስተናገደ ድንቅ ቦታ ነው!
ረቢዑል አንዋር እየመጣልን ነው አልሃምዱሊላህ!... መንደሩንም ኑር በኑር እናደርገዋለና ኢንሻአላህ 🥰
አላሁመ ሰሊ ወሰሊም አላ ሰይዲና ወሸፊዒና ወሐቢቢና ሙሐመድ ﷺ 💚

❤8👍2
ሁሌም ይሄን ሃዲስ ሳነበው ስሰማው ወላሂ በጣም ይገርመኛል
‹‹ከናንተ በፊት የነበሩ በኒ እስራኤላውያኖች መሀከል ሶስት ሰዎች ለጉዞ ተንቀሳቀሱ በመንገድ ላይ እያሉ መሸባቸው ሲመሽባቸው ለአዳር ከአንድ ዋሻ ውስጥ ገቡ ከተራራ ላይ የነበረ አንድ ቋጥኝ ተንከባሎ ዋሻውን ዘጋባቸው ተጨነቁ አላህን በመልካም ተግባራችን ካለመነው በቀር ከዚ ቋጥኝ የሚያድነን ነገር ምንም አይኖርም ስንገባም ማንም ያየን የለም ተባባሉ ከመካከላቸው አንዳቸው እንዲህ አለ፡-
👉 ‹‹አላህ ሆይ! አዛውንት ወላጆች ነበሩኝ እነሱ ሁሌም ወተት አጠጣቸዋለሁ ከመጠጣታቸው በፊት ቤተሰቦቼንም ልጆቼንም እንዲሁም ባርያዎቼን ወተት አላጠጣም ነበር አንድ ቀን እንጨት ለቀማ ሩቅ ቦታ ሄድኩ አጋጣሚ አምሽቼ ነበር እና ስመጣ ወደቤት ተኝተው አገኘኋቸው ወተቱን አልቤ ልቀሰቅሳቸው ስል እንቅልፍ ላይ ሆነው መቀስቀስ አልፈልኩም አሳዘኑኝ እንቅልፍ ማቋረጥ ከነርሱ በፊትም ቤተሰቤን ማጠጣትም አልፈለኩም ወተት የያዘውን ዋንጫ በእጄ እንደያዝኩ መንቃታቸውን ስጠባበቅ ህጻናት ልጆቼ ከእግሮቼ ስር ይንጫጫሉ እባክህን አጠጣን እራበን እያሉ ያለቅሳሉ ይንጫጫሉ ሳላጠጣቸው ልጆቼም ተኙ ወላጆቼ ከእንቅልፋቸው እስኪነቁ ስጠብቅ ሳለ ነጋ ጎህ ቀደደ ወላጆቼም ተነስተው ወተታቸውን ጠጡ አላህ ሆይ! ይህንን ድርጊት የፈጸምኩት ያንተን ውዴታ ከጅዬ ከሆነ በዚህ ቋጥኝ ሰበብ ከደረሰብን መከራ አውጣን ቋጥኙ ትንሽ ከፈት አለ ትንሽየ አየር አገኙ ግን መውጣት የማያስችላቸው ያክል ነው፡፡
👉 ሌላኛው ደግሞ እንዲህ አለ ፡-
አንዲት ልጅ ነበረችኝ እጅግ አፈቅራት ነበር፡፡››
‹‹ አንድ ወንድ አንዲትን ሴት የሚያፈቅራትን የመጨረሻው የፍቅር እርከን ያህል አፈቅራታለሁ በወሲባዊ ተራክቦ ጠየቅኳት ፍቃደኛ አልሆነችም አላህን የምትፈራ ሴት ነበርች አንድ የድርቅ ዓመት ተከሰተ (እርዳታዬን ፈልጋ) ወደኔ መጣች የምፈልገውን እንድፈጽም ቃል አስገብቼ አንድ መቶ ሀያ ዲርሀም ሰጠኋት ቃሏን አከብራ መጣች
ከዚያም ወሲብ ልፈፅም ፊቷ ቀረብኩ ልጅቷም አላህን ፍራ ያለ አግባብ ያለ ሀላል ክብረ-ንጽህናዬን አታበላሽ አለችኝ ከ አጠገቧ ዘወር አልኩ ምንም ነገር ሳልፈጽም፡፡ ከማንም አብልጬ እዎዳታለሁ የሰጠኋትንም ወርቅ ብድር ተውኩላት አላህ ሆይ! ይህንን ተግባር የፈጸምኩት የአንተን ውዴታ ከጅዬ ከሆነ ካለንበት መከራ አውጣን::» ቋጥኙ ትንሽ ከፈት አለ መውጣት ግን አይችሉም፡፡››
ሦስተኛው እንዲህ አለ ፡-
👉 ‹‹ ሰራተኞች ቀጥሬ አሰራ ነበር ለሁሉም ያገለገሉበት ክፍያቸውን ከፈልኳቸው ከመካከላቸው አንዱ ሲቀር ድርሻውን እኔ ዘንድ ትቶ ሄደ አንሶኛል አልፈልግም ብሎ ትቶ ሄደ ትቶ የሂደውን ገንዘብ ጥራጥሬም ፍየልም በግም እየገዛሁ እያራባሁ እየገዛሁ እየሸጥኩ ብዙ ብሮች አተረፍኩለት ብዙ ሀብት እስኪሆን ድረስ ከዘመናት በኋላ ችግር አጋጥሞት ያ የቀጠርኩት ሰራተኛ ወደ እኔ መጣ እንዲህም አለኝ ፡- ‹‹ዐብደላህ ሆይ! ድርሻዬን ስጠኝ›› አለኝ ይህ የምትመለከተው ሁሉ ግመሉም ከብቱም ፍየሉም ባሪያውም ድርሻህ ነው አልኩት ‹‹ ዐብደላህ ሆይ! አትቀልድብኝ›› አለኝ፡፡ እየቀለድኩብህ አይደለም አልኩት ሁሉንም ተረክቦ እየነዳ ወሰደ አንዳችም ነገር አልተወም አላህ ሆይ! ይህንን የፈጸምኩት ያንተን ውዴታ በመሻት ከሆነ ካለንበት መከራ አውጣን::» ቋጥኙ ተከፈተ ወጥተው ጉዟቸውን ቀጠሉ፡፡
@MEDINATUBE
የአላህ መልክተኛ (ሶ.ዐ.ወ) ተከታዩን ሲናገሩ አድምጫለሁ በማለት "አቡ ዐብዱረህማን ይናገራል፡-

(ቡኻሪና ሙስሊም)
@MEDINATUBE
❤9🥰3
#ትኩረት ❗️❗️
ዛሬ እኛው የሱፍይ መሻይኽ ልጆች ነን የምንለው የሀድራ ወዳጅ ነን የምንል ሰዎች ይሄን ነገር አንድ ሆነን እነዚህን ልጆች ካልተቃወምነው ነገ ምን ሊመጣ እንደሚችል ማሰብ እንኳ አይቻልም!!!
የሰው ልጅ እንዴት ይሄን ያክል ይወርዳል ቆይ! እንዴት ሸሪአውን አያይም? እንዴት ለሚጠሩትስ ለትልቁ ሰው ለሰይዳችን صلى الله عليه وسلم ሀያዕ አይኖረውም!?
አላህን ፍሩ! ተሰዉፍ እና ሱፍያ ከነ ማዕረግና ክብሩ ከናነተ የጠራና ሃላፊነት የማይወስድ መሆኑን በስሜ ለመላው መድሕ ወዳድ ማረጋገጥ እንፈልጋለን ። የዚህ አይነቱን ስራ ከማንም በላይ ቅድሚያ የምቃወመው እኛው የሀድራ ወዳጆች ነን።
በመድህ ላይ ድንበር ታልፏል አስቸኳይ መልእክት! ይሄን ነሺዳ ቪዲዮ ለመስራት የተገደድነው የመድሁን አለም ለመታደግና ከመሸርሸር ለመጠበቅ ሲባል ነው። ቪዲዮውን አንሱት አልያ ዘመቻውን አጠናክረን ለመቀጠል እንገደዳለን ለወንድሞቻችን እንዲደርሳቸው ሼር ሼር
ብዙ ጊዜ በሚሰሩት ነሺዳ ላይ ትችት አይጠፋቸውም ሆኖም ግን እኔ በእራሴ ማሕበራዊ ሚድያ ላይ ወገቤን አስሬ ለእነዚህ ልጆች ተከራከራያለሁ ይህ ይታወቅልኝ ሆኖም ግን ትክክል ያልሆነ ነገር ስሰሩት ከመተቸት ወደኋላ አንልም።
ዛሬም ነገም ወደፊትም ለሱፊያ ማሕበረሰብ እና የመሻይኾቻችን መድህ በአደብ እንደሰሩ ለማሳወቅ እንፈልጋለን ይህን ነሺዳ ቪድዮ ከዩቲዩብ ቻናል ላይ ማታጠፉ ከሆነ አይታችሁ የማታውቁት ቅጣት እንቀጣቸዋለን።

😢11👍4❤3🙏1
ወሀቢያዎች ከሚያናፍሱት ወሬ መካከል "መጀመሪያ መውሊድን የጀመሩት ዑበይዲዮች ናቸው የነሱን ፈለግ ነው የምትከተሉት ከነሱ ጋር ተመሳሰላችሁ"የሚለው ነው።በዚህም የሚፈልጉበት ለመውሊድ ያላቸውን ጥላቻ ለማንፀባረቅና በመውሊድ ዙሪያ መጥፎ ገፅታን ለመገንባት ነው።
ከመሰረቱ ዑበይዲዮች ማለት ከሞሮኮ አካባቢ ተነስተው እስከ ግብፅ ድረስ የተስፋፉ የጥመት አንጃዎች ነበሩ።
እኛ ለዚህ መልስ የምናቀርብላቸው በጥያቄ ይሆናል እሱም "እናንተ እንደምትሉት ከሆነ ኢብኑተይሚያ ስለ መውሊድ ሲናገር “መውሊድን ማላቅ ልዩ ቀን አድርጎ መያዝ የተወሰኑ ሰዎች እንደሚያደርጉት ማለት ነው፤ ለጥሩ እሳቤያቸውና ነቢዩን ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለምን ለማላቅ ለማክበር በመሆኑ ትልቅ አጅር አለው"ማለቱ የሚያሲዘው ዑበይዲዮች በግብፅ ምን ይሰሩ እንደነበር እያወቀ ነገር ግን የጀመሩት መወሊድ አጅር አለው እያለ ነው ማለት ነው።በዚህም አነሱን ያሞገሰና ያላቃቸው ሆነ ማለት ነው።እናንተ ደግሞ በተቃራኒው መውሊድን እነሱ ጀምረውታልና ጥመት ነው እያላችሁ ነው ሸይኻችሁ ደግሞ አጅር አለው እያለ ነው እንዴት ልትስማሙ ነው?
ወደኛ ስንመጣ መውሊድን ማክበር ለመቻሉ መረጃዎችን ስንጠቅስ ቁርኣንን ሐዲስንና ኢጅማዕን በማጣቀስ ነው የምናብራራው እንጂ በግብፅ የነበሩት እነንትና አክብረውታል በሚል አደለም።በመቀጠል ሙስሊም በዘገቡት ሶሒሕ ሐዲስ ላይ የዓሹራእ ቀንን ሱና ፆም እንድንፆም ከነቢዪ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም የመጣልን ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም አይሁዶችን በዛ ቀን ፆም ብለው ሲያሳልፉ አግኝተዋቸው ጠይቀዋቸው ከዛም እኛ ከናንት ለሙሳ የቀረብን ነን በማለት እሳቸውም ፆመው ኡመታቸውን እንዲፆሙ አመላከቱ ታዲያ ወሀቢያዎች ሆይ በናንተ አባባል መጀመሪያ አይሁዶች ስለቀደሙ ነቢዪ አይሁዶችን ተከተሉ ከነሱ ጋር ተመሳሰሉ እኛ አንፆምም ልትሉ ይሆን?
መውሊድን ባማረ ስብጥር እና በሃገር ደረጃ ማክበር የጀመሩት የኢርቢል ከተማ ንጉሱ አልመሊኩል ሙዞፈር አቡ ሰዒድ ኢብኑ ዘይኒዲን ኢብኒ በክተኪን እንደሆኑ ከጠቀሱ ዑለሞች መካክል አል ሓፊዙ አሲዩጢይ ሲሆኑ ከሱ በፊት መጀመሪያ አካባቢ በማክበር ከሚታወቁት መካከል ታላቅ ዓሊምና ሷሊሕ የሆኑት አልፈቂሁ አሻፊዒዩ ሙላ ዑመር አልመውሱሊይ አስከትሎም አል ቃዲ አለኽሚይ ይገኙበታል።
ወሀቢያዎች ለሙጃሂዱ #ሶላሑዲን አል አዩቢይ ጥላቻ እንዳላቸው ግልፅ ነው ምክንያቱም አሽዐሪይ ስለነበር።ለዛ የአል ሙጃሂድ ሶላሑዲን አል አዩቢይን እህት ያገቡት ንጉስ አል ሙዞፈረን ለማንቋሸሽ ደረጃቸውን በቻሉት መልኩ ለማውረድ ስብእናቸውን ለማጠልሸት የማይቆፍሩት ጉድጓድ የለም።ይሁንና ከራሳቸው ጎሳ የሆኑትን ወሀቢያዎች አጥብቀው የሚወዷቸውን የኢብኑ ተይሚያ ተማሪዎች ኢብኑ ከሲር እና አዘሀቢይ ስለ ንጉሱ አል ሙዞፈር የሚከተለውን በማለት የዚህን መልካም ጀግና መሪ ማንነት በኪታቦቻቸው አሰወፍረዋልና እሱን አጣቅሰን እንመልከት።ይህም ሁሌም ለወሀቢያዎች አንደሾህ ሆኖ ሲወጋቸው ይኖራል።
#ዘሃቢይ_ሲየር_አዕላሚ_ኑበላእ በሚባለው ኪታቡ ላይ 22ኛው ጁዝእ ከገጽ 335 እስከ 336 እንዲህ ሲል ስለ አመሊኩል ሙዞፈር ይጠቅሳል“አል መሊኩል ሙዞፈር...ሙጃሂዱን ሶላሁዲን አል አዩቢይን መኻደም ጀመረ አብሮትም ጂሃድ ወጣ ሶላሁዲን አል አዩቢይ አልመሊኩል ሙዞፈርን ወደደው በጣምም አስጠጋው እህቱንም ዳረው...ኢርቢልንም እንዲያስተዳድር ስልጣን ሰጠው...አል መሊኩል ሙዞፈር በጣም ሶደቃን ይወድ ነበር በየቀኑ ብዙ ዳቦ የሚያከፋፍል የነበረ ሲሆን...በየአመቱ ልብስ የሚያለብሳቸው፣ የሚመግባቸው፣ አንድ ዲናር ሁለት ዲናር የሚሰጣቸው ሰዎች ብዙ ናቸው...ለህመምተኞች ቤትን በመገንባት ሰኞና ሃሙስ ሁሌም እየመጣ ስለሁኔታቸው ይጠይቃቸዋል፣ይቀልዳቸዋል ከነሱ ጋርም ይውላል..."
ከዛም ሌሎች ስለሱ መልካም ነገሮችን ይዘረዝርና እንዲህ ይላል“በመውሊድ ላይ የሚያደርገውማ ለመግለጽ እጅጉን ይከብዳል...እንዳለ ኸልቁ ከዒራቅ እስከ አልጀሪያ ድረስ ወደሱ ይጎርፋሉ...ብዙ ዳሶች ይቆማሉ ይዋባሉምም...እዛም ላይ የውዳሴ ድምጾች ከፍ ይላሉ...እሱም በእያንዳንዱ ዳስ እየሄደ በቅርብ ሆኖ ይከታተላል ይመለከታል...ይህም ለቀናቶች ያህል የሚቀጥል ሲሆን...በመውሊዱ ላይ በጣም ብዙ ግመል፣በሬ፣በግ እና ፍየል ይታረዳሉ...ኢብኑ ዱህያ የሚባሉት ዓሊም የመውሊድ ኪታብ ጽፈው ለአልመሊኩል ሙዞፈር ሰጡት እሱም አንድ ሺህ ዲናር ሰጣቸው.........አልመሊኩል ሙዞፈር መልካም፣የሚተናነስ፣የሚወደስ ፈቂሆችን እና ሙሐዲሶችን የሚወድ ጥሩ ሰው ነበር”ይላል።
#ኢብኑ_ከሲር እስኪ ምን አለ? ኢብኑ ከሲር የኢብኑተይሚያ ተማሪና ወዳጅ ነው
አልቢዳየህ ወኒሃየህ በተባለ ኪታቡ 13ኛው ሙጀለድ ከገፅ 136 እሰከ 137 እንዲህ ይላል" የኢርቢል መሪ አልመሊኩል ሙዞፈር አቡ ሰዒድ ኩውከብሪይ ኢብኑ ዘይኒዲን ዐሊይ ሲሆን ከታላላቅ ፣ቸር እና የተከበሩ መሪዎች ውስጥ አንዱ ነው መልካም የሆኑ ነገራቶች ነበሩት እሱ ነው አል ጃሚዑ አል ሙዞፈሪይ የሚባለውን መስጊድ የገነባው........በረቢዑኒል አወል መውሊድን ያወጣ ነበር በሚገርም ሁኔታ ዝግጅትን ያዘጋጅ ነበር እሱ ጀግና ደፋር አቅለኛ ዓሊም ፍትሃዊ መሪ ነበር አሏህ ይዘንለት መኖሪያውንም ያማረ ያርገው........ አሸይኽ አቡል ኸጧብ ኢብኑ ዱህያ አንድ ሙጀለድ ኪታብ ስለመውሊድ በመጻፍ እና ስሙንም“አተንዊር ፊመውሊዲ አልበሺሪ አንነዚር” ሰይመው ለእሱ ሰጡት እሱም አንድ ሺህ ዲናር ሰጣቸው........ በ630 ሂጅራ አካባቢ ድረስ ማለትም እስከ ህልፈተ ሂወቱ ድረስ በስልጣን ላይ የቆየ ሲሆን በስልጣኑም ሆነ በስነምግባሩ ምስጉን ነበር”::ተመልከቱ እንግዲህ ወዳጃቸው ኢብኑ ከሲር እንዴት አመሊኩል ሙዞፈርን እያወደሰ እንደተናገረ።
#የኢብኑል_ጀውዚይ የልጅ ልጅ እንዲህ ይላሉ“ከአል ሙዞፈር መውሊድ ላይ የተገኙ እንዳሉት አምስት ሺህ ያህል በጎች፣አስር ሺህ ያህል ዶሮዎች፣በመቶዎች የሚቆጠሩ ፈረሶች፣መቶ ሺህ የሚሆን ቅቤ በእቃ ሆኖ፣ሰላሳ ሺህ ጣፋጭ ምግቦች በሳህን ሆነው ይቀርቡ ነበር.......ከመውሊዱ ላይ ታላላቅ ሱፊዮች፣ ሙሁሮች ይሳተፋሉ.....ከሱፊዮች ጋርም አብሯቸው በሃድራ ይወዛወዝ ነበር......በየአመቱ ለመውሊድ ሶስት መቶ ሺህ ዲናርን ያወጣል......ሚስቱ ራቢዐህ የሶላሁዲን አል አዩቢይ እህት እንዲህ ብላለች“የሚለብሰው ልብስ ሸካራና ዋጋው አምስት ዲናር የማይሞላ ልብስ ነበር”አንድ ጊዜ ላይ በዚህ ጉዳይ ላይ ስትወቅሰው እንዲህ አላት“እኔ የአምስት ዲናር ልብስ ለብሼ ሌላውን ሶደቃ ባወጣበት ይሻለኛል እኔ ውድ ልብስ ለብሼ ድሆችና ሚስኪኖችን ከምተዋቸው”አላት”ይላሉ።ተመልከቱ ምን አይነት ሰው እንደነበር....
አል ኢማሙ አሰኻዊይ እንዲህ ይላሉ“የመውሊድ ስራ የተጀመረው ከሶስቱ ክፍለ ዘመን በኋላ ነው ከዛ በኋላ ሙስሊሞች ከሁሉም አቅጣጫ በየትላልቅ አገሮች በመውሊድ መሰባሰባቸውን አላቆሙም በለይሎቹ የተለያዩ ሶደቃን ያወጣሉ፣የሰይዳችንን ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ታሪክ ያነባሉ.....በእነሱም ላይ የመውሊዱ በረካ በግልጽ ይታያል”አሉ::
ከመውሊዱ በረካ የምናገኝ አሏህ ያድርገን!
@Medinatube

❤10
27 አመታት ማህበረሰብን በማገልገል ላይ
የነብያቸን ﷺ ማዲድህ የኑር መስጂድ ኢማም እና ኻጢብ ሸይኽ ሰኢድ አህመድ የመኪና ስጦታ ተበረከተላቸው ።
የመውሊድን መቃረብ በማስመልከት በተዘጋጀው ፕሮግራም በመስጂዳችን ኑር መስጂድ በ ኢማምነት በዳዕዋ ለዘመናት ለሰጡት አገልግሎት የ ኑር መስጂድ ወጣት ጀመዐ እና የኑር መስጂድ ኮሚቴ ከ አህለል ኸይሮች ጋር በመተባበር ባዘጋጀው የምስጋና እና የ እውቅና ፕሮግራም ላይ የመኪና ስጦታ ተበርክቶላቸዋል ።
ስጦታውን ከ ክቡር ዶ/ር ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጅ ኡመር እድሪስ እና ከሸይኽ ሙሀመድ ሰብዬ እጅ ተቀብለዋል ።

❤16